Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትአርባ ሺዎችን ያስተናገደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

አርባ ሺዎችን ያስተናገደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

ቀን:

ሰዎች በበርካታ የዕለት ተዕለት የኑሮ ውጣ ውረድ ተጠምደው ሲንቀሳቀሱ ከሚያሳልፉት ጊዜ፣ ለተወሰነ ሰዓት ለራሳቸው መዝናኛና መፍታቻ ይሆናቸው ዘንድ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጤንነታቸውን ለማዳበር፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያዘወትሩ ይመከራል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዓመታዊ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መድረክ ዓይነተኛ መፍትሔ መሆን ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ ምንም እንኳ በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ ስፖርታዊ ፌስቲቫል እየሆነ ለበርካቶች አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሰብዕናቸው ላይ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሙሉ ለሙሉ አምጥቷል ባይባልም በተሳታፊዎች ዘንድ የሚያሳድረው የመዝናናትና የመፍታታት ስሜቱ ግን ትልቅ ቦታ እያገኘ መጥቷል፡፡

16ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው ይህ ዓመታዊ ሕዝባዊ ስፖርት፣ በመዝናኛነት ለበርካቶች ጥሩ አደባባይ ሆኗል፡፡ ከዓመት ዓመትም የተሳታፊዎቹ ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ዘንድሮ 42,000 ደርሷል፡፡ ይህም ከአፍሪካ ከፍተኛ የተሳታፊ ቁጥር ካላቸው የጎዳና ላይ ሩጫዎች ግንባር ቀደም ለመሆን አስችሎታል፡፡ ተሳታፊዎች በሩጫው ሰዓት እርስ በርሳቸው ከሚለዋወጧቸው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እሴቶች ጎን ለጎን ለአገሪቱ ተተኪ አትሌቶች መገኛም እየሆነም ይገኛል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 16ኛ ውድድሩን ባለፈው እሑድ ኅዳር 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲያካሂድ ኢትዮጵያውያኑ ወጣቶች ፎቴን ተስፋዬ ከመሰቦ ሲሚንቶ በሴቶች፣ እንዲሁም አቤ ጌታሁን ከደብረ ብርሃን ክለብ በወንዶች አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ አሸናፊዎቹ ለውድድሩ ከቀረቡት ታዋቂ አትሌቶች አንፃር ብዙም ዕውቅና የሌላቸው እንደነበሩም ሲነገር ተደምጧል፡፡ በወንዶቹ ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው መካከል በንሳ ዲዳ፣ ልዑል ገብረሥላሴና የኔው አላምረው ይጠቀሳሉ፡፡ በፉክክሩ እንደታየው ከሆነ ለአቤ ጌታሁን ጠንካራ ተፎካሪሪ የነበረው ኬንያዊ ጀሮም ሱምባሲ ሲሆን፣ አትሌቱ በአንድ ሰከንድ ተበልጦ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁም ታይቷል፡፡ የውድድሩ አሸናፊ አቤ ጌታሁን ርቀቱን  28 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ ሲያጠናቅቅ፣ ኬንያዊው ደግሞ በአንድ ሰከንድ ልዩነት ሁለተኛ መሆኑ ሁለቱ አትሌቶች ለመሸናነፍ ያረጉትን ፉክክር ያሳያል፡፡ ሦስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ከኦሮሚያ ፖሊስ አዱኛ ታከለ ሲሆን፣ 28 ደቂቃ 55 ሰከንድ ርቀቱን ያጠናቀቀበት ጊዜ ነበር፡፡

በሴቶች መካከል በተደረገው ፉክክር ከመሰቦ ሲሚንቶ ፎንቴን ተስፋዬ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች፡፡ አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 33 ደቂቃ 09 ሰከንድ ፈጅቶባታል፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ያጠናቀቁት ደግሞ ከዱማን ክለብ መልዩ ደቀቦ 33 ደቂቃ 17 ሰከንድና ከኦሮሚያ ማረሚያ ታደለች በቀለ 33 ደቂቃ 25 ሰከንድ መሆኑ ታውቋል፡፡

በዓለም ሊሮጥባቸው ከሚገቡ አሥር ታላላቅ የጎዳና ሩጫዎች ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አንዱ መሆኑ ይነገርለታል፡፡ የዓለም አቀፍ የጎዳና ሩጫዎች ማኅበር (ኤአይኤምኤስ) አባል ሆኖ መመዝገቡ ዝግጅት ክፍሉ አስታውቋል፡፡ ማኅበሩ በ90 አገሮች ከ300 በላይ መሰል የሩጫ ውድድሮችን አቅፎ የያዘ ስለመሆኑም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከ16 ዓመት በፊት በ10,000 ተሳታፊዎች ተጀምሮ በአሁኑ ወቅት 42,000 በላይ የደረሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ ለታላላቅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መገኛም መሆኑ እየታመነበት መጥቷል፡፡ በውድድሩ የመጀመርያው አሸናፊ የታላቁ ሩጫ መሥራች ኃይሌ ገብረሥላሴ ሲሆን፣ በሴቶች ብርሃኔ አደሬ ነበረች፡፡ በሁለተኛው በወንዶች ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ሲሆን፣ በሴቶች ባለቤቱ ወርቅነሽ ኪዳኔ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በሦስተኛው በወንዶች ስለሺ ስሕን ሲሆን፣ በሴቶች ባለቤቱ ጥሩነሽ ዲባባ ነበረች፡፡ በለንደን ኦሊምፒክ በማራቶን የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊው ፀጋዬ ከበደ ከታላላቆቹ ይጠቀሳል፡፡

      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...