Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትፈጣኑ ስንብት

ፈጣኑ ስንብት

ቀን:

በአጭር የምሥረታ ዕድሜ ከአገሪቱ ታላላቅ ክለቦች ተርታ የሚገኘው ደደቢት የዋና አሠልጣኝነት ቅጥር ከፈጸሙ የአምስት ወራት ዕድሜ ያስቆጠሩትን ዮሐንስ ሳሕሌን ከኃላፊነት ማንሳቱ ታውቋል፡፡ ስንብቱን አስመልክቶ ክለቡም ሆነ አሠልጣኙ የሰጡት ማብራሪያ የለም፡፡

ከውድድር ዓመቱ ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የደደቢት ዋና አሠልጣኝ ሆነው የቆዩት አሠልጣኝ ዮሐንስ፣ ቀደም ባሉት ዓመታት ክለቡን በሥራ አስኪያጅነትና በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ያገለገሉበት ወቅት እንደነበር ይታወቃል፡፡ አሠልጣኙ ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ከመሆናቸው በፊት የደደቢት እግር ኳስ ክለብ የዋና አሠልጣኝነት ድርሻ ይዘው ለወራት ቆይተውም ነበር፡፡

በተጀመረው የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጓቸው ሦስት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፈው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፈው፣ ወልዲያ ላይ ደግሞ ከወልዲያ ከተማ ጋር አቻ የተለያዩበትን ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

- Advertisement -

በደደቢትና በዋና አሠልጣኙ መካከል የተደረሰው ፈጣኑ ስንብት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በስማ በለው ካልሆነ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል የታወቀ ነገር የለም፡፡ ዝርዝሩን አስመልክቶ ሪፖርተር ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...