Tuesday, December 5, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የአካል ጉዳት ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችን ለማምረት ተስማማ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችን ለማምረት ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተስማማ፡፡

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ማኒስቴር ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ስምምነት መሆኑንና ወደ ምርት ስምምነት በቅርቡ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ 100 ሚሊዮን ከሚጠጋ ሕዝብ ውስጥ 17.6 በመቶ የሚሆኑት የአካል ጉዳተኞች መሆናቸውን፣ የዓለም ጤና ድርጅትና የዓለም ባንክ በጋራ ያካሄዱት የጥናት ውጤት ያሳያል፡፡ ይህ ቁጥር ማየትና መስማት የተሳናቸውንም ይጨምራል፡፡

በዓለም አቀፍ ሕጎችም ሆነ በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት መንግሥት የአካል ጉዳት ላለባቸው ዜጎች ምቹ ሁኔታን የመፍጠር፣ እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችን የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በሠለጠኑት አገሮች ዘመናዊ ሰው ሠራሽ እግሮችና እጆች በተመጣጣኝ ዋጋ ለአካል ጉዳተኞች የሚቀርቡ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ግን አካል ጉዳተኞችን በመርዳት ከመንግሥት ይልቅ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተሻለ ሪከርድ አላቸው፡፡ በመንግሥት በኩል ከሚታወቁ ድጋፎች መካከል፣ አካል ጉዳተኞች ከቀረጥ ነፃ የአካል ድጋፍ መሣሪያዎችን እንዲያስገቡ መፍቀድ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ጥቅማ ጥቅም ጥሩ የገቢ መሠረት ላላቸው አካል ጉዳተኞች ዕድል የሰጠ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አይደለም፡፡

የዓለም ባንክና የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ውስጥ 95 በመቶ የሚሆኑት በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡

በመሆኑም የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህንን መሠረታዊ የአካል ጉዳተኞችን ችግር ለመቅረፍ እንዲቻለው ነው፣ ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ላይ የደረሰው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለአካል ጉዳተኞች እንቅስቃሴ ድጋፍ የሚሰጡ ክራንቾችንና ዊልቸሮችን በማምረት ለሚኒስቴሩ እንደሚያስረክብና በተመጣጣኝ ዋጋ ለአካል ጉዳተኞች እንደሚሠራጭ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች