Wednesday, October 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በኤሌክትሪክ ማመንጨት ለሚሰማሩ የግል ኩባንያዎች የተቀመጠው የማመንጫ ጊዜ ገደብ ሊራዘም ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ታዳሽ የኃይል ማመንጫዎችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ለሚሳተፉ የግል ኩባንያዎች ይሰጥ የነበረው የጊዜ ገደብ ሊራዘም ነው፡፡

የጊዜ ገደቡን ለማራዘም የኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 ማሻሻል የሚጠበቅ ሲሆን፣ የዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅም ማክሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

በሥራ ላይ የሚገኘው የኢነርጂ አዋጅ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት፣ ለማስተላለፍ፣ ለማከፋፈልና ለመሸጥ፣ ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ወይም ወደ ውጭ አገር በመላክ ሥራ ላይ የግል ኩባንያዎች መሰማራት እንዲችሉ ይፈቅዳል፡፡

የግል ኩባንያዎች ያመነጩትን ኃይል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በድርድር ታሪፍ እንዲሸጡ ነው የሚፈቀደው፡፡ ነገር ግን ኩባንያዎች የማመንጨት ፈቃድ ከወሰዱበት ጊዜ አንስቶ ኃይል ማመንጨት እንደሚጠበቅባቸው የቀድሞው አዋጅ ይደነግጋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ የጊዜ ገደብ በቂ ባለመሆኑና ይህ አዋጅ ካወጣበት ጊዜ አንስቶ ፍላጎት ያሳዩ ኩባንያዎች በዚህ የጊዜ ገደብ ምክንያት ሲሸሹ እንደቆዩ ማብራሪያው ያሳያል፡፡ ከሌሎች እንደ ኢንዶኔዥያ ካሉ አገሮች ተሞክሮ በመውሰድ ይህ የጊዜ ገደብ እንዲራዘም በመንግሥት መወሰኑን ይገልጻል፡፡

 በመሆኑም በውኃ ኃይል ማመንጫ ለሚሰማሩ የአምስት ዓመት የጊዜ ገደብ ለፀሐይ፣ ለንፋስ፣ ለባዮ ማስ፣ ለድንጋይ ከሰልና ለተፈጥሮ ጋዝ ማመንጫዎች ደግሞ ሦስት ዓመት እንዲሆን በረቂቅ አዋጁ ቀርቧል፡፡ ረቂቁ ለዝርዝር ዕይታ ለተፈጥሮ ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች