Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት (1923 -1967) የፍርድ ቤት...

የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት (1923 -1967) የፍርድ ቤት ችሎት ገጽታ

ቀን:

የሟች አቤቱታ

አፈር ነው ገለባ 

እላዬ የኖረ

ድንጋይ ነው ቀላሉ

ላዬ የተከመረ

ቀባሪዬ ሁሉ

አዝኖ እያነባ

እያለኝ ይሄዳል

‹‹አፈሩ ይቅለልህ

ያርግልህ ገለባ››

ሰዎች በላዬ ላይ

የከመሩት አፈር

የድንጋዩ ቁልል

ይውጣስ ብባል እኔ

መች ያስወጣኝና

በምፅአት ቀኔ፡፡

አንዱዓለም ጌታቸው ፈለቀ ‹‹ዮሬካ›› (2008)

*********

የቻይናን ‹‹የዶሮ ዓመት›› ያደመቀው ትራምፕ መሳዩ የዶሮ ሐውልት

ቻይናውያን ከወር በኋላ የሚቀበሉትን የዶሮ ዓመት (Year of Rooster) አስመልክቶ፣ በቻይና በሰሜናዊ ሻንዚ ግዛት በሚገኝ የገበያ ማዕከል ፊት ለፊት የተሠራው የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን የመሰለ የዶሮ ሐውልት የጎብኚዎችን ቀልብ ስቧል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ የዶሮ ዓመት መቃረብን አስመልክቶ በገበያ ማዕከሉ መግቢያ የተሠራው ሐውልት ቀራፂ፣ በትራምፕ የፀጉር ስታይልና ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት በሚያሳዩት የእጅ እንቅስቃሴ መመሰጡን ተናግሯል፡፡

ጥር 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሚውለው የቻይና የጨረቃ አዲስ ዓመት ቀድሞ የተሠራውን ትራምፕ መሳይ የዶሮ ሐውልት፣ ተመሳሳዩ በትናንሽ ቅርፅ እንዲሠራላቸው የንግድ ማዕከሉ ጎብኚዎች ጠይቀዋል፡፡ ሐውልቱም በጎብኚዎች ዕውቅናን እያተረፈ ነው፡፡

**********

በሜክሲኮ ከአሥር ሺዎች በላይ የታደሙበት ልደት

ሜክሲኳዊው ኢባራ ግራሺያ የ15 ዓመት ልጁን ሩቢ ልደት ለማክበር ‹‹ሁላችሁም ታኅሣሥ 17 በማከብረው የልጄ ልደት፣ ቦላ ጆያ እንድትገኙ እጋብዛለሁ›› የሚል መልዕክት በቪዲዮ ተቀርፆ በፌስቡክ ይለጥፋል፡፡

የሰሜናዊ ሜክሲኮ ነዋሪነቱን በሚያሳየው የካው ቦይ አለባበስ ተውቦ ቪዲዮውን የለቀቀው ግራሺያ፣ ባላሰበውና ባልጠበቀው መልኩ 1.3 ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በልደት በዓሉ እንደሚገኙ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

ኤምኤስኤን እንዳሰፈረው፣ ከሁሉም የዕድሜ ክልል አሥር ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች በልደቱ የታደሙ ሲሆን፣ ከስፍራው የተገኙትም በማኅበራዊ ድረ ገጽ በተለቀቀው ጥሪ መሠረት ነው፡፡

ልደቱ የተጠራው በአካባቢው ለሚኖሩ 800 ሰዎች ቢሆንም፣ ከሜክሲኮ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በአውሮፕላን እንዲሁም በመኪና ከአምስት ሰዓት በላይ በመጓዝ ብዙዎች ታድመዋል፡፡ አየር መንገዶችም የታሪፍ ቅናሽ አድርገዋል፡፡

ያልታሰበ የሰው መጨናነቅ በፈጠረው የልደት በዓል የፖሊስ አባላትና የእሳት አደጋ ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ሩቢም በቀይ ምንጣፍ እንድትሄድ፣ የበርካታ መገናኛ ብዙኃንን ቀልብ እንድትስብም ዕድል ፈጥሯል፡፡

በልደት ግብዣው ለታደሙ መጠንና ምግብ የቀረበ ሲሆን፣ ታዋቂ ባንዶችም ተገኝተዋል፡፡ ታዳሚዎችም ሌሊት ሙሉ ሲጨፍሩ አድረዋል፡፡

*********

አደንዛዥ ዕፅን በገና ዛፍ

በደቡብ ምዕራብ እንግሊዝ በሚገኘው ግሉሴስትሪሻየር ግዛት፣ በአደንዛዥ ዕፅ ተክሎች የተዋበ የገና ዛፍ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የገና ዛፉ በተለያዩ ቀለማትና ጌጣጌጦች የተዋበ ሲሆን፣ አብዛኛውም የተሠራው ከማሪዋና ቅጠል ነበር፡፡

ሜትሮ ዩኬ እንደዘገበው፣ ዛፉ በገና ዛፍ ስም ወደሌላ ቦታ ሳይዘዋወር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው፣ ከሌሎች መሰል የገና ዛፎች ለየት ብሎ በመታየቱ ነው፡፡ ዛፉን ለማስዋብ መብራቶች፣ ኳሶችና ሌሎች ጌጣጌጦች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

ከዚህ ቀደምም የኒውፖርት ከተማ አስተዳደር ከተማ ለማስዋብ ባስቀመጣቸው የአበባ መትከያዎች ውስጥ የማሪዋና ተክሎች መገኘታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

***********

ባልጠበቀችው ሁኔታ የውስጥ ሱሪዋ የታየባት የቴሌቪዥን ዜና አንባቢ

በቀጥታ ስርጭት በቴሌቪዥን ዜና የሚያነቡ ጋዜጠኞች ማንበቢያ ስቱዲዩ ከመግባታቸው አስቀድሞ በገጠማቸው ክፉ ነገር፣ በማንበብ ላይ እያሉ ሲረበሹ ማስተዋሉ የተለመደ ነው፡፡ በዜና መሀል ሰዎችን ይቅርታ የሚጠይቁም አሉ፡፡

የጣሊያናዊቷ የቀጥታ ስርጭት ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ የገጠማት ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ሜትሮ ዩኬ እንዳሰፈረው፣ ኮስታንዛ ካላብሬስ ዜና ለማንበብ የገባችበት ስቱዲዮ ጠረጴዛው ከመስተዋት የተሠራ መሆኑን አላገናዘበችም፡፡ በመሆኑም የውስጥ ሱሪ ጭምር ያለውን ጥቁር ቦዲ በአጭር ቀሚስ ለብሳ ዜና ማንበቧን ይዛለች፡፡ ሆኖም ዜናውን ስታነብ ከፈት አድርጋ በዘረጋቻቸው እግሮቿ መሀል ጥቁር የውስጥ ሱሪዋም ይታይ ነበር፡፡

ዜናው እንደተጀመረ ከወገቧ በላይ ብቻ ትታይ የነበረ ቢሆንም፣ ካሜራው እያቀረባት ሲመጣ በመስታወቱ ተላልፎ የሚታየው የውስጥ ሱሪዋ ከዜናው ይልቅ ቀልብ መሳቡን ዘገባው ያሳያል፡፡

ተመልካቾችም ‹‹ካላብሬስ ዛሬ ገና አሪፍ ዜና አቀረበችልን›› ማለታቸውም ተሰምቷል፡፡ ቪዲዮው በዩቲዩብ በሺዎች በሚቆጠሩ መታየቱም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...