የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በረኛ የነበረው የሐዋሳ ከተማው ክብረ አብ ዳዊት ሥርዓተ ቀብር ኅዳር 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ተፈጸመ፡፡
ክብረ አብ በእሳት አደጋው ከሁለት የ6 ወርና የ3 ዓመት ልጆቹ ጋር ሕይወቱ ያለፈው ኅዳር 6 ቀን ሲሆን፣ ሥርዓተ ቀብሩም በሐዋሳ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙ ታውቋል፡፡
በመኖሪያ ቤቱ በተነሳው የእሳት ቃጠሎው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ክብረ አብ በሐዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ በተጠባባቂ በረኛነት በሚጫወትበት ጊዜ፣ በማርያኖ ባሬቶ በሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ቡድን ቋሚ ተሰላፊ ነበር፡፡