Wednesday, February 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ልታፀድቅ ነው

ኢትዮጵያ የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ልታፀድቅ ነው

ቀን:

ኢትዮጵያ የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት እንድታፀድቅ የስምምነት ሰነዱ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 2015 በፈረንሣይ ፓሪስ ከተማ የዓለም አገሮች የደረሱበት አዲስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ፈራሚ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን፣ በአሁኑ ወቅት 194 አገሮች ፈርመውታል፡፡ ይህንን ስምምነት ያፀደቁ አገሮች ደግሞ 118 መድረሳቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የፓሪሱ ስምምነት በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ ላይ አማካይ የሙቀት መጠን ጭማሪን ከሁለት ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በታች በበቂ ሁኔታ እንዲቀንስ፣ በተቻለ መጠን በ1.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መገደብን እንደ መሥፈርትነት አስቀምጧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ምጣኔ ሀብት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገርና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት መንገድን መከተል የሚያበረታታ ነው፡፡

አገሮች የሙቀት አማቂ ጋዞችን የማስተናገድ አቅምን በማጠናከር የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመቆጣጠር የሚረዱ ሥራዎችን፣ ለአብነት ያህልም የደን ልማትን ማጠናከር እንዳለባቸው ያስረዳል፡፡

ታዳጊና ገና በማደግ ላይ ያሉ አገሮች በዚህ ስምምነት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ፣ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ አማካይነት የሚደርስባቸውን ተፅዕኖ ለመቋቋም እንዲያስችላቸው ያደጉና ፈቃደኛ የሆኑ አገሮች የገንዘብ፣ የቴክኖሎጂና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርጉ ግዴታ ያስቀምጣል፡፡

ስምምነቱ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭና ተጠቂ አገሮች ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የስምምነቱ ማፅደቂያ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡

በዚህ የዓለም ሙቀት መጨመር በተደጋጋሚ ከሚጠቁ አገሮች ኢትዮጵያ ቀዳሚዊ መሆኗን፣ ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ እ.ኤ.አ. በ2050 የሚኖረው ዓመታዊ የግብርና ምርት መጠን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ማብራሪያው ይጠቁማል፡፡

ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባቀረበችው ሰነድ መሠረት እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2030 ድረስ የሙቀት አማቂ ጋዞችን በ64 በመቶ ለመቀነስ መስማማቷ ይታወሳል፡፡ ፓርላማው ስምምነቱን ለዝርዝር ዕይታ መርቶታል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ፓርላማው የሰብዓዊ ድርጊት መርሐ ግብር ሰነድን በሙሉ ድምፅ ማክሰኞ ታኅሳስ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. አፅድቆታል፡፡

በሰነዱ ላይ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል የሰብዓዊ ድርጊት መርሐ ግብር ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አፈጻጸሙን በተመለከተ በየዓመቱ ለፓርላማው ሪፖርት እንዲያቀርብ፣ እንዲሁም በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ አፈጻጸሙን የሚከታተልና ሪፖርት የሚያደርግ እንዲመደብ ያደርጋል፡፡      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጥቁር የመልበስ ውዝግብና የእምነት ነፃነት በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኅዳር ወር ላይ በፓርላማ...

የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጠጠር ገለልተኛ ተቋም ለመመሥረት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከ70 በላይ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊቀላቀሉ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

እስቲ አንገፋፋ!

እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስንነት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው...