Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትፌደሬሽኑ የመስክ ግምገማ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ

ፌደሬሽኑ የመስክ ግምገማ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 25 እና 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ባደረገው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የፌዴሬሽኑ የቀጣዩን አራት ዓመት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ አድርጓል፡፡ ጉባኤው የቀድሞ አትሌቶችን ወደ ኃላፊነት እንዲመጡ ያደረገበት መንገድ ከወትሮው የተለየ ሆኖ መጠናቀቁ ‹‹ለስፖርቱ አንድ ዕርምጃ›› ወደፊት ተብሎለት ተጠናቋል፡፡ አዲሱ የፌዴሬሽኑ አመራርም የአትሌቲክሱ መሠረት የሆኑ ክልሎች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የመስክ ግምገማ ለማድረግ ማቀዱ ተሰምቷል፡፡

ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ፣ በኃይሌ ገብረሥላሴ የሚመራው አዲሱ አመራር ከተቋሙ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአገሪቱን አትሌቲክስ ለማሳደግ እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለመገምገም ዕቅድ ይዟል፡፡ እስካሁንም ከአትሌቶች፣ ከአሠልጣኞችና ከአትሌቶች የማናጀር ተወካዮች ጋር በአትሌቲክሱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መነጋገሩ ታውቋል፡፡

በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የመስክ ግምገማ በዋናነት ክልሎች በአትሌቲክሱ ያላቸው ወቅታዊ አቋምና እንቅስቃሴ፣ የአትሌቶቻቸው ፍላጎት፣ የፌዴሬሽኖች የጽሕፈት አደረጃጀትና ስፖርቱን የመምራት አቅም፣ በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የሚያስተዳድራቸው ፕሮጀክቶችና መሰል እንቅስቃሴዎችን እንደሚመለከት ተነግሯል፡፡ በአራቱ ክልሎች ማለትም በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ የተቋቋሙት የአትሌቲስ ፕሮጀክቶች በመስክ ግምገማው ይካተታሉ ተብሏል፡፡

- Advertisement -

አመራሩ የመስክ ግምገማውን ካጠናቀቀ በኋላ ደግሞ ከክለቦች ጋር የሚወያይበትን መድረክ እንደሚያመቻች ተነግሯል፡፡ ክለቦች ሁሉም በሚያስብል ደረጃ ለዕውቅና ባበቋቸው አትሌቶች ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ፣ ከክለቦች ይልቅ ከውድድር አዘጋጆች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው የማናጀር ተወካዮች የአንበሳውን ድርሻ ወስደው መቆየታቸው አግባብ እንዳልሆነ በመግለጽ ቅሬታ ማሰማት ከጀመሩም ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

በነበረው አሠራር ክለቦች አስፈላጊውን ሁሉ አድርገው ለዕውቅና የሚያበቋቸው አትሌቶች በማናጀር ተወካዮችም ሆነ በራሳቸው ግንኙነት ለትልልቅ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ከበቁ በኋላ ወደ ክለባቸው የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው፣ በዚህ ዓይነት መንገድ ክለቦች አትሌቶቹን መቆጣጠር ቀርቶ ለአትሌቶቹ ያወጣውን ወጪ ያደረጉትን እንኳ የመጠየቅ መብት እንደሌላቸው ጭምር ነው የብዙዎቹ ክለቦች አመራሮች ሲናገሩ የሚደመጡት፡፡

እነዚህና ሌሎችም በአትሌቲክሱ ዙሪያ ተሰግስገው የሚስተዋሉ በርካታ ችግሮች እንዳሉ የሚናገሩት እነዚሁ ክለቦች፣ በኃይሌ የሚመራው አዲሱ አመራር ይህን አቅጣጫ ለማስያዝ ቀላል የማይባል ፈተና ከፊት ለፊቱ የሚጠብቀው ስለመሆኑ ጭምር ይናገራሉ፡፡

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በ17 የስፖርት ዓይነቶች ተሰጥኦና ዝንባሌ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በዕድሜ ደረጃቸው በመመልመል ዘመናዊና ሳይንሳዊ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወቃል፡፡ ይሁንና እነዚህ የዘመናዊ ሥልጠናና ክትትል የሚደረግላቸው ታዳጊ ወጣቶች በተለይም በአሁኑ ወቅት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አይታወቅም፡፡ የኢትዮጵያ አትሌክስ ፌዴሬሽንም ከዚህ ተሞክሮ በመውሰድ ለዓመታት በወረቀት ላይ የቆየው የአትሌቲክሱን ህዳሴ ወደ መሬት በማውረድ ስፖርቱን በትክክለኛው መስመር ሊመራው እንደሚገባ የዘርፉ ሙያተኞች ይመክራሉ፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...