Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአገር አቋራጭ አውቶቡሶች ዘመናዊ የቲኬት አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው

በአገር አቋራጭ አውቶቡሶች ዘመናዊ የቲኬት አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው

ቀን:

– ቲኬት ቆራጮች ሥጋት ገብቷቸዋል

በ1,500 የአገር አቋራጭ አውቶቡሶች በመላው የአገሪቱ ትራንስፖርት መስመሮች እንደሚጀመር ይፋ የተደረገው ዘመናዊ የቲኬት ሽያጭ አገልግሎት፣ ተሳፋሪዎች ከዚህ ቀደም ይገጥማቸው የነበረውን እንግልትና አላስፈላጊ ወጪ እንደሚያስቀር ተገለጸ፡፡

ክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከአውቶቡስ ባለንብረቶች ማኅበራት ጋር በመሆን አገልግሎቱን ለማቅረብ ለሁለት ወራት ሲያዘጋጅ የቆየውን በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት የሚሠራ የቲኬት አገልግሎት፣ ከመጪው ታኅሳስ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በ170 የጉዞ መስመሮች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀመር ይፋ ተደርጓል፡፡ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ቴክኖሎጂው ሥራ ላይ እንዲውል አደርጓል፡፡

ከአዲስ አበባ በመነሳት በሁሉም የአገሪቱ መዳረሻ መስመሮች በ1,500 የአገር አቋራጭ አውቶቡሶች የሚጀመረው ይህ የኤሌክትሮኒክ ቲኬት ሽያጭ፣ በመናኸሪዎች ሲታዩ የነበሩ ወከባዎችን ከማስቀረት ጀምሮ ቲኬት ለማግኘት በተጓዞች ላይ ይደርሱ የነበሩ እንግልቶችን ያስቀራል ሲሉ፣ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለ ማርያም ገለጸዋል፡፡

አቶ ካሳሁን ማክሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንደተናገሩት፣ ዘመናዊው አሠራር በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት አምስቱም መናኸሪያዎች ማለትም በአውቶቡስ ተራ፣ በአየር ጤና፣ በአስኮ፣ በላምበረትና በቃሊቲ መናኸሪያዎች ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ቲኬትና ክፍያ ሥርዓቱ በ21 የአውቶቡስ ባለንብረቶች ማኅበራት አማካይነት እንዲጀመር ስምምነት ተደርሶ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥራው እንደሚጀመር የገለጹት ደግሞ፣ የአገር አቋራጭ አውቶቡስ ባለንብረቶች ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃነ አምባዬ ናቸው፡፡ አቶ ብርሃነ እንዳሉት፣ ከመናኸሪያ ውጪ የሚታየውን ‹‹የሕገወጥ›› ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ በመናኸሪያዎች አካባቢ የሚታየውን ግርግር ብሎም በበርካቶች ተሳፈሪዎች ዘንድ ለአገር አቋራጭ አውቶቡሶች የነበረው አመኔታ እንደሚመለስ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በደርሶ መልስ ለተሳፋሪዎች አገልግሎት የሚሰጠው ይህ ቴክኖሎጂ፣ ተሳፋሪዎች ለጉዞ አስቀድመው ዕቅድ እንዲይዙና ወደሚፈልጉት ቦታ ለመጓዝ ሲያስቡም ከሳምንት በፊት ቲኬት እንዲቆርጡ የሚያስችላቸው እንደሆነ፣ የክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙኒር ዱሪ ተናግረዋል፡፡ ተሳፋሪዎች ክፍያ ለሁሉ በሚባሉ ወኪሎች አማካይነት ቲኬት እንዲያገኙ እንደሚደረግ፣ በሚሳፈሩበት ዕለትም የቀረጡትን ቲኬት ይዘው በመገኘት መሳፈር የሚችሉበት አሠራር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ለተቆረጠው ቲኬት ትክክለኛነት የሞባይል አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ ጭምር ማረጋጫ በመላክ የሚሠራው ቴክኖሎጂ ከወዲሁ ሥጋት የፈጠረባቸው የቀድሞ ቲኬት ቆራጮች ሥጋት እንደገባቸውና ሥራቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ መግለጻቸው ታውቋል፡፡ ለሸገር ሬዲዮ ሥጋታቸውን የገለጹ ቲኬት ቆራጮች ስለቴክሎጂው ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ቢናገሩም፣ አቶ ካሳሁን ግን ማንም ከሥራው እንደማይፈናቀልና ቴክኖሎጂውን ለመተግበር ሥልጠና መውሰድ የሚችሉ ሁሉ እንደሚካተቱበት አስታውቀዋል፡፡

አቶ ሙኒር በበኩላቸው እስካሁን 102 ቲኬት ቆራጮች የኤሌክትሮኒክ ቲኬትን የተመለከቱ ሥልጠናዎችን ለሁለት ሳምንት እንዲከታተሉ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...