Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ጂቡቲ በአዲሱ ወደብ አገልግሎቶች ላይ የ45 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገች

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የጂቡቲ መንግሥት አዲስ በተገነባው የዶራሌ ወደብ የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ 45 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ፡፡ ደረቅ ጭነቶችና ከውጭ የሚገቡ ተሸከርካሪዎች ትኩረት ተሰጥቷችው የቅናሹ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

 

የወደቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዋሂብ ዳሂር አደን በወደቡ ጉብኝት ሲያደርጉ ለነበሩ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ቅነሳው የተደረገው በቅርቡ የጂቡቲ መንግሥት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

ዋና ሥራ አስኪያጁ የ45 ዋጋ ቅናሽ ይደረጋል ቢሉም፣ ውሳኔው ከተላለፈ ገና አንድ ሳምንት ብቻ ስለሆነው ተግባራዊ የሚደረግበት ጊዜ በውል እንደማይታወቅ አስታውቀዋል፡፡

የዶራሌ ወደብ በ580 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባ ሲሆን፣ እስካሁን 1.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጭነት ማስተናገዱ ተገልጿል፡፡ ወደቡ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 220 መርከቦችን እንዳስተናገደ ታውቋል፡፡

የወደቡን አገልግሎት የሚያገኙ መርከቦች በመጠናቸው ላይ በመመሥረት  ከ17 ሺሕ እስከ 25 ሺሕ ዶላር ክፍያ ይፈጽማሉ፡፡

ጂቡቲ እስካሁን በአምስት ወደቦች አገልግሎት ስትሰጥ የቆየች ሲሆን፣ የቀጣናው ማዕከል ለመሆንም ዕቅድ ይዛለች፡፡

ቀደም ሲል በወጣ ዜና በወደብ አገልግሎቶች ላይ የ45 በመቶ ጭማሪ ይደረጋል የተባለው ስህተት ስለነበር፣ ከድረ ገጽ ላይ መነሳቱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች