- Advertisement -

ዐዞ እና መንጋጋው

አንዲት እናት ልጇ የዓባይ ወንዝን ሲሻገር በዐዞ በመበላቱ፡-

‹‹ግባተ መሬቱን አትድገሙ እናንተ፣

ታዞ ሄዷል እንጂ ልጄ መቼ ሞተ፤›› በማለት ሙሾዋን ስታወርድ፣ እህቱም፣

‹‹ላንድ ቀን ትዕዛዝ ሰዉ ይመረራል፤››

የእኔ ወንድም ታዞ ዓባይ ላይ ይኖራል፤›› ስትል አባትም፣

‹‹ልጄን አትጥሉብኝ ቢያዛችሁ ተሹሞ፣ ዐዞ አያውቅምና ከዚህ አስቀድሞ፤›› በማለት ሙሾአቸውን ሞሽሸዋል፡፡

- Advertisement -

ዐዞ በየኅብረተሰቡ በየቋንቋው በልዩ ልዩ መልክ ይገለጣል፡፡ በብሂል ውስም አይታጣም፡፡ ‹‹ማን ያወጣል ሥጋ ካዞ መንጋጋ›› አንዱ ነው፡፡ የአለቃ ደስታ ተክለ ወልድ፣ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት (1962)፣ ዐዞን የባህር አውሬ ሆደ መጋዝ፣ ጋድሚያ እንቅልፋም ያገኘውን ሰውና እንስሳ በጅራቱ እየጠለፈ ወደ ባሕር ውስጥ የሚገባ ብሎ ይፈታዋል፡፡ እንስቲቱ ባሸዋ ውስጥ ዕንቁላል ትወልዳለች፤ ከዚያም ገላግልት (ግልገሎች) ይወጣሉ ሲልም ያክላል፡፡

ስለዐዞ መንጋጋ ንቁ መጽሔት ካመታት በፊት አንድን ተመራማሪ ጠቅሶ እንደገለጸው፣ የዐዞ መንጋጋ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ ከሚኖሩ አራዊት ሁሉ ይበልጥ ከፍተኛ የመቀርጠፍ ኃይል አለው። ለምሳሌ ያህል፣ አውስትራሊያ አቅራቢያ በጨዋማ ውኃ ውስጥ የሚኖረው ዐዞ የመንከስ ኃይሉ ከአንበሳ ወይም ከነብር ጋር ሲወዳደር ሦስት እጥፍ ያህል ከፍ ያለ ነው። በጣም የሚያስገርመው ግን የዐዞ መንጋጋ ትንሽ ነገር እንኳ ሲነካው የሚሰማው ወዲያውኑ ነው፤ ሌላው ቀርቶ ከጣታችን ጫፍ ይበልጥ ቶሎ ይሰማዋል። ዐዞ እንደ ቅርፊት ያለ እጅግ ጠንካራ ቆዳ ያለው ከመሆኑ አንፃር ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ጄደብሊው ዶት ኦርግ በድረ ገጹ እንደጻፈው፣ የዐዞ መንጋጋ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የስሜት ሕዋሳት አሉት። ዳንከን ሊች የተባሉ ተመራማሪ በዚህ ላይ ጥናት ካደረጉ በኋላ ‹‹እያንዳንዱ የነርቭ ጫፍ የሚወጣው በጭንቅላቱ ውስጥ ከሚገኝ ቀዳዳ›› እንደሆነ አስተውለዋል። በመንጋጋው ውስጥ ያሉት ነርቮች በዚህ መንገድ መቀመጣቸው ምንም ነገር እንዳይጎዳቸው የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ የነርቭ ሴሎቹ አንድ ነገር ሲነካቸው ቶሎ እንዲሰማቸው ያስችላል፤ እንዲያውም በመንጋጋው ላይ ያሉ አንዳንድ ነርቮች አንድ ነገር ሲነካቸው የሚሰጡት ምላሽ በጣም ፈጣን ከመሆኑ የተነሳ በመሣሪያ እንኳ መለካት አይቻልም። በዚህም የተነሳ ዐዞ አፉ ውስጥ ያለ አንድ ነገር ምግብ ይሁን አይሁን በቀላሉ መለየት ይችላል። ይህም አንዲት ዐዞ ጫጩቶቿን በአፏ ይዛ ስትሄድ ተሳስታ እንኳ እንዳትጨፈልቃቸው ይረዳታል። የሚያስገርመው፣ የዐዞ መንጋጋ እጅግ ኃይለኛ የመቀርጠፍ ብቃትና ትንሽ ነገር ሲነካው ቶሎ የመለየት ችሎታን አጣምሮ መያዙ ነው።

  • ሔኖክ መደብር

 

 

- Advertisement -

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን

ከ ተመሳሳይ አምዶች

ባለ ጥምዝ ቀንዱ አምባራይሌ

አምባራይሌ አጠቃላይ ቁመናው ከቀንዱ ጥምዝ ጋር የአጋዘን ይመስላል፡፡ በመጠኑ ግን አነሰ ያለ ነው፡፡ የወንዱ ክብደት ከ92 እስከ 108 ኪሎ ግራም፤ የሴቶቹ ደግሞ ከ56 እስከ 70 ኪግ ይሆናል፡፡

የአሳ ነባሪ ሆድ ዕቃ

ከአሳ ነባሪ ሆድ ዕቃ የሚወጣ የስብ ክምችት የመሰለ ነገር አምበርጊስ ይባላል፡፡ አምበርጊስ ከእንስሳው የሚወጣው በቀጥታ በሚመገበው ምግብ ምክንያት ሲሆን በተጨማሪም የእንስሳው መታመም ምልክትም ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ጎሪላ

በመጠን ትልቁ ኤፕ ጎሪላ ነው፡፡ ጎሪላ ከሁሉም የፕራይሜት ቡድኖች በመጠኑ ይልቃል፡፡ ከ4-8 የሚሆኑ ጠንካራ ሰዎችን ያህል ጥንካሬ አለው፡፡ ጎሪላዎች እጃቸው ረጅምና ከእግራቸው በላቀ ሁኔታ ጡንቻማ ነው፡፡

ጀርባ ጥቁር ቀበሮ

ጀርባ ጥቁር ቀበሮ (Black-backed Jackal) በብዙ የኢትዮጵያ ሥፍራዎች ይገኛል፡፡ ከታንዛኒያ እስከ ቀይ ባሕር፣ እንዲሁም በሶማሊያ ይገኛል፡፡ በተረፈ በብዙ ሌሎች የአፍሪካ ሥፍራዎች ባይገኝም በደቡባዊ አፍሪካ በሚገኙ አገሮች ይኖራል፡፡

እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው እንቁራሪት

እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው የአውስትራሊያ የእንቁራሪት ዝርያ (ጋስትሪክ ብሩዲንግ ፍሮግ) ያልተለመደ ዓይነት የመራቢያ ሥርዓት አላት፤ የዚህች እንቁራሪት ዝርያ ከ2002 ጀምሮ እንደጠፋ ይታሰባል የሚለው ጄደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ ነው።

እንሽላሊቱ ኮሞዶ ድራጐን

ኮሞዶ ድራጐን የእንሽላሊት ዝርያ ነው፡፡ ከእንሽላሊት ዝርያዎች በትልቅነቱ የሚታወቀው ኮሞዶ፣ በማዕከላዊ ኢንዶኔዥያ ኮሞዶ ደሴት ላይ በብዛት ይኖራል፡፡ አንዱ ኮሞዶ ድራጐን እስከ 70 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን፣ ርዝመቱም ከሁለት እስክ ሦስት ሜትር ይደርሳል፡፡ መጋዝ የመሰሉ 60 ጥርሶች አሉት፡፡ ጥርሶቹ በተደጋጋሚ እየወለቁ የሚበቅሉም ናቸው፡፡

አዳዲስ ጽሁፎች

የቤተሰብ ኃላፊነት የተሸከሙ ሕፃናት

በመማሪያና በለጋ ዕድሜያቸው የቤተሰብ ኃላፊነት ተጭኖባቸው ከትምህርት ገበታ ርቀው የሚቀሩ ሕፃናት በርካታ ናቸው፡፡ በቤተሰብ መበተን፣ ከቀዬ በመፈናቀልና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሕፃናትና ታዳጊዎች ሲለምኑ፣ ሶፍትና...

አሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት ትንቅንቅ ማብቂያው መቼ ይሆን?

በናኦድ አባተ በአውሮፓውያን ዘንድ በስፋት የሚታወቀው “A House Divided Against Itself Cannot Stand.” (እርስ በርሱ የተከፋፈለ ቤት አይቆምም) አባባል ትልቅ መልዕክት አለው፡፡ ኢትዮጵያውያንም በታሪክ አጋጣሚ...

መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ላይ ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል!

በአገር ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከሚጠይቁ ገቢ ምርቶች መካከል ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ አገሪቱ ከምታገኘው አነስተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ከግማሽ በላይ የሚሆነው...

‹‹አስከፊ አደጋ ሊደርስ የሚችለው የመሬት መንቀጥቀጡ ልኬት ስለጨመረ ብቻ አይደለም›› አታላይ አየለ (ፕሮፌሰር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ተመራማሪና...

የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም የርዕደ መሬት ክስተት በበርካታ አገሮች የከፋ አደጋ አድርሷል፡፡ ለአብነት ያህል እ.ኤ.አ. በ2005 በፓኪስታን 75 ሺሕ ስዎች፣ እ.ኤ.አ. በ2008 በቻይና 69 ሺሕ...

ስለመነጋገር እስኪ እንነጋገር

በገነት ዓለሙ ዴሞክራሲ መብቶችና ነፃነቶች የሚሠሩበት የሕዝብ አስተዳደር ነው፡፡ ሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነቶችን መኗኗሪያ ያደረገ ሥርዓት ነው፡፡ እነዚህ መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በተፈጥሮ የተገኙ፣ ሰው በመሆናችን ብቻ...

የኑሮ ውድነቱን እያባባሱ ያሉ ዕርምጃዎች ይታሰብባቸው!

መንግሥት የዋጋ ንረቱን ከ30 በመቶ ወደ 16 በመቶ ዝቅ ማድረጉን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አማካይነት በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ገበያው ውስጥ ያለው የምርቶችና አገልግሎቶች ዋጋ የሚያሳየው...
[the_ad id="124766"]

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን