Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየዳያስፖራ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

የዳያስፖራ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

ቀን:

ለዛሬ ኅዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል የተጠራው የዳያስፖራ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡

የዳያስፖራ ማኅበር ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል አበበ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዳያስፖራውና በመንግሥት መካከል ባሉ ግንኙነቶች ላይ ለመምከር የተጠራው የሙሉ ቀን ስብሰባ የተራዘመው ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ነው፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ባሰራጨው መልዕክት መሠረት በስብሰባው ለመታደም ከውጭ የገቡ ዳያስፖራዎች፣ በአገር ውስጥ ያሉ ተቋማትና የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ 1,200 የሚጠጉ ተሳታፊዎች በስብሰባው እንደሚገኙ ማረጋገጫ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ ማኅበሩ ድንገት ከቦርዱ በተላለፈለት የአራዝሙ ጥያቄ ማክሰኞ ኅዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ለተሳታፊዎች ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን መግለጹን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የማኅበሩ ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ስዩም፣ ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመው አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ ብዙዎቹ በመንግሥት ኃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች ወደ ክልሎች ስለሄዱና የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመ ነው ብለዋል፡፡

ማኅበሩ የዳያስፖራ ስብሰባ ለኅዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ማዘጋጀቱን አስመልክቶ ኅዳር 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ ሰሞኑን የብሮድካስት ማስታወቂያም አስተላልፏል፡፡ በቴክኒክ ምክንያት ያሉትን አስመልክቶ አቶ አብርሃም እንደሚሉት፣ ‹‹ስብሰባውና ሌሎች ጉዳዮች ስለተደራረቡ እስከ ዜሮ ሰዓት ድረስ መረጋገጥ ነበረባቸው፡፡ ከሚመለከተው አካል ጋር ከተነጋገርን በኋላ ማራዘሙን መርጠናል፡፡ በቅርብ ቀን ስብሰባው ይደረጋል፤›› ብለዋል፡፡

ይኼንን ስብሰባ ለመታደም አጭር ጊዜ ይዘው ከውጭ የመጡ መኖራቸውን በተመለከተም፣ ‹‹ከአቅም በላይ በሆነ ጉዳይ ነው፤›› ያሉት አቶ አብርሃም፣ የተፈጠሩትን ሁኔታዎች አስተካክለው ስብሰባው መቼ እንደሚሆን በአፋጣኝ እንደሚያሳውቁና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋርም እንደሚነጋገሩበት ገልጸዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደመቀ አጥናፉ በበኩላቸው፣ ስብሰባው መራዘሙ ከማኅበሩ እንደተነገራቸውና ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡

የክልል ዳያስፖራ ጽሕፈት ቤቶች የጋራ ምክክር የውስጥ ስብሰባ ኅዳር 8 እና 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚካሄድ፣ ይኼ ስብሰባ ካለፈው ሳምንት ወደዚህኛው የተዘዋወረውም የክልል ተቋማት ተሳታፊዎች ሁለት ጊዜ ከሚመላለሱ ረቡዕ ኅዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም. የዳያስፖራ ማኅበር የጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝተው፣ በተከታዮቹ ሁለት ቀናት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የውስጥ ስብሰባ እንዲያደርጉ ታስቦ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስብሰባ የሚካሄድ መሆኑን፣ ከሩቅ የሚመጡ አንዳንድ የመንግሥት ተሳታፊዎች የዳያስፖራ ማኅበር የጠራውን ስብሰባ ለመታደም ብለው ቀድመው መግባታቸውን አክለዋል፡፡

ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፣ እንደሁም በግርግሩ ወቅት ንብረት የወደመባቸው ዳያስፖራዎች ጉዳይ፣ የመልካም አስተዳደርና ተያያዥ ጉዳዮች በስብሰባው ውይይት ይደረግባቸዋል ከተባሉ አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ‹‹ዳያስፖራው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለው ሚና›› የሚል ጽሑፍም ይቀርባል ተብሎ ታስቦ ነበር፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...