ጥቅምት ላይ በሶማሌላንድ በተካሄደው ምርጫ ያሸነፉት ሙሴ ባሂ አብዲን ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመው የፕሬዚዳንትነት ሥራቸውን ጀመሩ፡፡
በዴሞክራሲያዊ መንገድ ጥቅምት ላይ የተመረጡት ሙሴ ባሂ አብዲ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሲላንዮን በመተካት የሶማሌላንድ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ለመሆን በቅተዋል፡፡
የፕሬዚዳንቱ የቃለ መሃል ሥነ ሥርዓት በተለያዩ የጎረቤትና የአውሮፓ አገሮች ልዑካን ቡድን ታዳሚነት ተካሂዷል፡፡
አዲሱ ፕሬዚዳንት የሶማሌላንድን የኢኮኖሚ መውደቅ፣ ድህነትና የፀጥታ ጉዳይ ዋነኛ ሥራቸው እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