Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  የተቀዛቀዘው ኢንቨስትመንት እንዲያገግም ከመንግሥት ፈጣን ዕርምጃ ይጠበቃል!

  ኢትዮጵያ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምቹ ከሆነችባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል የፖለቲካና የማኅበራዊ መረጋጋት፣ በማደግ ላይ የሚገኝ ኢኮኖሚ፣ እጅግ በጣም ጥሩ የአየር ንብረትና ለም መሬት፣ ጠንካራ ዋስትናና ከለላ፣ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል፣ የአካባቢው እምብርትና ለዓለም ገበያ ቅርብ መሆኗ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተሻሻለና እያደገ የመጣ መሠረተ ልማትና ተወዳዳሪ የሆነ የማትጊያ ማዕቀፍ ያላት መሆኗ በተደጋጋሚ ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ከህንድ፣ ከቱርክ፣ ከቻይናና ከበርካታ አገሮች ብዛት ያላቸው ኢንቨስተሮች ሥራ ጀምረዋል፡፡ ማምረት የጀመሩና ውጤት ያገኙም አሉ፡፡ ይህ ተስፋ ሰጪ ጅምር ግን በተለያዩ መሰናክሎች በተለይ ደግሞ ባለፈው አንድ ዓመት በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ችግር ገጥሞታል፡፡ ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ የመንግሥትን ትኩረትና ፋታ የማይሰጥ ክትትል ይሻል፡፡

  አንድ አገር ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ስትሆን ከበርካታ አገሮች ጋር ከፍተኛ ፉክክር እንደሚገጥማት የታወቀ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ሳቢያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ በአበባ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ በሚገኙ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ማለትም በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በስኳርና ተያያዥ ምርቶች፣ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል፣ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ፣ በሴራሚክስ፣ በኤሌክትሮኒክስና በኤሌክትሪክ ምርቶች፣ ወዘተ ኢንቨስተሮችን የመሳብ እምቅ ኃይል ነበራት፡፡ በተግባርም አሳይታለች፡፡ አንፃራዊው ሰላምና መረጋጋት በመደፍረሱ ምክንያት ግን ይህ እምቅ ኃይል ለጊዜው ተቀዛቅዟል፡፡ ወደነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ የሆነ ትግል መደረግ አለበት፡፡ በጥናት ላይ የተመሠረተ ትግል፡፡

  መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በአስገዳጅ ሁኔታዎች ሳቢያ የመዋቅር ለውጥ ማድረጉ አንዱ ችግር ነው፡፡ መሥሪያ ቤቶች ይዋቀራሉ፣ ብዙ ሳይቆዩ ይፈርሳሉ ወይም ከሌላ ጋር ይዳበላሉ፡፡ የተጀመሩ ሥራዎች ይተውና ሌላ ዕቅድና ተቋም ይመጣል፡፡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከአንዱ ተቋም ወደ ሌላ ሲዘዋወሩ የተጀመረው ይቋረጥና አዲስ ማሰብ ይጀመራል፡፡ የመንግሥት መዋቅር በተደጋጋሚ ሲቀያየር አገሪቷንና ሕዝቧን ቤተ ሙከራ እያደረገ በመሆኑ ትልቅ ኪሳራ ያደርሳል፡፡ በሌላ በኩል የውጭ ኢንቨስተሮች በመንግሥት ላይ የሚኖራቸው መተማመን ይቀንሳል፣ ብሎም ይጠፋል፡፡ ችግሮች ሲያጋጥሙዋቸው በቀላሉ ሊፈቱላቸው የሚችሉ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከአንዱ ወደ ሌላው ሲዘዋወሩ ለእንግልት ይዳረጋሉ፡፡ ይኼ አገሪቱን የማትወጣው ችግር ውስጥ የሚከት ድርጊት ሊገታ ይገባል፡፡ አገሪቱም ከቤተ ሙከራነት መውጣት አለባት፡፡

  ሌላው በከፍተኛ ችግርነት የሚወሳው በመካከለኛው ቢሮክራሲ ውስጥ የሚታየው አደገኛ የሙስና ተግባር ነው፡፡ ይህ እንደ ሰደድ እሳት መላ አገሪቱን እየለበለበ የሚገኘው ሙስና ኢንቨስተሮችን ከማማረር አልፎ የአገሪቱንም ገጽታ እያጎደፈ ነው፡፡ መንግሥት በጀመረው ግምገማም ይሁን በተለያዩ መንገዶች በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙትን የብልሹ አሠራር ምንጮችን ጠራርጎ ማስወጣት ይኖርበታል፡፡ በሕዝቡ ላይም ሆነ በኢንቨስተሮች ላይ ሕገወጥ ድርጊት በመፈጸም ችግር በመፍጠር ላይ ያለው ይህ ሕገወጥ ኃይል፣ ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተገቢው ሕጋዊ ዕርምጃ ካልተወሰደበት አገር ያጠፋል፡፡ በስንት መከራ በማባበል የመጣን የውጭ ኢንቨስተር አማርሮ ከአገር ከማስወጣቱም በላይ፣ አገሪቱን ዳግም እንዳታንሰራራ አድርጎ ያጠፋታል፡፡ ለዚህ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው፡፡

  በቅርቡ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረው አለመረጋጋት ሳቢያ ውድመት የደረሰባቸውን የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንቶች ካሳ ከመክፈል በተጨማሪ፣ የተለያዩ ማነቃቂያዎችና ማትጊያዎችን የማድረግ ኃላፊነት በመንግሥት ጫንቃ ላይ ይወድቃል፡፡ ይህ ዓይነቱ ማዕቀፍ ተግባራዊ መደረግ ያለበት ሥጋት የገባቸው የውጭ ኢንቨስተሮች እንዳይሸሹና ወደዚህ ለመምጣት አስበው ያመነቱትን የበለጠ ለመሳብ ያግዛል፡፡ ሰላምና መረጋጋትን ከማስፈን በተጨማሪ በተለያዩ መስኮች የኢንቨስተሮችን መተማመን በፍጥነት መጨመር ተገቢ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የተለያዩ የማንቂያና የማትጊያ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ኢንቨስተሮች በሙሉ ልብ የሚሠሩበትን ዓውድ መፍጠር የግድ ይላል፡፡ ቀደም ሲል ይመረሩባቸው የነበሩትን ቢሮክራሲያዊ መሰናክሎች አንድ በአንድ ለይቶ በማወቅ ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት ተገቢ ነው፡፡ አላሠራ የሚሉ ሹማምንትን ጭምር ከኃላፊነታቸው በማንሳት ኢንቨስተሮችን መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡

  አሁን ያለው የኢንቨስትመንት ድባብ ለውጥ ያስፈልገዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ እነ ሩዋንዳን ከመሰሉ አገሮች ልምድ በመቅሰም ቀለል የሚሉ አሠራሮችን ማስፈን ተገቢ ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምን ሥርዓት በማስያዝ ለተፈለገለት ዓላማ በአግባቡ መጠቀም፣ ሰላምና መረጋጋቱን ዘለቄታዊና ለኢንቨስትመንት የሚያመች ማድረግ፣ አላስፈላጊ ሕጎችን፣ መመርያዎችንና ደንቦችን ማሻሻል ወይም መተው፣ የመሠረተ ልማት ችግሮችን መቅረፍ፣ ቢሮክራሲውን ከላይ እስከ ታች ማፅዳት፣ ከዘመኑ ጋር የማይመጠኑ ኋላቀር ድርጊቶችን ማስወገድ፣ ለኢንቨስትመንት የማይመቹ አሠራሮችን ማስወገድና በአዳዲስና አመቺ አሠራሮች መቀየር፣ ኢንቨስተሮች ለሚያቀርቡዋቸው ጥያቄዎች በአግባቡ በፍጥነት ምላሽ መስጠት፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ከተጣሉ ገደቦች ውስጥ ለኢንቨስትመንት ችግር የሚፈጥሩትን ማንሳት፣ ወዘተ. ተገቢ ተግባራት መከናወን አለባቸው፡፡ የኢንቨስተሮችን በራስ የመተማመን መንፈስ ለመጨመርና ለአገር ዕድገት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ከግምት በማስገባት ለመሠረታዊ ለውጥ መዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡ አገሪቱ በተለይ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በትራንስፖርት፣ በኃይድሮ ፓወር፣ በቴሌኮም፣ በመንገድ መሠረተ ልማት፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ በአግሮ ኢንዱስትሪና በመሳሰሉት ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችን ማግኘት አለባት፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገቱ በአስተማማኝነት የሚቀጥለውና አገሪቱም መለወጥ የምትችለው፣ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ሁሉን አቀፍ ዝግጅት ማድረግና ማስተናገድ ሲቻል ነው፡፡ የተቀዛቀዘው ኢንቨስትመንት እንዲያገግም መንግሥት ፈጣንና ወሳኝ ዕርምጃዎችን መውሰድ አለበት!  

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  አሜሪካ ሕወሓትን በማሳመንና በመጫን በሰላም ሒደቱ ትልቅ ሚና መጫወቷን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አስታወቁ

  የተመድና የአውሮፓ ኅብረት አበርክቶ አሉታዊ እንደነበር ጠቁመዋል በመንግሥትና በሕወሓት መካከል...

  አዲስ አበባና ኦሮሚያ ወሰን ለማካለል ተስማሙ

  ኮዬ ፈጬ፣ ቱሉዲምቱ፣ ጀሞ ቁጥር 2 ወደ ኦሮሚያ ለቡ፣ ፉሪና...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...

  የጉድለታችን ብዛቱ!

  ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ጎዳናውን ትውስታ እየናጠው ሁለትና...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ለዘመኑ የማይመጥን አስተሳሰብ ዋጋ ያስከፍላል!

  በኳታር እየተከናወነ ያለው የዓለም ዋንጫ በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ያልተጠበቁ ማራኪ ቴክኒኮችንና ታክቲኮችን ከአስገራሚ ውጤቶች ጋር እያስኮመኮመ፣ ከዚህ ቀደም በነበረ ችሎታና ዝና ላይ ተመሥርቶ...

  መንግሥት ለአገር የሚጠቅሙ ምክረ ሐሳቦችን ያዳምጥ!

  በሕዝብ ድምፅ የተመረጠ መንግሥት ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሐሳቦችን የማዳመጥ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሥራውን ሲያከናውንም በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በኃላፊነት መርህ መመራት ይኖርበታል፡፡ እያንዳንዱ ዕርምጃው በሕግ ከተሰጠው ኃላፊነት አኳያ...

  የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ ይደረግ!

  የሰላም ስምምነቱ ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› ሊሆን የሚችልባቸው ምልክቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ሚሊዮኖችን ለዕልቂት፣ ለመፈናቀል፣ ለከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና መሰል ሰቆቃዎች የዳረገው አውዳሚ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት...