Sunday, January 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅዳንኪራው

ዳንኪራው

ቀን:

ሐረር ባስተናገደችው 11ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል፣ ከተገኙት ታዳሚዎች ውስጥ ከደቡብ ኦሞ ዞን የመጣችው ወ/ሮ ዙፋን (በቀኝ) ትገኝበታለች፡፡ በመድረኩ የአሪ ብሔረሰብ ዳንኪራን ስታሳያቸው ሌሎችም አጅበዋታል፡፡ (ፎቶ በታምራት ጌታቸው)

********

ያ ቀን ….

በመስታወት አምሮ – በቀለማት ደምቆ

በቅርፅ አሠራሩ – አንዱ ካንዱ ልቆ

መስህብ የሆነው – ሲታይ አሸብርቆ፤

እንደ ጦር ቀጣና – ከቀውጢው ወረዳ

ጥይት ሳይተኮስ – ፈንጅው ሳይፈነዳ

የስንቱ ደም ፈሶ – ስንቱ አካሉ ጎሎ

ህልሙ – ከንቱ ሆኖ

ሳይወድ ለምፅዋት – በየቀዬው ውሎ

በቁሙ ታፍኖ – በቁሙ ተቀብሮ

የለት ጉርሱን ብሎ – ዳግም የማትገኝ

ሕይወቱን – ገብሮ፡፡

ባለኮከብ ቢባል – ሰማይ ጠቀስ ሕንፃው

ከተማ – የቆመው

ሻምፓኙ – ተከፍቶ

ሪቫኑ ተቆርጦ – ምርቃት የበቃው

ደቂቅ ለማትሞላ – ለህሊና ፀሎት

ስሙ – በተረሳው

በዛ ጭቁን – ሰው ነው

ያ ቀን – በከዳው

በቀን – ሠራተኛው

ደምሳሽ አስፋው – ከካዛንችስ

መታሰቢያነቱ – በግንባታ ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ የቀን ሠራተኞች ይሁን!

************

ፀጉሩን ሲቆረጥ በደረሰበት ጉዳት የ90 ሺሕ ፓውንድ ካሳ ያገኘው ሰው

የ45 ዓመቱ እንግሊዛዊ ዘወትር እንደሚያደርገው ወደ አንድ የወንዶች ፀጉር ቤት ጎራ ይልና ፀጉሩን መቆረጥ ይጀምራል፡፡ ድንገት የደም ስሩ የተነካው የ45 ዓመቱ ዴቭ ታይለር ለሁለት ተከታታይ ቀናት አገር አማን ብሎ የሥራ ስብሰባ ከተካፈለ በኋላ ድንገት በስትሮክ መያዙን ዘ ታይምስና ሜል ዘግበዋል፡፡ ታይለርን ያዩት ዶክተሮች እንዳስረዱት ፀጉሩን ሲቆረጥ በተጎዳው ደም ስሩ ምክንያት የደም ዝውውሩ ላይ ችግር ተፈጥሯል፡፡ በዚህም ታይለር ድንገት ራሱን ስቶ ወድቋል፡፡ ሦስት ወራትን ሆስፒታል ያሳለፈው ታይለር በመጨረሻ ለጉዳት በዳረገው የውበት ሳሎን የ90 ሺሕ ፓውንድ ካሳ ተከፍሎታል፡፡ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ አጋጣሚዎች መፈጠራቸውን ያስታወሰው ዘገባው እ.ኤ.አ. 2014 ላይ የሁለት ልጆች እናት አሜሪካ ውስጥ ፀጉሯን ስትሠራ በደረሰባት ጉዳት ለስትሮክ መጋለጧን ይጠቅሳል፡፡

********

ያሁ የ500 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን መረጃ ተሰረቅኩ አለ

ከጥቂት ወራት በፊት የተጠቃሚዎችን መረጃ መሰረቁን ያስታወቀው ያሁ፣ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ ደግሞ የ500 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች መረጃ እንደተሰረቀበት (ሀክ እንደተደረገበት) ገልጿል፡፡ ኩባንያው እንዳስታወቀው ሁለተኛው ከመጀመሪያው የባሰ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ኩባንያው እንደሚለው የተጠቃሚዎቹ መረጃ የተሰረቀው እ.ኤ.አ. 2013 ላይ ነው፡፡ ‹‹ይህኛው የመረጃ ስርቆት ከቀደመው በጣም የተለየ ነው፤›› ያለው ኩባንያው በኋለኛው የሀከሮች ጥቃት የተሰረቀው የበርካቶች መረጃ መሆኑንም ጨምሮ ጠቅሷል፡፡ ይህ ጥቃት ያሁ እያደረገ ያለውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ በተለይም አሁን ላይ ያቀደውን ዕርምጃ በእጅጉ እንደሚጎዳው እየተገለጸ ነው፡፡ በ1990ዎቹ ብዙዎች የሚጎበኙት ድረ ገጽና ቀዳሚ የኢንተርኔት መዳረሻ ነበር፡፡

*********

የዓለም ውድ የቤት እንስሶች

እንግሊዝ የእንስሳት አፍቃሪዎች አገር ነች ይባላል፡፡ ለዚህ በማበብ ላይ ያለው የቤት እንስሳት ገበያ ምስክር ሊሆን ይችላል የሚለው ሚረር ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ በቤት እንስሳት ንግድ ኢንዱስትሪ በዓመት አምስት ቢሊዮን ፓውንድ ወጭ ይሆናል፡፡ እንግሊዛውያኑም ለቤት እንስሳት ያለን ፍቅር ካለፉት ሺሕ ዓመታት ጀምሮ የዘለቀ ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ የቤት እንስሳት ኤክስፐርትና ምግብ አቅራቢው ግሪን ፓንትሪ መሥራች የሆኑት ሲሞን ቡዝ የዓለም አምስቱን ውድ የቤት እንስሳት ይዘረዝራሉ፡፡ የእነዚህ እንስሳት ዋጋ ውድ የተባለ ቤት ወይም መኪናን ዋጋ ያስንቃልም ተብሏል፡፡ ከእነዚህ መካከል በጣም ሀብታሞች የሚጋልቡትና በ16 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ የተሸጠው አንደኛው ውድ ፈረስ ነው፡፡ ከእስያ ውሾች ትልቁ የሆነው የቲቤቱ ውሻ የተሸጠው በ1.14 ሚሊዮን ሲሆን፣ ሁለተኛው ውድ የቤት እንስሳ እሱ ነው፡፡ ሦስተኛዋ ደግሞ 1.2 ሚሊዮን ዶላር በካናዳውያን ባለሀብቶች የተገዛችው ሚሱ የተሰኘችው ላም ነች፡፡ እስከ 850 ፓውንድ የሚያወጣው የእንግሊዙ ውሻ በአራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ በደቡብ አፍሪካ ብቻ የሚገኘው ነጭ አንበሳ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...