Wednesday, February 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአሥር የቦርሳ ዲዛይነሮች ትርዒት ያሳያሉ

አሥር የቦርሳ ዲዛይነሮች ትርዒት ያሳያሉ

ቀን:

የአይኒስ ዲዛይን ባለቤት ዓይንዓለም አየለ የቦርሳ፣ የአልባሳትና ጌጣጌጥ ዲዛይነር ስትሆን፣ ላለፉት ስምንት ዓመታት በቢዝነሱ ቆይታለች፡፡ በአገር ውስጥና በውጪ አገርም የአልባሳትና ቦርሳ ትርዒቶች ሲዘጋጁ ከሚሳተፉ ዲዛይነሮች መሀከል አንዷ ናት፡፡ ከፊታችን ዓርብ ሕዳር 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በሸራተን አዲስ ለሦስት ቀናት በሚቆየው የቦርሳ ትርዒት (ባግ ሾው) ሥራዎቻቸውን ከሚያሳዩ አሥር ኢትዮጵያውያን የቦርሳ ዲዛይነሮች መሀከልም ትገኝበታለች፡፡

 የቦርሳ ትርዒቱ ቆዳ (ሌዘር) በመጠቀም አገር ውስጥ ቦርሳ የሚያዘጋጁ ዲዛይነሮች ሥራዎች ለእይታና ለሽያጭ የሚቀርቡበት ነው፡፡ ዓይንዓለም ለሪፖርተር እንደገለጸችው፣ ከዚህ ቀደም ቦርሳ ላይ ብቻ ያተኮሩ ትርዒት ተካሄዶ ስለማያውቅ፣ ‹‹ባግ ሾው›› ዲዛይነሮች ሥራዎቻቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበት መልካም አጋጣሚ ይሆናል፡፡ ‹‹ከዚህ በፊት የተዘጋጁ ትርዒቶች በልብስ ብቻ ያተኮሩ ስለሆኑ፣ ቦርሳ እንደ ማጀቢያ ይቀርባሉ፡፡ ለቦርሳ ቅድሚያ የሚሰጠው ትርዒት ለቆዳ ቦርሳ ሽያጭ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል›› ትላለች፡፡

 ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቆዳ ቦርሳዎች ገበያ እያደገ ቢሆንም፣ ያን ያህል አመርቂ እንዳልሆነ የቦርሳ ዲዛይነሮች ይገልጻሉ፡፡ ከአገር ውስጥ ቦርሳ ይልቅ ወደ ውጪ ቦርሳዎች ሸመታ የማዘንበል ነገርም አለ፡፡ ዓይንዓለም እንደምትለው፣ ኅብረተሰቡ በልዩ ልዩ ዲዛይን የተዘጋጁ የቆዳ ቦርሳዎች የመሸመት ልምዱ እንዲኖረውም ተመሳሳይ ትርዒቶች ያስፈልጋሉ፡፡ የቦርሳ ዲዛይነሮች እርስ በእርስ ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክም ይሆናል፡፡ ‹‹በትርዒቱ የምንሳተፈው የቦርሳ ዲዛይነሮች የተለያየ ተሞክሮ ስላለን አብረን መሥራታችን በዘርፉ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤›› ስትል ትናገራለች፡፡

 በዲዛይነሯ ገለጻ፣ የቆዳ ቦርሳ ዘርፍን በዋነኛነት ከሚፈታተኑት ችግሮች ውስጥ ለቦርሳ ሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ውስንነት ይጠቀሳል፡፡ የቦርሳ ዚፕ፣ ዘለበትና ሌሎችም ቁሳቁሶችን ለማግኘት አስቸጋሪ ከመሆኑ ባሻገር ገበያ ላይ ያሉትም ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም፡፡ ችግሩ የቦርሳ ዲዛይነሮችን ባጠቃላይ እንደመሆኑ በትርዒቱ አማካይነት መገናኘታቸው በኅብረት መፍትሔ ለማፈላለግ እንደሚረዳቸው ታምናለች፡፡

