Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጌዴኦ የአገር ሽማግሌዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ

የጌዴኦ የአገር ሽማግሌዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ

ቀን:

ከመስከረም ወር 2009 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን በተለያዩ ከተሞች የተፈጠረውን ሁከትና የጠፋውን የሰው ሕይወት ምክንያት በማድረግ፣ በዞኑ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመ መሆኑን የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአቤቱታ ደብዳቤ አቀረቡ፡፡

ከዞኑ ተመርጠው ወደ አዲስ አበባ የተላኩት የአገር ሽማግሌዎች አቶ ጌርቾ ተሰማ ጨበሶ፣ አቶ ጌርቾ ዓለሙ ሻማና፣ አቶ ሐይቻ ደንፎ በቀቴና አቶ ሐይቻ ሚሊቄ ሾጢ ይባላሉ፡፡

የአገር ሽማግሌዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት የአቤቱታ ማመልከቻ እንደገለጹት፣ በተፈጠረው ሁከትና ረብሻ ስለጠፋው የወገን ሕይወት ያዝናሉ፡፡ ሁከቱ የተከሰተው ምንም ዓይነት የፖለቲካ አጀንዳ ሳይኖርና ማንኛውንም ብሔር ብሔረሰብ ወይም ሃይማኖትን ዒላማ ያደረገ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለሁከቱ ምክንያት የሆነው አንድ የከተማ ቦታ ለሁለት አካላት መመራቱ መሆኑን የጠቆሙት ሽማግሌዎቹ፣ ይኼ ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደርና የማዘጋጃ ቤቱ ብልሹ አሠራር ነው ብለዋል፡፡

መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ወጣቶች ግርግር ሲጀምሩ የአገር ሽማግሌዎች ለመከላከል ቢሞክሩም ሊቋቋሟቸው እንዳልቻሉ የገለጹት ሽማግሌዎቹ የ27 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን፣ የመንግሥትና የግለሰቦች ንብረት መውደሙን በደብዳቤያቸው አስረድተዋል፡፡ ችግሩ መከሰት እንዳልነበረበት ሽማግሌዎቹ ገልጸው፣ የወጣት አስተሳሰብ በመሆኑ ችግሩ ሊከሰት በመቻሉ ሁሉም የአካባቢው ሕዝብ ማዘኑን አስረድተዋል፡፡ የአገር ሽማግሌዎቹ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም ወደ ዞኑ በተላከው የፀጥታ ኃይል ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው በደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡ በተሳሳተ መረጃ መላው የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች እየተፈረጁ መሆኑንና በጅምላ ዕርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያትና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...