Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኦሕዴድ ባለሥልጣናትን ለመግደል አሲረዋል የተባሉ ተከሰሱ

የኦሕዴድ ባለሥልጣናትን ለመግደል አሲረዋል የተባሉ ተከሰሱ

ቀን:

በአምቦ ከተማ በርኩሜ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰቀለን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አውርደው በማቃጠል፣ የኦሕዴድ ባለሥልጣናትን ደግሞ ለመግደል ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ስድስት ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ተከሳሾች ደምሴ ባንቲ፣ ግርማ ለታ፣ ፈረጃ ጌታቸው፣ ደበላ ኃይሌ፣ ተመስገን ኩማና ቤለማ ጉታታ የሚባሉ ናቸው፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል መሆናቸውም በክሱ ተገልጿል፡፡

መንግሥትን በኃይል ትጥቅ ለመጣል ከኦነግ ተልዕኮ በመቀበል ተከሳሾቹ የተንቀሳቀሱት፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ላይ ቦምብ በመወርወር ተረኛ የነበረን የፖሊስ መኮንን ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

የኦሕዴድ ባለሥልጣናትን በመሣሪያ ተኩሰው ለመግደልና ቤታቸውን በቦምብ ለማቃጠል በማሰብ፣ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለይ በምዕራብ ሸዋ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ ከኦነግ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ትምህርት ቤት ወላጆቻቸውን እንዲያመጡ የሚጠየቁትንና በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት የተባረሩ ተማሪዎችን በማግባባት፣ ለሽብር ቡድኑ አባል ለማድረግም ሲሠሩ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡

በአካባቢው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተሰቀለን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አውርዶ ማቃጠል፣ ለተለያዩ የጦር መሣሪያዎችና የእጅ ቦምብ መግዣ፣ ከውጭ አገር ከሚላክላቸው በተጨማሪ ወርኃዊ መዋጮ በማድረግ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበርም በክሱ ተገልጿል፡፡

በአምቦ ከተማ ቀበሌ 02 ውስጥ ቤት በመከራየትና የተለያዩ ስብሰባዎችን በማድረግ፣ የቡድኑን መጠሪያ ‹‹የጠዋት ፀሐይ ጮራ ነፃነት›› የሚል ስያሜ ከሰጡ በኋላ፣ በየወሩ 20 ብር በማዋጣት ለትጥቅ መግዣ ለማዋል ስምምነት ማድረጋቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

የተለያዩ የሽብር ድርጊቶችን ለመፈጸም የኦነግን ትዕዛዝ በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሞ፣ የኦነግን ዓርማ በመጠቆም ፎቶ ተነስተው በፌስ ቡክ በመለጠፍ፣ ሌሎችንም ለማነሳሳት በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር ውለው የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ እንደተመሠረተባቸው የክስ ሰነዱ ያብራራል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ተከሳሾቹ ከጠበቃ ጋር ተነጋግረው እንዲቀርቡና የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆናቸው፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አስተርጓሚ እንዲልክ ብሏል፡፡ ለመጠባበቅም ለታኅሳስ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...