Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ይፍተር ዘሺፍተር›› – ማርሽ ቀያሪው ገድለኛ አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ሲሸኝ

ትኩስ ፅሁፎች

በሞስኮ ኦሊምፒክና በዓለም ዋንጫዎች በ5,000 ሜትርና በ10,000 ሜትር ሻምፒዮን የነበረው ገድለኛው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር፣ እሑድ ታኅሣሥ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ ስምንት ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲፈጸም ከነበረው ሥነ ሥርዓት ከፊል ገጽታ :: (ፎቶ በናሆም ተስፋዬና በዳንኤል ጌታቸው)

* * *

ፈተና

በሕይወት ላይ ቁማር

ስጫወት ቆይቼ

አንዳንዴም ስበላ

አንዳንዴም በልቼ

እንዲህ እንደዋዛ

አብረን ብዙ ኖረን

ምንም ሳናስበው

የሕይወት ፈተና

ማጣርያ ገጠመን

ጥሎ ማለፍ ሆነ

ፈተና መጣና

ሕይወት ጥላኝ ሄደች

አሸናፊ ሁና፡፡

  • ዘመላክ ብርሃኑ ‹‹ሳይሆን መጀን›› (2007) ዓ.ም.  

* * *

ለ18 ዓመት ከታካሚ ሆድ የቆየው መቀስ ወጣ

የ54 ዓመት ጎልማሳ ከሆነው ማቫን ናት ሆድ ዕቃ ከ18 ዓመታት በፊት የቀዶ ሕክምና ሲደረግለት የተረሳ መቀስ መገኘቱን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ በወቅቱ የመኪና አደጋ ደርሶበት የቀዶ ሕክምና ባደረገበት አጋጣሚ በሐኪሞች የተረሳው መቀስ ስድስት ኢንች ርዝመት ያለው ሲሆን ይህም ግለሰቡ በቅርቡ በተደረገለት አልትራ ሳውንድ ሊታይ ችሏል፡፡ በቬትናም ሃኖይ ከተማ ከዚህ ታካሚ ሆድ መቀሱን ለማውጣት የተደረገው ቀዶ ሕክምና ሦስት ሰዓት የፈጀ ነበር፡፡ ግለሰቡ ለዓመታት የሆድ ሕመም የነበረበት ሲሆን ከ18 ዓመት በፊት ቀዶ ሕክምና ያደረጉለት ሐኪሞች በመፈለግ ላይ ናቸው፡፡

* * *

ከእስር ያመለጠው ወንጀለኛ ፎቶውን ፌስቡክ ላይ ለጠፈ

በስርቆት ወንጀል ተፈርዶበት ከነበረበት እስር ቤት ያመለጠው ብራያን ብሪመር የተባለው እስረኛ ጥቅጥቅ ባለ አረንጓዴ ደን የተነሳውን ፎቶግራፍ ፌስቡክ ገፁ ላይ በመለጠፍ ፖሊሶችን ምን ታመጣላችሁ እያለ መሆኑ ተዘገበ፡፡

ብሪመር የለጠፈው ከእስር ካመለጠ ሌላ እስረኛ ጓደኛው ጋር የተነሳውን ፎቶግራፍ ሲሆን እስረኞቹ ባለፈው እሑድ ብራዚል ማስ ውስጥ ከሚገኙ ሁለት እስር ቤቶች ካመለጡ 72 እስረኞች መካከል ናቸው፡፡ ብሪመርና ጓደኛው ፎቶ መለጠፋቸውን ተከትሎ ጓደኛው ወዲያው ተይዟል፡፡

* * *

               የ64 ዓመቷ ቻይናዊት ወለዱ  

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ከወደ ቻይና ምናልባትም የዓለም ድንቅ ተዓምር ሳይፈጠር እንዳልቀረ ቻይና ዴይሊ ዘግቧል፡፡ በቻይና የመውለድ ዕድሜ ትልቅነት ቀዳሚዋ እንደሚሆኑ የተነገረላቸው የ64 ዓመቷ ሴት ልጅ ወልደዋል፡፡ በሰሜናዊ ቻይና ጀሊን ግዛት በ64 ዓመታቸው የወለዱት እናት ከዚህ በፊት ብቻ ልጃቸውን በሞት ተነጥቀው ነበር፡፡ አዛውንቷ የተገላገሉት በሙሉ ቀዶ ሕክምና ሲሆን ቀዶ ሕክምናውም በሰላም ነበር የተካሄደው፡፡ አዛውንቷ ግን ከባድ ድካም ነበረባቸው፡፡ ቢሆንም ግን እንደነቁ ሕፃኗን ፍለጋ እጃቸውን ዘርግተዋል፡፡  

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች