Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከሚገኙ የልብስ መሸጫ መደብሮች በአንዱ::ለክርክር ጊዜ የለም ለማለት የሚመስል ዘመንኛ የዋጋ አነጋገር

ትኩስ ፅሁፎች

የሚሄድ በርጋታ

የሚሄድ በርጋታ ድምፁ ሣይሰማ

የሚኖር ይመስላል ከሁሉ የተስማማ

ራሱን ሰውሮ

ከሰዎች አዕምሮ

ቀርበነዋል ሲሉት የሚገኘው ርቆ

በጥርሱ እየሣቀ ሕይወቱን ደብቆ

ባልተጠበቀ ቀን ድንገት የሚመጣ

የቅጽበት ፈገግታው ከልብ የማይወጣ

አንስተው ጥለውት ገድለነዋል ብለው

ተነስቶ የሚገኝ ከመካከላቸው

ቢቀርቡት ቢርቁት የማይለወጠው

ሰላም ፍቅር እንጂ ጥላቻ የማይገዛው

ድምፁ ሳይሰማ የሚኖር በርጋታ

ዓይኖቹ ቀዝቃዛ ግንባሩ ማይፈታ

ምን? ይሆን ሚስጥሩ የሚደበቅበት

ፍቅሩ ወይ ጥላቻው የማይታወቅበት

ምንድነው? ከሰው ልጅ እሱ የሚፈልገው

ቢጥሉት ቢያፈርጡት የማይለወጠው፡፡

ንጉሴ ካሳዩ ወልደሚካኤል፣ ቅጠሎች ነን፣ (2010)

* * *

በፈረንጆች ገና የውበት ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ ቁጥር እየጨመረ ነው

በፈረንጆች አዲስ ዓመት መቃረብ ለገና በዓል ውብ ሆኖ ለመታየት የሚደረጉ የፊት ቀዶ ጥገናዎች ቁጥር መጨመሩን የዘ ኢንዲፔንደንት ዘገባ ያመለክታል፡፡ የፈረንጆች ገና የሚያከብሩት የሚደሰቱበት የዓመቱ የተለየ ጊዜም ብቻ ሳይሆን ሰዎች የበለጠ ተግባቢ የሚሆኑበትና ማኅበራዊ ግንኙነታቸውን የሚያሻሽሉበትም ነው፡፡ ለዚህ ልዩ ጊዜ ፀጉርን በሚገባ ተሠርቶ ወይም የፊት ሜካፕ አድርጎ መገኘት ብቻ በቂ የሆነ አይመስልም፡፡ በአሁኑ ወቅት ይልቁንም በውበት ቀዶ ጥገና አምሮ መገኘት የብዙዎች ውሳኔ እየሆነ እየተስተዋለ ነው፡፡ ዘገባው እንደሚያመለክተው ደግሞ ሰዎች በበዓሉ ላይ ውብ ሆኖ የመታየት ፍላጎታቸው እንደዚህ ጣሪያ እንዲነካ ያደረገው ሠልፊ ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ሰዎች ራሳቸውን ፎቶግራፍ እንስተው በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ካለጠፉ እዚያ ቦታ ላይ ነበሩ ወይ? የሚል ጥያቄ የሚነሳበት የሠልፊና የማኅበራዊ ድረ ገጽ ጊዜ ነውና፡፡

* * *

ቤልጂየም የቢራ መጠጣት ባህሏ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ አመላከተች

የቢራ ንግድ በቤልጂየም እጅግ አዋጭ የሚባል ቢዝነስ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ የቢራ ንግዱና የመጠጣት ባህል አገሪቱ ለአውሮፓ የምታበረክተው አንዱ ነገር ሆኖ እንዲመዘገብ ትፈልጋለች፡፡ ቤልጂየም የቢራ ባህሏ በማይዳሰሱ ቅርሶች ዘርፍ በዩኔስኮ እንዲመዘገብላት ጥያቄ አቅርባለች በማመልከቻው ላይ የአገሪቱ ቢራ አምራቾች ማኅበር እንደጠቀሰው በአገሪቱ ቢራ እንዲሁ የሚጠጣና የሚቸረቸርም መጠጥ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከሰዎች የዕለት ዕለት እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘና ከፌስቲቫሎች ጋርም ግንኙነት ያለው ነው፡፡

* * *

ጀሥቲን ቢበር በአድናቂው ላይ ቦክስ ሠነዘረ

ካናዳዊው የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ጀሥቲን ቢበር በአንድ አድናቂው ላይ ያደረሰው አካላዊ ጉዳት መነጋገሪያ ርዕስ አድርጎት ሰንብቷል፡፡ ባለፈው ሣምንት በባርሴሎና ተዘጋጅቶ ወደ ነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት በመሄድ ላይ ሳለ ነበር አጋጣሚው የተፈጠረው፡፡ ያሆ ኒውስ እንዳስነበበው፣ ድምፃዊው ፕሮግራሙ ወደተዘጋጀበት ቦታ በመሄድ ላይ ሳለ ከሩቅ የተመለከተው አድናቂ መኪናውን እየተከተለ ይሮጥ ጀመረ፡፡ በመኪናው መስኮት ውስጥ እጁን አሳልፎም ወጣቱን ድምፃዊ ለመንካት ይሞክራል፡፡ የጂሥቲን ምላሽ ግን አድናቂውን እንዳገኘ ታዋቂ ሰው አልነበረም፡፡ ቡጢ ሰነዘረበት ወዲያውም የሰውየው ፊት በደም ተጨማለቀ፡፡ አብረውት የነበሩት ጓደኞቹ በድርጊቱ በጣም ተደናግጠው እንደነበር በዘገባው ተመልክቷል፡፡ የ22 ዓመቱ ጀሥቲን የሙዚቃውን ኢንዱስትሪ የተቀላቀለው ገና የ15 ዓመት ታዳጊ ሣለ ነበር፡፡ ‹‹ቤቢ›› በሚለው ነጠላ ዜማው ዕውቅናን አትርፏል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያልተገቡ ባህሪያት ማሳየት መጀመሩ በሥራው ላይ እንቅፋት እየፈጠረ እንደሚገኝ ይነገራል፡፡  

* * *

 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች