Tuesday, March 5, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሜድኮ ባዮ ሜዲካል በዕውቅና ችግር የነርሲንግ ተማሪዎችን ለሌሎች ኮሌጆች እንዲያስተላልፍ ተወሰነ

ሜድኮ ባዮ ሜዲካል በዕውቅና ችግር የነርሲንግ ተማሪዎችን ለሌሎች ኮሌጆች እንዲያስተላልፍ ተወሰነ

ቀን:

– ኮሌጁ ውሳኔው ፍትሐዊነት የጐደለው ነው ብሏል

ሜድኮ ባዮ ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ካምፓስ በነርሲንግ ትምህርት ዘርፍ የዕውቅና ፈቃድ እድሳት መሥፈርቶችን ሳያሟላ በመገኘቱ እያስተማራቸው የነበሩ 130 ተማሪዎችን ፈቃድ ወዳላቸው ሌሎች የትምህርት ተቋማት እንዲያሸጋግር ጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ያደረገውን ግምገማ መሠረት በማድረግ ውሳኔ ማስተላለፉን የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ኤጀንሲው እንደሚለው ኮሌጁ የዕውቅና ፈቃድ እድሳት በጠየቀበት የነርሲንግ ትምህርት ሥልጠና ዘርፍ ግምገማ ተካሒዶ ኮሌጁ የተቀመጠውን አነስተኛ ግምገማ እንዳላሟላ ተረጋግጧል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ድጋሚ ግምገማ ተደርጎ ኮሌጁ መለኪያውን ባለማሟላቱ የ2009 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት የነርሲንግ ተማሪዎችን ዕውቅና ወዳላቸው ሌሎች ኮሌጆች እንዲያስተላልፍ ተወስኖ ተገልጾለትም ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ነገር ግን ኮሌጁ ቅሬታ በማቅረቡ ቅሬታው ተቀባይነት አግኝቶ ኮሌጁ ክፍተቶችን እንዲያሟላ የሁለት ሳምንት ጊዜ ተሰጥቶት ነበር፡፡ በመጨረሻ ጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበር በታዛቢነት ተገኝቶ በተደረገው ሌላ ግምገማ ቀደም ሲል በተሰጠው አስተያየት መሠረት ማስተካከያ ባለማድረጉ የነርሲንግ ትምህርት የዕውቅና ፈቃዱ እንዳይታደስ ተወስኗል፡፡

የሜድኮ ባዮ ሜዲካል ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መኰንን ሐጎስ ለሪፖርተር እንደገለጹት ደግሞ ውሳኔው ግራ የሚያጋባና ፍትሐዊነት የጐደለው ነው፡፡ ኮሌጁ በሁለት በሦስት ወራት ውስጥ ግራ የሚያጋቡ ደብዳቤዎች ከኤጀንሲው እንደደረሰው፤ የተደረጉት ግምገማዎችም በጎነት በጎደለው አመለካከት የተደረጉ ናቸው በማለት ተናግረዋል፡፡ ኮሌጁ ላለፉት 15 ዓመታት በነርሲንግ ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎችን ሲያሠለጥን መቆየቱን በመጠቆም ዛሬ ላይ አነስተኛ መመዘኛ አላሟላም መባሉ አጠያያቂ እንደሆነም ይገልጻሉ፡፡ ‹‹ውሳኔው በፍፁም የምንቀበለው አይደለም›› የሚሉት ዶ/ር መኰንን የኤጀንሲው ተደጋጋሚ ዕርምጃዎች ኮሌጁን እንዳዳከሙ ያስረዳሉ፡፡

ከከፍተኛ የትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የተማሪና የግብአት ምጣኔ፣ የባለሙያ ብቃትና ሌሎችም መሰል ዝርዝር ጉዳዮች በዝቅተኛ መመዘኛ ውስጥ የሚካተቱ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ኮሌጁም ምንም እንኳ ለረዥም ዓመታት የነርሲንግ ሥልጠና ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዝቅተኛውን መለኪያ አሟልቶ ባለመገኘቱ ዕርምጃው ሊወሰድበት ችሏል፡፡

የዘንድሮ ዓመት የትምህርት ዘመን ከተጀመረ በመቆየቱ በቀጣይ የተማሪዎቹ በሌሎች ዕውቅና ባላቸው ኮሌጆች የመመደብ ሒደት እንዴት ሊፋጠን ይችላል? የሚል ጥያቄ ለኤጀንሲው አቅርበን ነበር፡፡ የተማሪዎች ፍላጐትና የቦታ ቅርበት እንዲሁም የተቀባይ ኮሌጆች ፍላጐት ከግንዛቤ እንደሚገባ፣ ነገር ግን እስካሁን ተማሪዎች የሚመደቡባቸው ኮሌጆች አለመለየታቸውን የሚያረጋግጥ ምላሽ አግኝተናል፡፡ ሜድኮ የተማሪዎቹን ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ለኤጀንሲው እንዲልክ ተደርጐ የተማሪዎቹ ማስረጃ ከተመረመረ በኋላ ምደባው የሚካሔድ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ኮሌጁ በሚሰጣቸው ሌሎች ሥልጠናዎች ላይም ግምገማ እየተደረገ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመስከረም ወር ከሪፖርተር ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሙህዬ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በሥልጠና መቆየት ያለባቸውን ዓመታት ሳይቆዩ የማስመረቅ፣ ባልተፈቀደ ካምፓስ ትምህርት የመስጠትና ሲኦሲ ያልወሰዱ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስመረቅና መሰል ችግሮች እንደታየባቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...