Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአዲስ አበባ ፈጣን የአውቶብስ መስመር ተጨማሪ ብድር ተገኘ

ለአዲስ አበባ ፈጣን የአውቶብስ መስመር ተጨማሪ ብድር ተገኘ

ቀን:

ለአዲስ አበባ ፈጣን የባቡር መስመር ግንባታና አውቶብሶችን ለማስገባት ተጨማሪ 35 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ከፈረንሣይ መንግሥት ተገኘ፡፡

ከፈረንሣይ የልማት ኤጀንሲ 50 ሚሊዮን ዩሮ ባለፈው ዓመት ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ ተጨማሪ የ35 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ስምምነት እንዲፀድቅ ለፓርላማ ቀርቧል፡፡

ፈጣን የአውቶብስ መስመር ግንባታ በዊንጌት-ጎፋ ገብርኤል አድርጎ እስከ ጀሞ የሚዘልቅ ነው፡፡

ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው ወጪ 101.6 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡ ከፈረንሣይ የተገኙ ሁለቱ ብድሮች 85 ሚሊዮን ዩሮ የሚሆነውን ወጪ ይሸፍናሉ፡፡ የተቀረው 16.6 ሚሊዮን ዩሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚሸፈን የብድር ስምምነቱ ያመለክታል፡፡

ይህ ፕሮጀክት የከተማዋን ነዋሪዎች የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ እንደሚያስችል፣ መንግሥት ከሚያከናውናቸው የባቡርና የመደበኛ አውቶብስ በተጨማሪ በቀጣይ የሚከናወን እንዲሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፓርላማው የብድር ስምምነቱን በዝርዝር ተመልክቶ የውሳኔ ሐሳብ እንዲያቀርብለት ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...