Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአይኤምኤፍ ኃላፊ ለሁለት ቀናት ቆይታ እንደሚመጡ ይጠበቃል

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ጠቅላይ ሚስትሩን ጨምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኃላፊዎችን ያነጋግራሉ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስቲያን ላጋርድ፣ ከሐሙስ ታኅሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት ቆይታ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

ክሪስቲያን ላጋርድ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ሲጠበቅ፣ በማግሥቱ ማለትም ታኅሳስ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት በሚካሄደው የውይይት መድረክ ንግግር እንደሚያሰሙ ታውቋል፡፡

‹‹የአፍሪካ የኢኮኖሚ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች በቀጣናው አሳታፊ ዕድገት እንዲመዘገብ ቴክሎኖሎጂ የሚኖረው ሚና፤›› በሚል ርዕስ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ተጋባዥ በመሆን ንግግር የሚያቀርቡት የአይኤምኤፍ ዳይሬክተሯ፣ ከንግግራቸው በኋላም ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ የሚያደርጉበት መርሐ ግብር መሰናዳቱን ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ከስድስት ዓመታት በፊት የቀድሞውን የአይኤምኤፍ ዳይሬክተር ዶሚኒክ ስታራውስ ካህንን በመተካት እየሠሩ የሚገኙት ላጋርድ፣ የአፍሪካ ጉዳዮችን የሚከታተሉላቸውን ኢትዮጵያዊውን አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴን መሾማቸው አይዘነጋም፡፡ ይህም ሆኖ አይኤምኤፍ በኢትዮጵያ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀዛቀዘ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ሲያቀርባቸው የነበሩ የሰሉ ትችቶች ለአይኤምኤፍ እንቅስቃሴ መዳከም ምክንያት እንደነበሩ ሲነገር ይደመጣል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በቅርቡ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት፣ የአይኤምኤፍ ኃላፊዎች እንደሚመጡና እንደሚወያዩ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ካሰማቸው የማሻሻያ ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑት የዓለም ባንክንና አይኤምኤፍን ሐሳቦች የሚያንፀባርቁ ናቸው በማለት የንግዱን ማኅበረሰብ መወረፋቸው አይዘነጋም፡፡ 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች