አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- አንድ ኪሎ ግራም የዶሮ ሥጋ
- ስድስት የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
- ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ሚጥሚጣ
- ስድስት የሾርባ ማንኪያ ደረቅ ጠጅ ወይም ግማሽ ጆግ የቀረረ እርሾ (መዘፍዘፊያ)
- ሁለት መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
- አንድ መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተገረደፈ የባሮ ቅጠል
- አንድ መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የካሮት ፍቅፋቂ
- ግማሽ ሊትር ወተት
አዘገጃጀት
- ዶሮውን በደንብ አጥቦ ይበልጥ ንፁህ እንዲሆን ለሩብ ሰዓት ደረቅ ጠጁ ወይም የቀረረው እርሾ ውስጥ ከዘፈዘፉ በኋላ በውኃ ማጠብ፤
- ቀይ ሽንኩርቱን፣ የባሮ ቅጠሉንና የካሮት ፍቅፋቂውን ማጠብ፤
- ወተቱን ከትንሽ ውኃ ጋር ጥዶ የዶሮውን ዋና ዋና ብልቶች (እግር፣ መላላጫና ፈረሰኛ)፣ የባሮ ቅጠሉንና የካሮት ፍቅፋቂውን አብሮ መቀቀል፤
- ሲበስል ሥጋውን ብቻ ከመረቁ ለይቶ ማውጣት፤
- ሥጋውን ንፁህ ዕቃ ላይ አድቅቆ መክተፍ፤
- የተከተፈውን ሥጋ መጥበሻ ላይ በቅቤና በሚጥሚጣ አመስ አመስ አድርጎ ማቅረብ፡፡
- ደብረ ወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) «የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት» (2003)