Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ይድረስ ለሪፖርተርይድረስ ለንግድ ባንኮችና ለማዕከላዊ ባንክ

ይድረስ ለንግድ ባንኮችና ለማዕከላዊ ባንክ

ቀን:

በሀገራችን የግል ኢንቨስትመንት ወደ ፋይናንሺያል ኢንዱስትሪው በመግባት የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ይገኛል:: እነዚህ የፋይናንስ ኢንደስትሪው ውስጥ ገብተው በመሠስራት ላይ የሚገኙትን ኩባንያዎች እንዲቆጣጠርና ወደፊት ወደ ኢንደስትሪው ለሚቀላቀሉት ተቋማት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ ፈቃድ እንዲሰጥ የማዕከላዊው ባንክ ማለትም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በአዋጅ የተደገፈ ህጋዊ ግደታ ፣መብትና ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

ከ2ዐዐ7 ዓ.ም በፊት በፋይናንስ ኢንደስተሪው ውስጥ የተሰማሩ አክስዮን ማህበራት አመታዊ የባለአክስዮኖች መደበኛ ሰብሰባቸውን የበጀት አመቱ በተጠናቀቀ በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ስብሰባ በመጥራት በቦርድ ስራ አፈፃፀምና ኦዲት በተደረገው የሂሳብ መዛግብት ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋሉ፡፡ ምንም እንኳን የሚደረገው መደበኛ ስብሰባ ከሚሰጠው ጊዜ አንፃርም ሆነ ከሚነሱት ሀሳቦች አንፃር አመርቂና በቂ ነው ተብሎ ባይታሰብም እንደነገሩ ሁኔታ ቦርዱ በሚያቀርበው የመነሻ ሀሳብ መሠረት ውሳኔዎች ይወሰናሉ፡፡ ከነዚህ ከሚወሰኑት ውሳኔዎች ውስጥ አብዛኛው የባለአክስዮን አባላት በአንክሮ የሚከታተሉት በበጀት አመቱ ውስጥ በተገኙው ትርፍ ላይ የሚደረገው ድልድል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

በትርፍ ድልድሉ ውሳኔ ከተወሰነ በኋላ ከሁለትት እስከ ሶስት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ኩባንያዎች ለባለአክስዮኖቻቸው ትርፍ ማከፋፈል ይጀምራሉ፡፡ በመሆኑም ባለአክስዮኑ የደረሰውን የትርፍ ድርሻ በሚፈልገው መንገድ ለሚፈልገው አላማ ያውለዋል፡፡ ይህን አይነት አሠራር ላለፉት አመታት ሲጠቀመበት በመቆየቱ ባለ አክሲዮኖች ለጉዳዩ መርሀግብር በማሙጣት አስፈላጊ ነው ብሎ ለሚያስበው ጉዳይ የሚደርሰውን ትርፍ ድርሻ ያውል ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አንዳንድ ባለአክስዮኖች የሚያገኙትን ትርፍ ድርሻ ለኑሮአቸው እንደ ብቸኛና ቋሚ ገቢ ምንጭ በመቁጠር ወጪያቸውን በዚሁ መሠረት ያቅዳሉ ያቀዱትንም ያከናውናሉ፡፡

- Advertisement -

ይህን የተለመደ አሠራር በመተው ከ2ዐዐ7 ዓ.ም አመታዊ ትርፍ ክፍፍል ውሳኔ ከተወሰነ በኋላ ወደ ብሄራዊ ባንክ ሄዶ መፅደቅ አለበት በሚል ምክንያት ባንኮችም ሆኑ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የትርፍ ድርሻ ድልድሉን ሳይከፍሉ ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ፡፡ የ 2008 ዓም የባለ አክሲዮኖች አመታዊ መደኛ ስብሰባ ከተካሄዳ በኋላ እስከ አሁን ድረስ የትርፍ ድርሻ ድልድለ አልከፈሉም፡፡ በመሆኑም የአስዮን ባለቤቶች ጥቅም መጉዳቱን መግለጽ አስፈላጊ አይደለም የሚል ይኖራል ማለት አይቻልም፡፡

በርከት ያሉ ባለአክስዮኖኖት በሚያገኙት የትርፍ ድልድል እንደ ዋና የገቢ ምንጭ በማድግ ኑሮአቸውን የሚመሩ እንዳሉ መገመት አስቸጋሪ አይሆንም ፡፡ ነገር ግን የማዕከላዊ ባንኩ ቁጥጥሩን አልጨረሰም በማለት የተመደበው የትርፍ ድልድል በወቅቱ ሳያገኙ በመቅረታቸው አንዳንድ ባለአክስዮኖች ችግር ላይ መውደቃቸው አልቀረም፡፡

እንደ ባለአክሰዮኖች እምነት ማዕከላዊ ባንኩ አስፈላጊ ነው ብሎ የሚያስበውን ቁጥጥር ማድረግ እንዳለበት ን የዚህም ቁጥጥር አስፈነጊነቱና ጠቀሜታው የጐላ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን በቁጥጥር ስም ባለአስዮኖች የትርፍ ድልድላቸውን ለረዥም ጊዜ ማለትም ከሁለት ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ሳያገኙ መቅረታው ፍትሀዊ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ በመሆኑም ማዕከላዊ ባንኩ ውሳኔውን በግልፅና በአስቸኳይ በመወሰን የግል ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለባለአክስዮኖቻቸው የተደለደለውን ትርፍ እንዲያከፋፍሉና ማከፍፈላቸውንም ማረጋገጥ ያለበት ይመስለኛል፡፡ አለበለዚያ ግን ማዕከላዊ ባንኩ የንግድ ባንኮችንና የኢንሹራንስ ኩባያችን እየተቆጣጠረ ነው ወይስ እያቆጣጠረ ነው ለማለት ድፍረት የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡

 

ከባለአክስዮኖች አንዱ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...