የአገር ውስጥ የቆዳ ቦርሳ ዲዛይነሮች ሥራዎቻቸውን ለዓለም ገበያ ያቀረቡባቸው ትርዒቶች ቢኖሩም በቂ አይደለም፡፡ ዲዛይነሯ ስለ ጉዳዩ ስትናገር፣ ‹‹በዓለም የሚወደድ ቆንጆ ቆዳ ስላለን፣ የግብዓቶች ችግር ከተቀረፈ በዓለም ተወዳዳሪ እንሆናለን፤›› ትላለች፡፡

በትርዒቱ ከአይኒስ በተጨማሪ የአፋር፣ አፍሪካን ሞዛይክ፣ ዳንኤል፣ ማቱ፣ መላ፣ ራታቱዊ ባግስ፣ ሩቢ ሌዘር አክሰሰሪስ፣ ሲባጎና ዛፍ ዲዛይነሮችም ይሳተፋሉ፡፡ ከቦርሳዎቹ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ 20 በመቶው፣ የአባታችን ጓዳ ለተሰኘው የተራድኦ ድርጅት እንደሚሰጥ ከትርዒቱ አዘጋጆች አንዱ የካክተስ ኮምንኬሽን ሥራ አስኪያጅ ያስር ባርሽ ዓርብ ህዳር 2 ቀን 2009 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል፡፡ ትርዒቱ ቅድሚያ የሰጠው ለሴት የቦርሳ ዲዛይነሮች መሆኑንም አክሏል፡፡

‹‹የገና በዓል እየደረሰ በመሆኑ ሰዎች የቆዳ ቦርሳ ለስጦታ እንዲገዙ እንፈልጋለን፡፡ የቆዳ ቦርሳ ምርትን የምናስተዋውቅበትም ትርዒት ነው፤›› ሲል ተናግሯል፡፡ ከአጋር አዘጋጆቹ መሀከል የሸራተን አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አንቶኒ ዌድ፣ ከትርዒቱ መክፈቻ ቀን በኋላ ባሉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ያለው ሽያጭ ለሕዝብ ክፍት እንደሆነና በርካታ ሸማቾች እንደሚጠብቁ ገልጿል፡፡ ሆቴሉ ማኅበረሰባዊ ግዴታቸውን ከሚወጣበት መንገድ አንዱ መሆኑንም አክሏል፡፡ ከዲዛይነሮቹ ቦርሶች መሀከል የተመረጠው ለጨረታ ቀርቦ ገቢው ለዕርዳታ እንደሚሰጥም ተናግሯል፡፡

ሌላዋ አጋር አዘጋጅ የአፍሪካን ሞዛይክ መሥራችና ሞዴል አና ጌታነህ በበኩሏ፣ ትርዒቱ ፋሽንን ከበጎ አድራጎት ጋር በማጣመሩ እንደምትደግፈው ተናግራለች፡፡ የቦርሳ ዲዛይነሮች መበረታታት እንዳለባቸውና ሥራዎቻቸው ለሕዝብ ሲደርሱ፣ የበለጠ ለመሥራት እንደሚነሳሱም ገልጻለች ‹‹ዲዛይነሮቹ እየሠሩት ያለው ሥራ ሊታይላቸው ይገባል፡፡ እርስ በእርሳቸው በመተባበርም የቆዳ ቦርሳ ዘርፉን ማሳደግ ይችላል፤›› ስትል አና አስረድታለች፡፡ ‹‹ባግ ሾው›› ዓመታዊ መርሐ ግብር የማድረግ ዕቅድ አለ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጥቁር የመልበስ ውዝግብና የእምነት ነፃነት በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኅዳር ወር ላይ በፓርላማ...

የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጠጠር ገለልተኛ ተቋም ለመመሥረት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከ70 በላይ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊቀላቀሉ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

እስቲ አንገፋፋ!

እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስንነት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው...