Monday, March 20, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበደብረብርሃን ከተማ በግማሽ ቢሊዮን ብር ሪፈራል ሆስፒታል እየተገነባ ነው

በደብረብርሃን ከተማ በግማሽ ቢሊዮን ብር ሪፈራል ሆስፒታል እየተገነባ ነው

ቀን:

በደብረብርሃን ከተማ በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ የሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ በመከናወን ላይ ሲሆን፣ የቀድሞውን ሐኪም ግዛው መታሰቢያ ሆስፒታልን ደግሞ ወደ ሪፈራል ለማሳደግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ አስታወቁ፡፡

ከንቲባው አቶ ታገል አምሳሉ እንደገለጹት፣ የሪፈራል ሆስፒታሉን ግንባታ በባለቤትነት የሚያካሂደው የአማራ ክልል ሲሆን፣ የሐኪም ግዛው ሆስፒታልን ደግሞ ወደ ሪፈራል የሚያሸጋገረው የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡

የግንባታውና የማሸጋገሩ ሥራ ሲጠናቀቅ በደብረብርሃን ከተማ አሁን በአገልግሎት ላይ ያለውን ሪፈራል ሆስፒታል ጨምሮ ቁጥሩን ወደ ሦስት ከፍ እንደሚያደርግ ከንቲባው አስረድተዋል፡፡

ከእነዚህ ጤና ተቋማት በተጨማሪ ሦስት ጤና ጣቢያዎችና አምስት ጤና ኬላዎች ለኅብረተሰቡ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

ቀደም ሲል የተጀመሩት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እየተስፋፋ ሲሆን፣ በከተማ ደረጃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ማስፋፊያና ጽሕፈት ቤትም ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ ታገል፣ በከተማው ወደ 400 የሚጠጉ ኢንቨስትመንቶች ሥራ ላይ ሲሆኑ፣ ከእነዚህም መካከል ከ200 በላይ የሚሆኑት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው፡፡ ከ13ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ወገኖችም የሥራ ዕድል ፈጥረዋል፡፡

በንግድና በአገልግሎት መስኮች ከተሰማሩት መካከል 90 ከመቶ ያህሉ የከተማዋ ነዋሪዎችና የአካባቢው ተወላጆች መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከተማዋ  ለኢንቨስትመንት ምቹ መዳረሻ መሆኗን ከግምት በማስገባት 350 ሜጋዋት ኃይል ማስተላለፍ የሚችል የሰብስቴሽን ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑንና የግንባታውም 70 ከመቶ  መጠናቀቁንም አስረድተዋል፡፡

ደብረብርሃን ከተማ ከተቆረቆረች ከ500 ዓመት በላይ አስቆጥራለች፡፡ ሆኖም የዕድሜዋን ያህል አላደገችም፡፡ በጣሊያን ወረራ ዘመን (1928-1933) በተሠራ ስድስት ሜትር ስፋት ባለው አንድ የአስፋልት መንገድ ብቻ ለዓመታት ስትገለገል ቆይታለች፡፡

በአሁኑ ጊዜ 22 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ የ30 ኪሎ ሜትር የኮብልስቶን፣ ከ36 ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ ጠጠር መንገዶች እንዲሁም የአንድ ዩኒቨርሲቲ፣ የአምስት ኮሌጆች፣ የሦስት ከፍተኛ ሁለተኛና የ26 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባለቤት እንደሆነች ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ዜጎች የተፈተኑበት የኑሮ ውድነት

በኢትዮጵያ በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ዜጎችን አቅም...

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸውና በተቀናጀ መልኩ...

ወደ ኋላ የቀረው የሠራተኞች ደኅንነት አጠባበቅ

በአበበ ፍቅር ለሠራተኞች የሚሰጠው የደኅንነት ትኩረት አናሳ በመሆኑ በርካታ ዜጎች...