Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል ለ23 ታራሚዎች ሞት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ተከሰሱ

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል ለ23 ታራሚዎች ሞት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ተከሰሱ

ቀን:

–  በቃጠሎው ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል ተባለ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በፌዴራል ማረሚያ ቤት ቂሊንጦ የእስረኞች ማቆያ ቤትን በማቃጠል፣ የ23 ታራሚዎች ሕይወት እንዲጠፋና ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድመዋል የተባሉ 38 ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀእናለ)ን፣ አንቀጽ 38ን፣ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ (1፣2፣4 እና 6)ን ተላልፈው መገኘታቸውን በመግለጽ ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባትና የአልሸባብ ድርጅቶችን ዓላማና ተልዕኮ በመቀበል በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ሥር የዋሉና በማረሚያ ቤት የሚገኙ መሆናቸውን በክሱ ላይ ገልጿል፡፡

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አመፅና ሁከት በኃይል በማስነሳትና ከእስር በማምለጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት በተፈረጁት ኦነግ፣ ግንቦት ሰባትና አልሸባብ ድርጅቶችን ለመቀላቀል በማሰብ፣ ተከሳሾቹ ከጥር ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ አባላት በመመልመል ከተለያዩ ዞኖች በማሰባሰብና በማደራጀት ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው በክሱ ተጠቁሟል፡፡

በውጭና በአገር ውስጥ ከሚገኙ ታራሚዎች ገንዘብ በማሰባሰብ የአመፁን ድርጊት በኃይል ይመራሉ ያሉዋቸውን በከባድ ወንጀልና በውንብድና የተከሰሱትን ታራሚዎች በመመልመል፣ ‹‹የሽብርና የዱርዬው ቡድን›› የሚል ስያሜ በመስጠት ሲመካከሩ መክረማቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

የ66 ዓመት ዕድሜ ያላቸውና በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ከእነ አቶ መላኩ ፈንታ ጋር ተከሰው በአራት ዓመታት ከስምንት ወራት የእስራት ቅጣት የተጣለባቸው የአዲስ ካርዲያክ የሕክምና ማዕከል ባለድርሻ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ፣ ለ‹‹ሽብርና ዱርዬው ቡድን›› 70,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አመፁ እንዲፈጸም ተልዕኮ መስጠታቸውንና እሳቸውም በክሱ መካተታቸውን ያስረዳል፡፡

‹‹የሽብርና ዱርዬው ቡድን›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ቡድን ተከሳሾችን በሴል በማደራጀት፣ ስለሽብር እንቅስቃሴ በማስረዳትና በመግለጽ ከመለመለ በኋላ በሚስጥር ኮድ መረጃ በመለዋወጥ አመፁን በመጋቢት ወር 2008 ዓ.ም. ለመፈጸም የተዘጋጀ ቢሆንም፣ ከውጭ ይመጣሉ ብለው ያሰቧቸው የግንቦት ሰባትና የኦነግ ታጣቂዎች በመቅረታቸው ለሌላ ጊዜ ማስተላለፋቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡

ተከሳሾቹ ለማረሚያ ቤቱ መረጃ ይሰጣሉ በማለት የጠረጠሯቸውን ታራሚዎች መግደል እንዳለባቸው በመመካከር በፌሮና በዱላ በመቀጥቀጥ መግደላቸውን፣ ፖሊስ ለቆጠራ ሲገባ አፍነው በመያዝ መሣሪያውን ቀምተው ታራሚዎች እንዲወጡ በማድረግ መኝታ ቤቱን በእሳት ማቃጠላቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ከማረሚያ ቤቱ አምልጠው ለመውጣት ዕቅድ በመያዝ ‹‹የሽብርና የዱርዬው ቡድን›› በማደራጀት ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በማረሚያ ቤቱ ላይ በፈጸሙት የእሳት ቃጠሎ ወንጀል ድርጊት፣ የ23 ታራሚዎች ሕይወት እንዲጠፋ ወይም እንዲቃጠሉ በማድረግና ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገው የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን ተላልፈዋል በማለት፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...