Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየ11ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል ዝግጅት መጠናቀቁ ይፋ ሆነ

የ11ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል ዝግጅት መጠናቀቁ ይፋ ሆነ

ቀን:

በየዓመቱ ኅዳር 29 የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ለማክበር የሚያስፈልጉትን ዝግጅቶች ማጠናቀቁን የሐረሪ ክልል አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ይህ ከ3,000 እስከ 4,000 ታዳሚዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቀው በዓል በደመቀ ሁኔታ እንዲያልፍና ለእነዚህ ታዳሚዎች የሚሆንና ከበዓሉ በኋላ አገልግሎት የሚሰጡ ሰፋፊ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በከፊል መጠናቀቃቸውም ተገልጿል፡፡

አቶ አብዱልማሊክ በከር የሐረሪ ክልል ምክትል አፈ ጉባኤና የበዓሉ ዝግጅት ዐቢይ አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ፣ ለበዓሉ ስለተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ሐረሪ ይህን ዕድል በማግኘቷ ደስተኛ እንደሆነች፣ የመቻቻልና የፍቅር አገር መሆኗን ለማሳየት የተዘጋጀችበትና እንግዶቿም የማይረሳ ትዝታ ለማሰነቅ መትጋቷን ገልጸዋል፡፡

በርካታ ሚሊዮን ብሮችን በመመደብ በክልሉ አዳዲስ ግንባታዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ነባር ግንባታዎች ላይም የማስፋፋትና የማደስ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ 56 ሺሕ ሰው የሚይዘው፣ ሆቴል የሚኖረውና በአምስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቀው ስታዲየም ግንባታ ከአዳዲሶቹ አንዱ ነው፡፡ ለበዓሉም አከባበር የመጀመሪያው ደረጃ ከነሜዳው ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ የሐረሪ ባህል ማዕከል እንዲሁ ከብዙ ዓመት መጓተት በኋላ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በውስጡም ከወጣቶች መዝናኛ እስከ 2,500 ሰዎች የሚይዝ አዳራሽ፣ ሙዚየም፣ አምፊ ቲያትር፣ የወጣቶች ማዕከልና ቢሮዎችን አካቶ ተጠናቋል፡፡ 3.4 ኪሎ ሜትር ነባር መንገድ እንደ አዲስ ተገንብቷል፡፡ ለክብር እንግዶች የሚሆን 43 ክፍሎች ያሉት የእንግዳ ማረፊያ ተሠርቷል፡፡ ይህ በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ግቢ ውስጥ በሐረሪ የቤት አሠራር ዓይነት በዘመናዊ መንገድ የተገነባና ሙሉ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡

በተለያዩ ሥፍራዎች የተገነቡት አዳዲስ ባለአራት ፎቅ የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንዱስትሪ ማምረቻ ሕንፃዎችም፣ ለበዓሉ እንዲሆኑ በማሰብ ኢንተርኔት፣ ሻወርና ልዩ ልዩ መገልገያ ተገጥሞላቸው ለእንግዳ ማረፊያነት ተዘጋጅተዋል፡፡ በዓሉ ሲያልፍ ደግሞ በአነስተኛና ጥቃቅን ለተሰማሩ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

አቶ መሐመድ ኢብራሂም ይባላሉ፡፡ ተወልደው ያደጉት ሐረር ውስጥ ነው፡፡ በቀድሞዋ ምሥራቅ ሐረርጌ በመጀመሪያ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ ሐረሪ ክልል ስትሆን ደግሞ የግንባታ ዕቃዎችን በማቅረብ ሥራ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ አሁን ላይ በሐረሪ ክልል በባለሀብቶች ተጀምሮ ግንባታቸው ከተጠናቀቁት አንዱ የሆነውና 74 የተለያየ ደረጃ ያላቸው የመኝታ ክፍሎች፣ ወንደርላንድ የሚባለው የልጆች መጫወቻዎች፣ ካፍቴሪያ፣ እንዲሁም ንግድ ሱቆች ያካተተ ሆቴል ባለቤት ናቸው፡፡ ሆቴሉ ለበዓሉ ዝግጁ እንደሆነ ተናግረው፣ ሐረሪን እያሰቃያት ያለውን የውኃ ችግር ለመፍታት ክልሉ የጀመራቸውን የውኃ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ እንዲረባረብ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ክልላችን የቱሪስት መዳረሻ ነች፡፡ ሆቴሎች እየተገነቡ ነው ኅብረተሰቡም በማደግ ላይ ነው፣ በዛው ልክ ኢንቨስትመንት እየመጣ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ቀጣይነት የሚኖራቸው የውኃው ችግር ሲቀረፍ ነው፤›› በማለት ክልሉ በውኃ እጥረት እንደሚሰቃይ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የቆየውን የውኃ ችግር ለመፍታት ምን እየተሠራ እንደሆነና በፀጥታና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሃምዛ መሐመድ፣ የክልሉን የውኃ እጥረት ለመቅረፍ ከበፊት ጀምሮ ሥራዎች እየተሠሩ ቢሆንም፣ በወሳኝ መልኩ ሊቀረፍ እንዳልቻለ ሆኖም በቅርቡ በምሥራቅ ሐረር እየተገነባ ያለው የውኃ ፕሮጀክት በተወሰነ ደረጃ ይቀርፈዋል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል፡፡ የውኃ ፕሮጀክቱ በ300 ሚሊዮን ብር በኤረር ቀበሌ ገበሬ ማኅበር እየተገነባ ሲሆን፣ ለ150 ሺሕ ሕዝብ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ ከድሬዳዋ 17 ኪሎ ሜትር አቋርጦ የሚመጣው ውኃ ለ400 ሺሕ ሕዝብ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡ ለውኃ እጥረት ምክንያት እየሆነ ያለው የኃይል አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ፣ 20 ሚሊዮን ብር ከፍለው ኃይል ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

ፀጥታን በተመለከተ ከአምስቱ አጎራባች ክልሎች ጋር ጥምር ኮሚቴ በማቋቋም እየተሠራ ሲሆን፣ ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችም አስፈላጊው ጥበቃ እንደሚደረግላቸው የሐረሪ ክልል ኅብረተሰብም የፀጥታውን ኃላፊነት እንዲወስድ መሥራታቸውን ተናግረዋል፡፡      

በተያያዘ ዜና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ያለው አባተ በዓሉን በማስመልከት ረቡዕ ኅዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ መግለጫቸው ‹‹ሕገ መንግሥታችን ለዲሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን›› በሚል መሪ ቃል ለ11ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የበዓሉ ቀን ከመድረሱ በፊትም በፌዴራሊዝም ዙሪያ ውይይቶች እንደሚደረጉም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...