Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልምን የት?

ምን የት?

ቀን:

‹‹ሆሄ›› የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ተዘጋጀ

የንባብ ባህልን ለማጎልበትና ንባብና መጻሕፍት የመወያያ አጀንዳ እንዲሆኑ የሚያስችል የሥነ ጽሑፍ ዓመታዊ ሽልማት ፕሮግራም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ክፍለ ትምህርትና በኖርዝ ኢስት ኤቨንስት በጋራ ተዘጋጀ፡፡

‹‹ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት›› የሚል መጠሪያ ያለው ተቋም የሽልማት ዝግጅቱን ከዘንድሮ ጀምሮ በዓመቱ ሲያካሂድ፣ የሥነ ጽሑፍ ሥራ ያበረከቱ ጸሐፍትን አወዳድሮ ከመሸለም ባለፈ በሥነ ጽሑፍ፣ በንባብ እንዲሁም በትምህርት የላቀ ድርሻ የተወጡ ግለሰቦችን ዕውቅና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

 ኖርዝ ኢስት ኤቨንስትስ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ የንባብ ባህልን ከማዳበር አኳያም ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በዓመቱ ውስጥ ከሥነ ጽሑፍ ሽልማቱ በተጓዳኝ የሚዘጋጁ ስድስት የውይይት መድረኮች፣ ሁነቶችና የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ይኖሩበታል፡፡

******

‹‹ሜክሲኮ ቡናና ሻይ››

      በዳንኤል ቢሠጥ እቴቴ የተሰናዳው ‹‹ሜክሲኮ ቡናና ሻይ›› መጽሐፍ መሰንበቻውን ለኅትመት በቃ፡፡ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማጠንጠኛቸውን ያደረጉ ወጎች የያዘው መጽሐፉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኝና ለአዲስ አበባ ከተማ እንግዳ የሆነ ወጣት የሚገጥሙትን ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ፈተናዎች በስላቅ በግነትና በሽሙጥ አዋዝቶ ይተርካል፡፡ ዋጋውም 65 ብር ነው፡፡ ጋዜጠኛ ዳንኤል ከዚህ ቀደም ‹‹አፈር ብላ›› ያለው የግጥም መድበልና ‹‹የታች ሠፈር ቀልዶች›› የተሰኘ የቀልዶች ስብስብ አሳትሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...