Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቡና ግብይት አዋጅ ሊሻሻል ነው

የቡና ግብይት አዋጅ ሊሻሻል ነው

ቀን:

የአገሪቱን የቡና ወጪ ንግድ ለማሳደግና ከቡና ግብይት ጋር የተያያዙ ሕገወጥ ተግባራትን የበለጠ ለመቆጣጠር እንዲቻል፣ የቡና ግብይት አዋጅ እንደሚሻሻል ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማት ግብይት ባለሥልጣን እንዳስታወቀው፣ በአዋጁ ለማሻሻል ከሚካተቱ ዋና ዋና አንቀጾች መካከል ወደ ቡና ንግድ የሚገቡ ነጋዴዎች ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት፣ የብቃት ማረጋገጫ ሊያገኙ እንደሚገባ የሚያመለክተው አንዱ ነው፡፡ በቡና ንግድ ለመሰማራትና ፈቃድ ጠይቀው የኋላ ታሪክ ተጠንቶ ጭምር እንዲሆን የሚያስችል አሠራር እንደሚኖር፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ረዲ አህመድ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የቡና እሴትን ጨምሮ ለመላክ የጥሬ ቡና ግዢን የሚመለከተው ክፍል ላይ ማሻሻያ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በኢትዮጵያ የምርት ገበያ የቡና የጨረታ መነሻ፣ ዕለታዊ ገበያን መሠረት ባደረገ የጨረታ መነሻ ዋጋ እንዲካሄድ መወሰኑንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ከ2004 ወዲህ ዕለታዊ የጨረታ መነሻ ዋጋን መሠረት ያደረገ ጨረታ እንዲቋረጥ ተደርጎ ነበር፡፡ አሁን ግን ዕለታዊ የጨረታ መነሻ በማድረግ አምስት በመቶ ከፍና ዝቅ በማድረግ ጨረታው እንዲካሄድ በመወሰኑ በቀጣዩ ሳምንት ይጀመራል ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት 437 የሚሆኑ ላኪዎች ሲኖሩ፣ ከእነዚህ ውስጥ 54 ከላኪነት ታግደዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ቡና በአገር ውስጥ ገበያ እንዲውል በማድረጋቸው ጉዳያቸው በሕግ እንዲታይ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በቡና የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ላኪዎች ብቃትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ ያመለከቱት ዳይሬክተሩ፣ በዚህ ሥራ አዳዲስ ላኪዎች እንዲገቡ እንደሚደረግና የውጭ ኩባንያዎችም ተሳታፊ የሚሆኑበት አሠራር እንደሚመቻች አክለዋል፡፡

በቡና ግብይት ውስጥ ያለውን ችግር ለመፍታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መምከራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በዘርፉ ማነቆ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በቀጣይነት የሚወሰዱ ዕርምጃዎች ይኖራሉ ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ካሉ 437 ቡና ላኪዎች ውስጥ 120 ያህሉ 90 በመቶ የሚሆነውን ቡና ወደ ውጭ የሚልኩ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥም 60 በመቶውን ቡና ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡት 40 ላኪዎች ናቸው ተብሏል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...