አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 1 ኪሎ ግራም የጎድን ሥጋ
- 10 የነጭ ሽንኩት ፍሬ በደቃቁ የተከተፈ
- 2 ጭልፋ የወይራ ዘይት (የፈለጉትን ዓይነት ዘይት መጠቀም ይቻላል)
- ጨው እንዳስፈላጊነቱ
- 2 የሻይ ማንኪያ የተከተፈ አረንጓዴ ቃሪያ
- 2 የሻይ ማንኪያ ጦስኝ
አዘገጃጀት
- ነጭር ሽንኩቱን፣ ጦስኙን፣ ዘይቱን፣ ጨውንና ቃሪያውን በአንድ ሳህን መቀመላቀል፤
- ጎድኑን በመጥበሻ ላይ አድርጎ የተዘጋጀውን ድብልቅ ማፍሰስ፤
- ጎድኑ የፈሰሰበትን ድብልቅ እንዲመጠው ከ10 እስከ 15 ደቂቃ መጠበቅ፤
- ማብሰያ ኦቨኑን 260 ዲግሪ ሴንቲግሬድ አድርጎ ለ20 ዲቃቃ ማብሰል፣ ከ20 ደቂቃ ማብሰል በኋላ ከየሙቀት መጠኑን ወደ 165 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቀንሶ እስከ 60 ደቂቃ ማብሰል
- ሥጋውን በአሉሚኒየም ፎይል ጠቅልሎ ማብሰያ ውስጥ ማስገባት ሥጋው እኩል እንዲበስል ያደርገዋል፡፡
(ከኦል ሪሲፔስ ድረ ገጽ)