ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ችግር ውስጥ መሆናቸውን መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳረጋገጠ አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያውያኑ የት እንደሚገኙ ካይሮ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል እንዳጣራም አስታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በኮትዲቯር በተደረገ ውይይት የሊቢያ መንግሥት በሊቢያ የተንሰራፋውን የባሪያ ንግድ እንዲያስቆም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ ገልጸው፣ ይህንን ማድረግ ካልቻለ ግን የአፍሪካ አገሮች የራሳቸውን ዕርምጃ ለመውሰድ እንደወሰኑ ተናግረዋል፡፡
ለስደተኞቹ ደኅንነት ሲባል የት እንዳሉ ከመግለጽ የተቆጠቡት አቶ መለስ፣ ስደተኞቹን ለማስወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
ሊቢያ በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው መንግሥት አልባ የሆነ አገር ስለሆች፣ ምን ያህል ስደተኞች እንዳሉ ለማወቅ አስቸጋሪ አድርጎታል ሲሉ ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