የቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር የአሁኑ የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ፣ ለ‹‹ዘመን›› መጽሔት ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መጽሔቱ ለኃላፊው ካቀረበላቸው ጥያቄዎች አንዱ ለሆነው፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ድጋፍ እየሰጡ በአዲስ አበባና በክልል የተሠሩ መኖሪያ ቤቶች ሕገወጥ ብለው እንዲፈርሱ ያደረጉትን ኃላፊዎች ይዞ፣ መልካም አስተዳደርን ማምጣት ይቻላል ወይ? ለሚለው የሰጡት ዘይቤያዊ ምላሽ ነው፡፡ ቤቱን ያስፈረሰ ብቻ ሳይሆን ሥርዓቱን ሲመራ የነበረውን ኃይል ጨምሮ ሁሉ በየደረጃው ተጠያቂና ተሳታፊ የነበረ ሁሉ ለሕግ የሚቀርብበት ሥርዓት መኖር እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹ዋናው ጉዳይ ግን እነርሱን አሁን ከላይ ብናጠፋቸው ፍልፈል ላይ እንደሚተከል ችግኝ ነው የሚሆነው፤ ለዚህ መድኃኒቱ የሚሆነው ፍልፈሉን ማውጣት ነው፤›› ብለዋል፡፡