Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢትዮጵያን ሠራዊት እንቅስቃሴ ተከትሎ አልሸባብ በሶማሊያ ባደረገው መስፋፋት መንግሥት ሥጋት እንደሌለው ተገለጸ

የኢትዮጵያን ሠራዊት እንቅስቃሴ ተከትሎ አልሸባብ በሶማሊያ ባደረገው መስፋፋት መንግሥት ሥጋት እንደሌለው ተገለጸ

ቀን:

በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ተጠባባቂ ኃይል ከያዛቸው ቦታዎች ከለቀቀ በኋላ፣ የሽብር ቡድኑ አልሸባብ እያደረገ በሚገኘው መስፋፋት መንግሥት ሥጋት እንደሌለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለጹ፡፡

ቃል አቀባዩ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር አሁንም በሥራው ላይ እንደሆነ፣ ከዚህ ውጪ ያለው የኢትዮጵያ ጦር እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ጥንቃቄና ኃላፊነት የተሞላበት በመሆኑ የአልሸባብ መስፋፋት በኢትዮጵያ ላይም ሆነ በአካባቢው ሥጋት አይኖርም፡፡

በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ውስጥ ሁለት ሺሕ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተልዕኮ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ በመጠን ያልተገለጸ ነገር ግን በርካታ ሺዎችን የያዘ ተጠባባቂ ጦር በሶማሊያ የተለያዩ ግዛቶች በተልዕኮ ላይ እንደሚገኝ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

ይህ ጦር በቁጥሩ ግዙፍና ተልዕኮውንም የሚቀበለው ከኢትዮጵያ መንግሥት እንደሆነ፣ ኃላፊነቱም ለኢትዮጵያ ሥጋት የሚሆኑትን ማስወገድና ለአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ድጋፍ መስጠት መሆኑ ይነገራል፡፡ ይህ ጦር ለበርካታ ጊዜያት ከያዛቸው የሶማሊያ አካባቢዎች እየለቀቀ ነው፡፡ እስካሁንም ባኩል፣ ሂራንና ጋልጋዱድ ከተባሉ አካባቢዎች ለቋል፡፡

የአልሸባብ ወታደሮች ያለምንም ችግር አንድም ጥይት ሳይተኩሱ የኢትዮጵያ ሠራዊት የለቀቃቸውን አካባቢዎች እየተቆጣጠሩ መሆኑን የአልጄዚራ የቪዲዮ ምሥል ያሳያል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ፣ የኢትዮጵያ ጦር እንቅስቃሴ ሥልታዊና በሎጂስቲክስ ችግር ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ሠራዊት ወደ ሶማሊያ የገባው እስከ መጨረሻው ለመቆየት አለመሆኑን፣ አሁን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴም ከሶማሊያ ለቆ የመውጣት እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሠራዊት ወደ ሶማሊያ የገባው በብሔራዊ የደኅንነት ሥጋት፣ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ተወልደ፣ አሁን የኢትዮጵያ ጦር የሚያደርገው እንቅስቃሴም ኃላፊነት የተሞላበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...