አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 175 ግራም ካሮት
- 175 ግራም ድንች
- 115 ግራም የዶሮ ፈረሰኛ (አጥንቱ የወጣ)
- 50 ግራም የተቀቀለ በቆሎ
- 300 ሚሊ ሊትር የሕፃናት ወተት
አዘገጃጀት
- ካሮቱን መፋቅ፣ ድንቹን መላጥና በቀዝቃዛ ውኃ አጥቦ በአራት ማዕዘን ቅርፅ መክተፍ
- የፈረሰኛውን ሥጋ አለቅልቆ በስሱ መክተፍና ከድንቹና ከካሮቱ ጋር ትንሽ ድስት ውስጥ መጨመር
- በቆሎና ወተቱን ጨምሮ ከድኖ የዶሮ ሥጋው እስኪበስል ድረስ ለ20 ደቂቃዎች መቀቀል፡፡ ለስልሶ ጓጓላው እስኪጠፋ ድረስ መፍጨት ወይም በማንኪያ ማድቀቅ
- በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ አውጥቶ መመገብ፡፡
- ሜላት ዮሴፍና ህሊና በለጠ ‹‹ጣዕም ያላቸው የሕፃናት ምግቦች›› (2009)