Monday, March 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብርሃንና ቡና ባንክ የምርት ገበያን ሥርዓት ተቀላቀሉ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ክፍያና ርክክብ ለሚያስፈጽሙ ሁለት ባንኮች ተጨማሪ ባንኮች ዕውቅና ሰጠ፡፡ ዕውቅና የተሰጣቸው ባንኮች ቁጥር 12 ማድረሱንና ለተመሳሳይ ሥራ አምስት ባንኮች ጥያቄ ማቅረባቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

ባለሥልጣኑ ማክሰኞ፣ ታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ዕውቅና የሰጣቸው ብርሃን ባንክና ቡና ባንክ ናቸው፡፡ ባለሥልጣኑ በምርት ገበያው አማካይት ክፍያ ለሚያስፈጽሙ ተቋማት ዕውቅና መስጠትና አፈጻጸማቸውንም የመቆጣጠር ሥልጣን በአዋጅ እንደተሰጠው የጠቀሱት የምርት ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኦሌሮ ኦፒዮ (ኢንጂነር)፣ በዚህም ባንኮቹ እስካሁን በሙከራ ደረጃ ሲ የነበረውን ሥራቸውን ወደ ሙሉ ትግበራ መግባታቸውን የሚያጋግጥ ሒደት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከእጅ ንክኪ ነፃ የክፍያ ሥርዓት ለመፈጸም፣ ባለሥልጣኑ የሚያስተገብረው ሥርዓት ባንኮችንም ሆነ የግብይቱን ክንውን እንደሚጠቅም አስታውቀዋል፡፡  

ለሁለቱ ባንኮች የዕውቅና ሰርተፍኬቱን ያበረከቱት የባለሥልጣኑ ቦርድ ሰብሳቢና በሚኒስትር ማዕረግ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ይናገር ደሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ለባንኮቹ የተጠሰጠው ዕውቅና የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ አጋዥ ነው ብለዋል፡፡ አዲሱ የምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ ነገራም፣ የምርት ገበያው ስድስት ምርቶችን እንደሚያገበያይ ጠቅሰው፣ አዳዲስ ምርቶችን ለማገበያየት ዝግጅት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

የቡና ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ታደሰ ጭንቅልና የብርሃን ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አሰፋ፣ የምርት ገበያን ግብይቶች ለማስፈጸም በተቀመጠው ሕግ መሠረት እንደሚተገብሩ አስታውቀዋል፡፡

በ2009 ዓ.ም. ምርት ገበያው በአሥሩም ባንኮች አማካይነት የ1,464 አባላትና የ4,149 ደንበኞች በድምሩ 5,613 የባንክ ሒሳቦች ተከፍተው አገልግሎት እንደሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ የተጠቃሚዎች ቁጥር በ2008 ዓ.ም. ከነበሩት 5,292 የባንክ ሒሳቦች ጋር ሲነፃፀሩ የ5.72 በመቶ ጭማሪ አላቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በቅደም ተከተል የ42.27 በመቶ፣ 12.54 በመቶ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ 11.66 በመቶ የክፍያ ተሳትፎ እንደነበራቸው መረጃው ጠቅሷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሁሉም ባንኮች ከተፈጸመው የ25.91 ቢሊዮን ብር ክፍያ ውስጥ 99.997 በመቶው የክፍያ ሥርዓቱን ተከትሎ ያለ ምንም ችግር እንደተከናወነ፣ ቀሪው 0.003 በመቶ ደግሞ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እጥረት ጋር በተያያዘ ጥቃቅን ግድፈቶች እንደተስተናገዱበት የምርት ገበያው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህም ሆኖ በምርት ገበያው አባላትም ሆነ በደንበኞች ጥቅም ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዳልተፈጠረ መረጋገጡን ምርት ገበያው ይገልጻል፡፡

      በ2009 ዓ.ም. የ665,888 ሺሕ ብር ክፍያ በሦስት ባንኮች የአሠራር ስህተት ሳቢያ የተሳሳተ መረጃ ለምርት ገበያው ተላልፎ ወዲያውኑ መታረሙ ተጠቅሷል፡፡ ይህም በ2008 ዓ.ም. ካጋጠመው የ21 ሚሊዮን ብር የአሠራር ስህተት ጋር ሲነፃፀር፣ በ96.84 በመቶ መሻሻል አሳይቷል ብሏል፡፡

      በባለሥልጣኑ ዕውቅና ተሰጥቷቸው በክፍያ ሥርዓቱ ውስጥ ከሚሳተፉ ባንኮች  ስምንቱ የምርት ገበያውን የክፍያ ሥርዓት የሚከተል ሙሉ ለሙሉ ዘመናዊ ሥርዓት የተገበሩ (አውቶሜትድ) ሲሆን፣ ዳሸንና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንኮች ደግሞ ሥራውን አጠናቀው በሙከራ ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች