Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅሥራና ባለሙያ ሲገናኙ

ሥራና ባለሙያ ሲገናኙ

ቀን:

ሁሉም ሥራ ራሱን የቻለ ባለሙያ ይሻል (ይፈልጋል) እንጨት መፍለጥ እንኳ! እንጨት ያለ ሙያተኛው ቢፈለጥ በመጥረቢያው እግር ይጎዳል ወይም እንጨቱ ዘሎ (ተፈናጥሮ) ዓይን ወይ ጥርስ ወይ ግንባር ሊመታ ይችላል፡፡ እንኳንስ ሰፊ የምህንድስና ዕውቀትና ጥበብ እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠር መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቀው የአስፋልት ሥራ እንዲሁ በዘፈቀደ ያለ ሙያተኛ አይሠራም፡፡ መሠራትም የለበትም፡፡ ግና የአዳማ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት ሹማምንት የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ተከራይተው፣ በራሳቸው የሰው ኃይል ግንባታውንም ሆነ ቁጥጥሩን እንሠራዋለን (መሥራት አለብን) በማለት በ2008 ዓ.ም. ማጠናቀቂያና በ2009 ዓ.ም. መግቢያ ባሉት ወራት ከማያ ሆቴል እስከ መረብ ቁጥር 2 ሥጋ ቤት ያለውን መንገድ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ሠርተው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም የተሠራው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ አገልግሎት በጀመረ በ15ኛው ቀን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል  ፈራርሶ የነበረው እንዳልነበረ ሆኖ ይገኛል፡፡ ዘጠና ቀናት ሳይሞላው (ሳያስቆጥር) በመፈራረሱ የሙከራ ጊዜውን ያልጨረሰ አስፋልት መንገድ (Apprentice Asphalt) በሚል መጠሪያ ስም የአካባቢው ነዋሪ እየጠራው ይቀልዳል፡፡ በአንፃሩ በናዝሬት ከተማ ዳርቻ ሰንጥቆ የሚያልፈውን የቀለበት መንገድ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ አገር በቀሉ ኮንትራክተር ግንባታውን፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን መንግሥታዊው ድርጅት (ትኮዲአማ) በጥምረት እየገነቡ (እየሠሩ) ይገኛሉ፡፡ ድንቅና ማለፊያ ሥራ ነውና በርቱ ተበራቱ ሊባሉ ይገባል፡፡ እናም በቅርቡ የናዝሬት ከተማን እንዲያስተዳድሩ በክልሉ መንግሥት እንደ አዲስ የተሾሙ ተሿሚዎች በመንገድ ጥራትና ደኅንነት፣ በከተማ ማስተር ፕላን ትግበራና ውሳኔዎች ላይ ቁርጠኝነት ይጠበቅባቸዋል እላለሁ፡፡ ሥራና ባለሙያ ሲገናኙ እንዲህ ዓይነት ውጤት ይገኛል፡፡

አማቾ ማሆጋኖ፣ ከናዝሬት 

ጨረቃና ፀሐይ

ግዛቴ ነው ብላ

ሠማይን በሞላ

ሆና ከአናት በላይ

ስታቃጥል ፀሐይ

ስታጠቁር ገላ

ስታሲዘን ጥላ

በውሎው መጨረሻ

እንደው ወደ ማምሻ

ይሄንን ብትሰማ

ጨረቃ ተገርማ

ከዋክብት አስከትላ

ተውባ ተኳኩላ

በብርሃን ስቃ

ፈ – ን – ድ – ቃ

ስ – ታ – ቃ – ጥ – ል

ብርሃን ብትጥል

ጨለማው ቢገለል

ሠማይ ተገረመ

በውበት ሰጠመ

ጨረቃና – ፀሐይ

ብርሃን ሰጥተው ሳለ

የአንዳቸው ግን አቃጠለ

ቀንና ሌት እየነጣጠለ፡፡

ታሪኩ ከበደ፣ ምክረ ሰይጣን፣ (2008)

***************

ከሦስት ሰዎች አንድ ልጅ የመውለድ ሳይንስ

በእንግሊዝ የሚገኙ ዶክተሮች፣ ከሦስት ሰዎች አንድ ልጅ እንዲወለድ በማድረግ የአቅም ማነስ፣ የአእምሮ ጉዳት፣ የጡንቻ መላላትና የልብ መታወክ በሽታን ማስቀረት እንችላለን ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ዶክተሮቹ ከሦስት ሰው አንድ ልጅ የማስወለድን ሳይንስ እንዲተገብሩ የዩናይትድ ኪንግደም የውልደት ተቆጣጣሪ ቢሮ ውሳኔን እየተጠባበቁ ሲሆን፣ ተቆጣጣሪው ሳይንሱ ጥቅም ላይ ይዋል ወይስ ይከልከል የሚለውን ውሳኔውን በቅርቡ ያስታውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሳይንሱ ከዚህ ቀደም በሜክሲኮ የተሞከረ ሲሆን፣ በእንግሊዝ ግን ለተጨማሪ ምርምር እንዲዘገይ ተደርጓል፡፡

ከስምንት እርግዝናዎች ላንዱ ላይሳካ ይችላል የተባለው ይኸው ሳይንስ፣ በፈቃጁ አካል ይሁንታን ካገኘ፣ በሽታዎቹ ባሉባቸው ላይ ብቻ ተግባራዊ እንዲሆን ጠንካራ አሠራር መዘርጋት እንዳለበትም ከባለሙያዎች ሐሳብ ቀርቦበታል፡፡

 ***************

ለአምስት ዓመት የቤት እንስሳት እንዳይኖረው የታገደ ጡረተኛ

ጀምስ ማክሊላንድ የተባለው የ67 ዓመት ስኮትላንዳዊ ጡረተኛ ውሻውን በአግባቡ ባለመያዙ ለአምስት ዓመታት የቤት እንስሳት እንዳይኖረው ታገደ፡፡

ማክሊላንድ በስኮቲሽ የእንስሳት ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት ገደብ የተጣለበት፣ በቤቱ ውስጥ ለ6 ወራት ያቆየችውን ውሻ በአግባቡ ባለመንከባከቡ፣ የውሻው ክብደት በመቀነሱ፣ ፀጉሩ በመብነኑና፣ ሰውነቱ ላይ የመላላጥና የመቁሰል አደጋ በመድረሱ ነው፡፡

ጉዳት የደረሰባት ትራክሲ የተባለችው ውሻ በተደረገላት ሕክምና ሙሉ ለሙሉ የዳነች ሲሆን፣ ለሚያሳድጓት አዲስ ቤተሰቦች እንደምትሰጥ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

  ***************

የጣት አሻራ

  • የጣት አሻራ የሚፈጠረው ከ3ኛው የፅንስ ወራት ጀምሮ ነው፡፡
  • የሰው ልጅ ህልም ማየት ወይም መስማት የሚጀምረው የእናቱ ማህፀን ውስጥ እያለነው፡፡
  • ሕፃናት ሲወለዱ በሰውነታቸው ውስጥ 26 ቢሊዮን ሴሎች ይገኛሉ፡፡ በጉርምስና ወቅት የሰውነታችን ሴሎች ቁጥር ወደ 50 ትሪሊየን ያድጋል፡፡
  • በሰውነታችን ውስጥ በአንድ ሴኮንድ 15 ሚሊዮን የደም ሴሎች ይሞታሉ፡፡
  • የሰውነታችን ትልቁ እጢ ጉበት ነው፡፡
  • በሰውነታችን ውስጥ በአንድ ሰዓት 100 ግራም ፕሮቲን ይመነጫል፡፡
  • በእናት ማህፀን ውስጥ ባለው የ9 ወራት ቆይታ፣ የፅንስ ልብ 60,000,000 ጊዜ ይመታል፡፡
  • ዓይናችን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 20 ሚሊዮን ጊዜ ይርገበገባል፡፡

የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ፤ 2006

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...