Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ሀገራችንን እንወቅ!›› ከተሸከርካሪ እስከ ጋሪ

ትኩስ ፅሁፎች

በምሕፃር ኤንቱኦ በመባል የሚታወቀው ብሔራዊ አስጎብኚ ድርጅት ካሰማራቸው ተሸከርካሪዎች አንዱ ከወደረኛው የቢሾፍቱ ጋሪ ጋር

*****

የጅብ ሞኝነት. . .

ከዕለታት አንድ ቀን ጅብና ቀበሮ ቤት ፍለጋ ይሄዳሉ፡፡ ጅቡ ትልቅ ቤት ሲያገኝ ቀበሮዋ ብዙ ቀዳዳዎች ያሉት ትንሽ ቤት አገኘች፡፡ ቀበሮዋም ጅቡን “አንበሳ ቢመጣብህ በየት በኩል ታመልጣለህ? እኔ ግን በቀዳዳዎቹ አመልጣለሁ፤” አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ጅቡ ቤት እንድትቀይረው ለምኗት ቤታቸውን ተቀያየሩ፡፡

ቀበሮዋም ቤቷን ቆልፋ ውስጥ ተቀመጠች፡፡ አንበሳም በመጣ ጊዜ ጅቡ አንበሳውን አባረረው፡፡ ከዚያ ጅቡና ቀበሮዋ እንደገና ተገናኝተው ምግብ እንፈልግ በማለት ምግብ ፍለጋ ተሰማሩ፡፡ ጅቡ ወፍራም በሬ ሲያገኝ ቀበሮዋ ተባይ የሞላበት አህያ አገኘች፡፡

በዚህ ጊዜ ቀበሮዋ ጅቡን “ተመልከት የእኔ አህያ ብዙ ጮማ ስላለው እያንጠባጠበ ነው የሚሄደው፤ ያንተ ግን ምንም የሚያንጠባጥበው ቅባት የለውምና እንቀያየር” አለችው፡፡ ተቀያየሩም፡፡

ከዚያ በኋላ እንደገና ሲገናኙ ቢላዋ ፍለጋ ተሰማሩ፡፡ ጅቡ ቢላዋ ሲያገኝ ቀበሮዋ ግን ላባ አገኘች፡፡ ቀበሮዋም እንዲህ አለች “አንተ ቢላዋ አለህ፡፡ ነገር ግን ቢሰበርብህ ምንም ማረድ አትችልም፡፡ እኔ ግን በቀላሉ ሌላ ላባ ስለማገኝ እንቀያየር” ብላው ተቀያየሩ፡፡

ከዚያ ቀበሮዋ በቢላው በሬውን ስታርድ ጅቡ ግን አልቻለም፡፡ “አህያውን በዚህ ላባ ላርደው አልችልም፡፡ አንቺ ልታርጂው ትችያለሽ?” ብሎ ጅቡ ቀበሮዋን ጠየቃት፡፡ ቀበሮዋም ቢላውን ጅቡ እንዳያየው በላባው ሸፍና አህያውን በማረድ አብረው በሉ፡፡

ከዚያም ሄደው መንገድ ላይ ተቀምጠው ሳለ ማርና ቅቤ የተሸከመ ግመል አዩ፡፡ ቀበሮዋም ከግመሉ ጋር የሚጓዙትን ሰዎች “ደክሞኛል፤ እባካችሁ ግመሉ ላይ ጫኑኝ::” ብላ ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም ጭነዋት ሲሄዱ ቀበሮዋ ማሩንና ቅቤውን ሙልጭ አድርጋ በልታ ቅሎቹን በሽንቷ ሞላቻቸው፡፡ ከዚያም “ቤቴ ደርሻለሁና እዚህ አውርዱኝ፡፡” አለቻቸውና ወረደች፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ገበያ ሄደው ማሩንና ቅቤውን ለመሸጥ ቅሎቹን አውርደው ሲከፍቷቸው መጥፎ ጠረን ሸተታቸው፡፡

ገዢውም “ይህ ምንድነው? ይገማል፡፡” አላቸው፡፡

የግመሉ ባለቤቶችም “አንዲት ቀበሮ ደክሞኛል ብላ ስትለምነን ጭነናት እቤቷ ስትደርስ አውርደናት ነበር፤” አሉት፡፡

ከዚያ በኋላ ቀበሮዎችን ሁሉ አንድም ሳይቀር ሰብስበው እንዲዘሉ በማድረግ ማርና ቅቤያቸውን የበላችው ግን ስለሚከብዳትና መዝለል ስለማትችል በዚህ ሊለዩዋት ወሰኑ፡፡ ከዚያም ከአጥፊዋ ቀበሮ በስተቀር ሁሉም ያለምንም ችግር ስለዘለሉ ሌባዋን ቀበሮ በመያዝ አስረዋት በኋላ ሊገርፏት ትተዋት ሄዱ፡፡

