Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኅዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በሐረሪ ክልል አስተናጋጅነት በሐረር...

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኅዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በሐረሪ ክልል አስተናጋጅነት በሐረር ከተማ ሲከበር ከነበሩት ትርዒቶችና እንግዶች መካከል

ቀን:

ኧረ በፈጠረሽ!

ንግግር አብቅቼ አፌን ተለጉሜ

ንግግር አብቅተሽ አልናገር ብለሽ

ስለተኮራረፍን

ፀሐይ ተሰበረች አላበራም ብላ

ጨረቃም ጠፋችው ደንግጣ ኮብልላ

ዳግም ዳቦ ላትጥል ተፈጥማ ምላ፡፡

እኔና አንቺ ብቻ አለነው ከዚሁ

አኩርፈሽ አኩርፌ

ኩርፍርፍ ብለን

ፍጥረት እስኪደንቀው የእኛ እንደዚህ መሆን፡፡

ኧረ በፈጠረሽ!

አን..ዴ ሣቅ በይና

ፀሐይ ብልጭ ትበል

ሕይወት ትስረፅና!::

———-

1965 ዓ.ም.

ዮናስ አድማሱ፣ ‹‹ጉራማይሌ››፤ (2006)

* * *

በጋና ሐሰተኛው የአሜሪካ ኤምባሲ ከአሥር ዓመት በኋላ ተዘጋ

ጋና አክራ ውስጥ የአሜሪካን ሰንደቅ እያውለበለበና የፕሬዚዳንት ኦባማን ፎቶግራግ ሰቅሎ ለአሥር ዓመት ሲሠራ የቆየው ሐሰተኛ የአሜሪካ ኤምባሲ ባለፈው ሳምንት መዘጋቱን ሲኤንኤንና ቢቢሲ ዘግበዋል፡፡ ይህ ለአሥርት ሐሰተኛ ቪዛዎችንና ሌሎችንም ሰነዶች ሲሰጥ የኖረው ኤምባሲ ኃላፊዎች ወንጀለኛ የጋና ባለሥልጣናትና የቱርክ ሕገወጦች መሆናቸው በዘገባው ተመልክቷል፡፡ ይህ ሐሰተኛ ኤምባሲ በሰጣቸው ሐሰተኛ ሰነዶች ምን ያህል ሰዎች ወደ አሜሪካ እንደገቡ ማወቅ አልተቻለም፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኤምባሲው ሐሰተኛ ቪዛዎችን ብቻም ሳይሆን በዘረጋው የወንጀለኞች ሰንሰለት አማካይነት ትክክለኛዎቹንም ያገኝ ነበር፡፡ ኤምባሲው በተበረበረበት ወቅት 150 የሚሆኑ ፓስፖርቶችና መታወቂያዎች ተገኝተዋል፡፡ የተገኙት ቪዛዎችና ፓስፖርቶች ከተለያዩ አሥር አገሮች የተገኙ ናቸው፡፡ በጋና አክራ ተመሳሳይ ሐሰተኛ የኔዘርላንድ ኤምባሲም ተገኝቷል፡፡

*******

ውሾቿን አትክልት በሊታ ያደረገች

የ41 ዓመቷ ፓውላ ላውስ ለውሾቿ አትክልት፣ ስኳርድንች፣ ፍራፍሬ፣ ቅመማ ቅመምና እፅዋት ብቻ በመመገብ የራሷን የአመጋገብ ሥርዓት እንዲከተሉ አድርጋለች፡፡

ሜትሮ ዩኬ እንደዘገበው፣ ፓውላ ሥጋና የእንስሳት ውጤቶችን ለራሷ መመገብ አቁማ ወደ አትክልቱ ፊቷን ብታዞርም፣ ለውሾቿ ሥጋ ትመግብ ነበር፡፡ ሆኖም እሷ አትክልት ውሾቿ ደግሞ ሥጋ እየበሉ አብረው መቀጠል ስለማይችሉ፣ ለውሾቹ የሚስማማ አትክልት ነክ ምግብ ላይ ጥናት በማድረግ፣ ውሾቿንም አትክልት በሊታ አድርጋቸዋለች፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...