Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ለአትሌቶች ቀጣይ ሕይወት ሥልጠና ሊሰጥ ነው

የኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ለአትሌቶች ቀጣይ ሕይወት ሥልጠና ሊሰጥ ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ጋር በመተባበር አትሌቶች በዕድሜና በሌሎች ምክንያቶች ሙያቸውን ካቆሙ በኋላ ቀጣይ ሕይወታቸውን ሊመሩበት የሚያስችላቸውን ሥልጠና ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ሥልጠናው የኦሊምፒክ ፕሮግራሞችን መሠረት ያደረገ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

እንደ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው መግለጫ ከሆነ፣ ፕሮግራሙ “Athlete Career Transition” በመባል በሚታወቀው የኦሊምፒክ ሥልጠና ፕሮግራም ውስጥ አትሌቶች ከአትሌትነት ሙያቸው ከተገለሉ በኋላ በቀሪው ሕይወታቸው ምን ይሠራሉ?  በምን ዓይነት የሙያ ዘርፍ መሰማራት ይችላሉ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ከመሆኑ ጎን ለጎን በራስ የመተማመን አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት መልካም እንደሚሆንላቸው ጭምር ተገልጿል፡፡  

ሥልጠናው በኦሊምፒክ ማዕቀፍ ከኦሊምፒክ ፕሮግራሞች ወይም ስፖርቶች ጋር ተጣጥሞ የሚሰጥ መሆኑን የገለጸው መግለጫው፣ ትምህርቱ በሁለት መልኩ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት የመጀመርያው አትሌቶች በፈለጉት የትምህርት መስክ መሠማራት ይችሉ ዘንድ የሥልጠናው ወይም የትምህርቱ ይዘትና የሚፈጀው ጊዜ፣ ሥልጠናው ወይም ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ እንዲሁም የሥልጠናው አሊያም የትምህርቱ አዋጭነት በኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ፣ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ለትምህርቱ በሚመረጡ አትሌቶች መካከል በሚደርሱበት ስምምነት የሚወሰን እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

በሁለተኛው አማራጭ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) “Athlete Learning Gateway Online” በሚል በቀረፀው የሥልጠና መስመር ውስጥ አትሌቶች በ‹‹ኦን ላይን›› የአትሌቱን ወቅታዊ ብቃት ለማሻሻልና በሌሎችም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዕውቀታቸውን እንዲያጎለብቱ የሚጠቀሙበት መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ለአብነትም የስፖርት አሠልጣኝነት፣ የስፖርት ቢዝነስ ማኅበረሰብና የስፖርት ሳይንስ (Sport coaching, Business of Sport in Society and Science of Sport) በሚለው ላይ ግንዛቤ ለማግኘት እንደሚረዳቸው ጭምር በመግለጫው ተካቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የኮሙኒኬሽንና ፕሮጀክት ባለሙያው አቶ ዳንኤል አበበ በመግለጫው አካተው እንዳስታወቁት ከሆነ፣ በዚህ የሥልጠና ማዕቀፍ ውስጥ ለመሳተፍ ስፖርቱን ከሚመራው የአገር አቀፍ ማኅበር የድጋፍ ደብዳቤና የአትሌቱ ማመልከቻ፣ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ በኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲና በአትሌቱ መካከል የተደረሰው ስምምነት፣ እንዲሁም የተመረጠው ትምህርት ለምን እንደተመረጠና ተገቢነቱን የሚገልጽ ማብራሪያ ከአትሌቱ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ በመጨረሻም በመጀመርያው አማራጭ ላይ አትሌቱ መማር የሚፈልገውን ትምህርት በመለየት ትምህርቱን ሊከታተልበት ካሰበው ዩኒቨርሲቲ ወይም የሥልጠና ማዕከል የገንዘብ ድጋፍ ያገኘበት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ጭምር ተጠቅሷል፡፡

ሥልጠናው ለሴቶችም ሆነ ለወንዶች እኩል መሆኑን የገለጸው መግለጫው፣ ለፕሮግራሙ መሳካት የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) አካል ከሆነው ኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግም አስታውቋል፡፡ በመሥፈርቱ መሠረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ካስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ መረብ ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ባድሜንተን ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት (አንድ ወንድና አንድ ሴት) አትሌቶችን ለመጀመርያ አማራጭ፣ ለሁለተኛው አማራጭ ደግሞ እያንዳንዳቸው አምስት አምስት አትሌቶችን ስም ዝርዝርና ሌሎችንም አስፈላጊ የሚባሉ ማስረጃዎችን እስከ ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲልኩ ተጠይቋል፡፡ ምርጫውን በተመለከተ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጠው የኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ መሆኑንም በመግለጫው ተካቷል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...