Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ መሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወደ ፌዴራል መንግሥት ተዛወሩ

የአዲስ አበባ መሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወደ ፌዴራል መንግሥት ተዛወሩ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሌ፣ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ፊርማ ኅዳር 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በወጣ ደብዳቤ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው የተሾሙት አቶ ሰለሞን፣ ባለፈው ዓርብ ኅዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. አዲሱን የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀላቅለዋል፡፡

አቶ ሰለሞን ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በትግራይ ክልል የመቐለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ በኋላም የትግራይ ክልል የከተማ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡

በኅዳር 2004 ዓ.ም. የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ ከወጣ ከአሥር ወራት በኋላ አቶ ሰለሞን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት፣ በአቶ ኩማ ደመቅሳ ከንቲባነት ወቅት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በአቶ ሰለሞን የአምስት ዓመታት የሥልጣን ቆይታ በአዲስ አበባ መሬት ዘርፍ በርካታ ሕጎች ወጥተዋል፡፡ በርካታ አመራሮችና ሠራተኞች ከሥራ ተሰናብተዋል፡፡

የተቀላቀለ ስሜት እየተንፀባረቀበት የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ዘርፍ አሁንም ከቅሬታ ነፃ መሆን አልቻለም፡፡ በአዲስ አበባ መሬት ሕገወጥ አሠራር ብቻ ሳይሆን ሙስና የተንሰራፋበት በመሆኑ፣ የከተማው ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

መንግሥት ይህንን ችግር ለመቅረፍ በርካታ የመዋቅር ለውጥ ከማድረጉ በተጨማሪ፣ በርካታ ሕጎችን ሲያወጣ ቆይቷል፡፡ ዕርምጃን በሚመለከትም ከ600 በላይ አመራሮችና ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ የወሰደ ሲሆን፣ የተወሰኑት በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡     

አቶ ሰለሞን በመሬት ዘርፍ ችግር እንዳለ ያምናሉ፡፡ አቶ ሰለሞን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ከተማ በመሬት ዘርፍ ያለውን ችግር ለመፍታት ዘመናዊ አሠራር መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡

‹‹በመሬት ዘርፍ ያለውን ችግር ለመፍታት በርካታ ደንቦችንና መመርያዎችን አሻሽለን ወደ ሥራ አስገብተናል፡፡ ችግር ባለባቸው አመራሮችና ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ ወስደናል፤›› ሲሉ አቶ ሰለሞን በሥልጣን ዘመናቸው ካከናወኗቸው ሥራዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ የአሠራር ማሻሻያ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ ሥራ በተጨማሪ በተለይ በሊዝ አዋጁ በዋናነት መሬት የሚቀርበው በሊዝ ጨረታ በመሆኑ፣ በየወሩ በርካታ መሬቶች በጨረታ መቅረባቸውን በመልካም ጎን ይመለከቱታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በመልሶ ማልማት ሥራዎች በርካታ ቦታዎችን ነፃ በማድረግ ለግንባታ ያዘጋጁ መሆኑን አቶ ሰለሞን ገልጸው፣ ነገር ግን በመልሶ ማልማት ፕሮግራም የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ፈታኝ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

‹‹ከ600 ሔክታር በላይ መሬት በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ነፃ አድርገናል፡፡ በማድረግ ላይም ነን፡፡ አሁን የሚታዩት ልማቶችም የዚህ ፕሮግራም ውጤቶች ናቸው፤›› ሲሉ አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሰለሞን እንደሚሉት፣ በአጠቃላይ በዘርፉ ኪራይ ሰብሳቢነት (ሙስና) አለ፡፡ ችግሩ በአመራሮች ላይም ያለ ስለሆነ ከባድ ትግል ይጠይቃል ይላሉ፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ሲሉ ጉዳዩ ያለበትን ደረጃ አስረድተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን እንደ አዲስ ከመሠረቱ በኋላ ሚኒስትር ዴኤታዎችን በመሾም ላይ ይገኛሉ፡፡

ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ እስካሁን ሳይነካ ቀጥሏል፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡ በቅርቡ በሚጠራው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አዳዲስ ሹመቶች ይፋ እንደሚደረጉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡     

 

  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...