Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ተሰየመ

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ተሰየመ

ቀን:

– አዲሱ ተሿሚ በጡረታ ላይ የነበሩት የቀድሞ የልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ በመሆን ሲያገለግሉ በነበሩት በአቶ ጌታሁን ናና ምትክ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጥሩነህ ሚጣፋ ተሾሙ፡፡

አቶ ጌታሁን ናና ያልተጠበቀ ነው በተባለው ሹመት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሾሙ በኋላ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥነቱን ማን ይረከበው ይሆን? የሚለው በጉጉት ሲጠበቅ ቆይቶ፣ ሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ግን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ሹመት ከመንግሥት መገኘቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

አቶ ጥሩነህ ሚጣፋ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥነትን ሹመት ከማግኘታቸው በፊት፣ ለምክትል ገዥነቱ ሥልጣን ከብሔራዊ ባንክ በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ከነበሩ ባለሙያዎች ሊመደቡ ይችላሉ የሚል ግምት ነበር፡፡ ከዚህ በተለየ ምልከታ መንግሥት በጡረታ ተገልለው የነበሩትን የቀድሞ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትንና የብሔራዊ ባንክ የቀድሞ ባልደረባን ምርጫው አድርጓል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ራሱን የቻለ የማስተዳደር ሥልጣን ያለውና ተጠሪነቱ በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑን ማቋቋሚያ አዋጁ ይገልጻል፡፡

አቶ ጥሩነህ የልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው እስከተሰየሙ ድረስ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊ በመሆን ሠርተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

አሁን የተሾሙበት የኃላፊነት ቦታ በተለይ የአገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለበት ሲሆን፣ አቶ ጌታሁን ናና የሚመሩትን ልማት ባንክና ቀሪዎቹን የአገሪቱን ባንኮች በበላይነት የመቆጣጠር ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አዲሱ ተሿሚ በኢትዮጵያ የባንክ ኢዱስትሪ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ናቸው ተብሏል፡፡

አቶ ጥሩነህ በብሔዊ ባንክ ውስጥ ረዥም ጊዜ ካገለገሉና ጠንካራ ከሚባሉ ባለሙያዎች መካከል አንዱ እንደነበሩ፣ በቅርብ የሚያውቋቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቅርንጫፎች ማስተባበር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለአራት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ፣ በመስከረም 2009 ዓ.ም. ጡረታ መውጣታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ፣ አቶ ጥሩነህ ኅዳር 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ከብሔራዊ ባንክ የተለያዩ ኃላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

አቶ ጌታሁን ወደ ልማት ባንክ በፕሬዚዳንትነት እንዲሄዱ የተደረገው፣ የልማት ባንክን በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ኢሳያስ ባህረ ከኃላፊነት እንዲነሱ በመደረጉ ነው፡፡

አቶ ጌታሁን የልማት ባንክ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ከያዙ በኋላም የቀድሞው የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለ ኢየሱስ በቀለ የልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትና አማካሪ በመሆን መሰየማቸው ይታወሳል፡፡ ይኼም ሹመት የልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ቁጥር ስድስት እንዳደረሰው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...