Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ ተጠቆመ

ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ ተጠቆመ

ቀን:

ላለፉት በርካታ ዓመታት የፌዴራል መንግሥት ካቢኔ አባልና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የክልሉ ፓርቲ ሕወሓት መወሰኑን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገለጹ። 

የሕወሓት አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰኞ ታህሳስ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በፌዴራልና በክልሉ መንግሥት፣ እንዲሁም በፓርቲ ኃላፊነቶች የሚመደቡ የሥ አስፈጻሚ አባላቱን ዝርዝር ይፋ አድርጓል። 

አምስት የሥ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በትግራይ ክልል፣ አራቱ ደግሞ በፌዴራል ደረጃ እንዲሠሩ መወሰኑን የሕወሓት አስፈጻሚ መግለጫ ያመለክታል።

በዚህ መሠረት በትግራይ ክልል እንዲሠሩ የተመደቡት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (/)ዲስ ዓለም ባሌማ (/) እና / ኬሪያ ኢብራሂም ናቸው።

በሕወሓትሕፈት ቤት የፖለቲካ ኃላፊነቶች ላይ የተመደቡት ደግሞ ቀደም ሲል የሕወሓት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት  አቶለም ገብረ ዋህድ፣ በፌዴራል መንግሥት የቀድሞ የመንግሥት ጉዳዮች ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የፍትሕ ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው።

በፌዴራል መንግሥት መዋቅሮች ውስጥ እንዲሠሩ ከተመደቡት መካከል፣ በሕወሓት ጽሕፈት ቤት ውስጥ እያገለገሉ የነበሩትናወሓት በቅርቡ ባካሄደው 35 ቀናት የፈጀ ግምገማ ማገባደጃ ላይ፣ ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት በተጨማሪ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ የመረጣቸው / ፈትለወርቅ ብረ እግዚአብሔር ናቸው።

በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት እያገለገሉ የሚገኙ ሦስት የሕወሓት አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ በፌዴራል መንግሥት መዋቅር ውስጥንዲያገለግሉመድበዋል። እነዚህ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት አብረሃም ተከስተ (/) እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ ናቸው።

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶባይ ወልዱን ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነትና ከድርጅቱ ሊቀመንበርነት በማንሳት፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው እንዲያገለግሉ መወሰኑ ይታወሳል። በድርጅቱ አሠራር መሠረት የክልሉ ፕሬዚዳንት የፓርቲው አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል መሆን የሚጠበቅበት በመሆኑ፣ አቶ ዓባይን ከሥራ አስፈጻሚነትናፓርቲው ሊቀመንበርነት በማንሳቱ ከክልል ፕሬዚዳንትነትልጣናቸውም እንደሚነሱ ይጠበቃል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘምወሓት አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አባላቱን በፌዴራል፣ በክልልና በፓርቲ ምድቦች ባለፈው ሰኞ ደልድሏል። በትግራይ ክልል እንዲያገለግሉ ከተመደቡት ውስጥ የፓርቲው ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን  (/ር) ለክልሉ ፕሬዚዳንትነት ሆነው እንደሚቀርቡ፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የፌዴራል ፓርላማ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የሚመረጠው ደግሞ ከክልሉ ምክር ቤት አባላት መካከል እንደሚሆን የክልሉ መንግሥት ይደነግጋል።

በመሆኑም እሳቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ለመሆን የሚጠበቅባቸውን የክልሉ ምክር ቤት አባል የመሆን ሕገ መንግሥታዊ መሥፈርት እንዴት ሊያሟሉ እንደሚችሉ የተጠየቁት እኝሁ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ጉን ተከትሎ የተጓደሉ የክልሉ ምክር ቤት አባላትን ለመተካት በሚካሄድ የማሟያ ምርጫ ተሳትፈው የምክር ቤቱ አባል ሊሆኑ እንደሚችሉና ይህ ሒደትም በፍጥነት እንደሚከናወን ገልጸዋል።

የማሟያ ምርጫ የሚካሄደው በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በተለያዩ ምክንያቶች የተጓደሉ አባሎቻቸው እንዲሟሉላቸው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ቦርዱ ጥያቄው በቀረበስት ወራት ውስጥማሟያ ምርጫ እንደሚያካሂድምርጫ ሕጉ 532/2007 አንቀጽ 29 ሥ ተደንግጓል።

የፌዴራል ፓርላማ ተመራጭ አባል ለአፈ ጉባዔው በማሳወቅ አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ መልቀቅ እንደሚችል የሥነ ሥርዓትና የአባላት ምግባር ደንቡ ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ደብረ ጽዮን (/ር) ከፌዴራል በፓርላማ አባልነታቸው ከመልቀቅ የሚያግዳቸው ነገር አይኖርም።

ከትግራይ ክልል ምክር ቤት የማሟያ ምርጫ ጥያቄ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀርቦ እንደሆነ ሪፖርተር ላቀረበው ጥያቄ፣ የቦርዱ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዓለም ዓባይስከ ማክሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ አለመቅረቡን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...