Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጨው ዋጋና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መንግሥት ውሳኔ አሳለፈ

በጨው ዋጋና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መንግሥት ውሳኔ አሳለፈ

ቀን:

– በፋብሪካ የማምረት ሥራው ለአንድ ድርጅት ተሰጥቷል

የጥሬ ጨው አምራቾችን፣ አዮዲን ያለው ጨው አቀነባባሪ ፋብሪካዎችን፣ የጅምላ አከፋፋዮችንና በቸርቻሪዎች ለተጠቃሚዎች የሚደርስበት ዋጋና ተያያዥ ጉዳዮች በሚመለከት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ዓርብ ኀዳር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

በንግድ ሚኒስትሩ ዶ/ር በቀለ ቡላዶ ተፈርሞ የወጣው የውሳኔ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ጨው መሠረታዊ ሸቀጥ በመሆኑ በ2005 ዓ.ም. አዮዲን የተቀላቀለበት ጨውና አዮዲን የሌለውን ጨው አምራቾች በኩንታል የሚሸጡበት ዋጋ ተወስኖ ሲሠራበት ቆይቷል፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት የጨው ማምረቻ መሣሪያ ግዢ፣ የሠራተኛ ደመወዝ፣ የጥገናና ሌሎች ግብዓቶችን መሠረት አድርጎ ከአምራቹ ተደጋጋሚ ቅሬታ በመቅረቡ የዋጋ ማሻሻያ መደረጉ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በመሆኑም ጥሬ ጨው አምራቾች አዮዲን ያልተጨመረበትን ጥሬ ጨው፣ ለፋብሪካዎች ብቻ ተጨማሪ እሴትና ኤክሳይዝ ታክስን ጨምሮ በኩንታል 257.95 ብር እንዲሸጡ መወሰኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ፋብሪካዎቹ በማጠብና በአዮዲን በማበልፀግ ለጅምላ አከፋፋዮች ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በኩንታል 529.68 ብር ይሸጣሉ፡፡ ጅምላ አከፋፋዮቹ ደግሞ ከፋብሪካው ብቻ የገዙትን ለቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለባቸውን ወጪዎች፣ ቫትና የትርፍ ህዳግ አራት በመቶ ይዘው እንዲሸጡ መወሰኑን ዶ/ር በቀለ በደብዳቤው ገልጸዋል፡፡

ቸርቻሪ ነጋዴዎች ለተጠቃሚ የሚሸጡበት ዋጋ ከጅምላ አከፋፋይ በገዙበት ዋጋ ላይ የሚያወጡትን ወጪ ጨምረውና ስድስት በመቶ የትርፍ ህዳግ ይዘው እንዲሸጡ መወሰኑንም አክለዋል፡፡

የታጠበ ጥሬ ጨው በግብዓትነት ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ብቻ፣ ከፋብሪካ የመግዢያ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምረው በኩንታል 455.05 ብር እንዲሸጡ መደረጉን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

አዮዲን ያለውን ጨው በተለያየ መጠን በማሸግ ለገበያ የሚያቀርቡ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች፣ ያለባቸውን ወጪ ጨምረውና አምስት በመቶ የትርፍ ህዳግ ይዘው እንዲሸጡ ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በንግድ ሕጉ የተቀመጠውን የገበያ ሰንሰለት በጠበቀ መንገድ የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መቆጣጠር እንዳለበትም ማሳሰቢያ እንደተሰጠው የሚኒስትሩ ደብዳቤ ያሳያል፡፡ ማንኛውም ሰው በሚያመርተው ወይም በሚያከፋፍለው የምግብ ጨው ውስጥ፣ አዮዲን እንዲኖረው አስገዳጅ ደንብ መውጣቱንም ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

አዋጁንና ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግ ጥሬ ጨው በዘመናዊ ፋብሪካ ተቀነባብሮ ለምግብ ጨው የወጣውን አስገዳጅ የደረጃ ምልክት በመያዝ ብቻ ወደ ገበያ መቅረብ እንዳለበት፣ የተላለፈው ውሳኔ ያስረዳል፡፡

ከኅዳር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በጨው ግብይት ሰንሰለት ውስጥ ተሳታፊ ለሚሆኑ አካላት፣ በወጣላቸው የመግዢያና መሸጫ ዋጋ ተግባራዊ እንዲሆን ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል፡፡

በተለይ ጨው የሚመረትባቸው ክልሎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት፣ በፋብሪካ የታጠበ ጥሬ ጨው በግብዓትነት ከሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ውጪ ከማምረቻ ቦታ ወደ ገበያ እንዳይወጣ፣ በየመዋቅራቸው ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ የማሳሰቢያ ደብዳቤውን በዋናነት ለአፋር ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለንግድ፣ ኢንዱስትሪና ትራንስፖርት ቢሮ ልኮ በግልባጭ ለሚመለከታቸው 14 ተቋማት አስታውቋል፡፡

ጨው የማምረቱን ሥራ በኢትዮጵያውያንና በቱርክ ባለሀብቶች በ300 ሚሊዮን ብር ተቋቁሟል ለተባለው ኤስቪኤስ የጨው ማምረቻ ድርጀት መሰጠቱም ታውቋል፡፡ ቫቭ ዲስትሪካት በተባሉት የቱርክ ባለሀብት፣ የሳራ ቡና ኤክስፖርተር ባለቤት አቶ ሰይድ ዳምጠውና ስታር ቢዝነስ ግሩፕ በጋራ ያቋቋሙት ጨው ፋብሪካ፣ የሦስት ወራት መጠባበቂያ ማለትም ጥሬ ዕቃ የሚያቀርብበት፣ የተመረተውን የሚሸጥበትና መጠባበቂያ የሚሆን ከ635.6 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልገውም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአፍዴራ የተተከለው ዘመናዊ የጨው ማምረቻ ፋብሪካ (ኤስቪኤስ) ቆሻሻውን ከጨው በመለየት በኬሚካል አጥቦና አድርቆ ከፈጨ በኋላ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አዮዲን በመቀላቀል፣ በፀሐይና በንፋስ አዮዲኑ እንዳይጠፋ አየር በማያስወጣ ማሸጊያ በማድረግ ለሽያጭ የማዘጋጀት ግዴታ እንደተጣለበት ተገልጿል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...