Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየአልኮል የካንሠር መንስኤነት እየጨመረ እንደሆነ በጥናት ተጠቆመ

የአልኮል የካንሠር መንስኤነት እየጨመረ እንደሆነ በጥናት ተጠቆመ

ቀን:

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በፓሪስ የካንሠር ኮንግረስ ላይ የቀረበ መረጃ እንደሚያሳየው አልኮል ተጠቃሚነት በተለይም በባለፀጋ አገሮች እ.ኤ.አ. 2012 ላይ ለ700,000 ለአዲስ የካንሠር ኬዞች፤ ለ366,000 የካንሠር ሞቶች ምክንያት ሆኗል፡፡ አልኮል የሚጠጡና የማይጠጡ ሰዎችን የካንሠር ተጋላጭነት ያጠኑት ተመራማሪዎች አልኮል በየዓመቱ በአምስት በመቶ በካንሠር ለመያዝ እንዲሁም ለ4.5 በመቶ የካንሠር ሞቶች ምክንያት እየሆነ ነው፡፡

ይህ ጥናት ገና አለመታተሙን ለአጃንስ ፍራንስ ፔሬስ የገለጹት የካንሠር ምርምር ኤጀንሲው ኬቨን ሺልድ ‹‹በርካቶች አልኮል ለካንሠር መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ የላቸውም›› ብለዋል፡፡ እሳቸው እንደሚሉት የአልኮል ውሱድ መጠን በተለይም ከጡት ካንሠር ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አለው፡፡

ከካንሠር ጋር በተያያዘ የአልኮልን ተፅዕኖ የመዘኑት ተመራማሪዎቹ አልኮል በተለይም ለኢሶፋገስ ከዚያም ኮሎሬክታል ካንሠር መንስኤ እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ኤጀንሲ የሆነው ዓለም አቀፉ የካንሠር ምርምር ተቋም አልኮልን በ‹‹ግሩፕ 1›› ካርሲኖ ጂን፣ ማለትም ካንሠርን ከሚያስከትሉ ነገሮች ጋር ይመድበዋል፡፡ ቢሆንም ግን እንደ ሺልድ ያሉ ተመራማሪዎች በምን መልኩ አልኮል የካንሠር መንስኤ ይሆናል የሚለው በግልጽ እንደማይታወቅ ይናገራሉ፡፡

- Advertisement -

ከካንሠር ጋር በተያያዘ የአልኮል ተፅዕኖ በሰሜን አሜሪካ፣ አውስትራሊያና አውሮፓ (በተለይም ምሥራቁ) ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ነገሮች እየተቀየሩ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ተፅዕኖው እየበረታ መሆኑ በተመራማሪዎቹ ተገልጿል፡፡

ካንሠር ከቁጥጥር ውጭ የሆነን የሕዋስ ዕድገትና መስፋፋት ሲሆን፣ ማንኛውንም የሰውነት ክፍል ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ብዙዎቹ የካንሠር ዓይነቶች ለካንሠር መንስኤ ይሆናሉ ከተባሉ እንደ ቶባኮ ካሉ ነገሮች በመጠበቅ ሊከላከሏቸው የሚቻል እንደሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም ብዙዎቹ የካንሠር ዓይነቶች በተለይም በጊዜ ከተደረሰባቸው በቀዶ ሕክምና፣ በሬዲዮ ወይም ኬሞቴራፒ ሊድኑ እንደሚችሉ ይገልጻል፡፡

ካንሠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች ቀዳሚው ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. 2012 ላይ 14 ሚሊዮን ሰዎች በካንሠር ሲያዙ 8.2 ሚሊዮኖች ደግሞ በካንሠር ሕይወታቸውን እንዳጡ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡ በዓመት 60 በመቶ የሚሆኑ አዳዲስ የካንሠር ኬዞች የሚመዘገቡት በአፍሪካ፣ እስያና መካከለኛና ደቡባዊ አሜሪካ ነው፡፡ እነዚህ የዓለም አካባቢዎች ከዓለም የካንሠር ሞት 70 በመቶ የሚሆነው የሚመዘገብባቸውም ናቸው፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...