ከዚያም ጅቡ መጥቶ “ምን ሆነሻል? ለምንድነው የታሰርሺው?” አላት፡፡

ቀበሮዋም “ቅቤና ማር መብላት አልፈልግም ስላቸው አስረውኝ ሄዱ፤” አለችው፡፡ ጅቡም “ልፍታሽና እኔን እሰሪኝ፤” አላት፡፡

ነጋዴዎቹም ተመልሰው ሲመጡ ጅቡን ይገርፉት ጀመር፡፡

እሱም “ተውኝ፣ ተውኝ” ሲላቸው፡፡

“እዚህ ምን ትሰራለህ?” አሉት፡፡

“ቀበሮዋ ቅቤና ማር ታገኛለህ ስትለኝ እኔን እንድታስረኝ ጠይቄአት ነው፤” አላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ቀበሮዋ ዛፍ አናት ላይ ወጥታ በኦሮምኛ “ዓይኑን አትግረፉት፣ ጆሮውን አትግረፉት፣ ነገር ግን ሌላ ቦታ ግረፉት፤” አለቻቸው፡፡ ሰዎቹም ጅቡን ሲገርፉት ስጋው ከላዩ ላይ ስለተነሳ ለቀውት ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ ቤት እንደደረሰም ልጆቹ አይተው “አሃ! አባታችን ስጋ አመጣልን፤” ብለው በሉት፡፡ የጅብ ሞኝነት ሕይወቱን አሳጣው፡፡

  • በዘይነባ አቢበከር ደረሞ የተተረከ የሐረር ተረት

‹‹መሞትህን አላምንም››

‹‹መሞትህን አላምንም፣ ጠያይም ስንኞች›› በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃው የግጥም መድብል 66 ግጥሞች ይዟል፡፡ ገጣሚው ጌድዮን አሰፋ ሲሆን፣ በ84 ገጾች ግጥሞቹ ቀርበዋል፡፡ መጽሐፉ በ30 በመሸጥ ላይ ነው፡፡

መዝገበ ቃላት

ከመጀመሪያ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሚረዳ መዝገበ ቃላት ለገበያ ቀርቧል፡፡ በሀብታሙ መለሰ የተዘጋጀው መጽሐፉ ለባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ጂኦግራፊና ሌሎችም ትምህርቶች የሚያግዙ የተመረጡ ቃላት ይዟል፡፡ መጽሐፉ በ50 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

የስዎን እሺ የምጭንበት

ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ለባለጉዳዮች አቤቱታ በቶሎ ምላሽ አይሰጡም ነበር፡፡ በሌላ በኩል ለጠየቃቸው ሁሉ ‹‹እሺ›› እንጂ ‹‹አይሆንም›› የሚል ምላሽ አይሰጡም፡፡ በአንድ ወቅት አንድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የነበረው ግሪካዊ ለቤት መሥሪያ የሚሆን 200 ካሬ ሜትር ቦታ በፒያሳ አካባቢ እንዲሰጠው ንጉሡን አስፈቀዶ ቢትወደድ ዘንድ ይሄዳል፡፡

ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስም እንደተለመደው እሺ እያሉ ሳይፈጽሙለት ሦስት ዓመታት አለፉ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ግሪካዊው ቢትወደድ ዘንድ ይሄድና ‹‹30 አህያ፣ 20 አጋሰስና 10 ግመል የምገዛበት ገንዘብ ያበድሩኝ›› ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ በሁኔታው የተገረመው ቢትወደድም ‹‹ይህ ሁሉ የጭነት ከብት ምን ልታደርግበት ነው?›› ሲሉ ጠየቁት፤ እርሱም ‹‹ዝም ብለው ያበድሩኝ እንጂ አልነግረዎትም›› ይላቸዋል፡፡ ‹‹እንግዲያውስ ለምን እንደፈለከው ካልነገርከኝ እኔም አላበድርህም›› ሲሉት ‹‹የሰዎን እሺ የምጭንበት›› አላቸው ይባላል፡፡ በዚህን ጊዜ በነገሩ ስቀው የጠየቀውን የገንዘብ ብድር ሳይሆን ለቤት መሥሪያ የሚሆነውን ቦታ ሰጡት፤ ንጉሡም ይህንን ሰምተው ኖሮ ቢትወደድን አስጠርተው ‹‹በሰው ስታላግጥ ነገረልን›› አሉዋቸው ይባላል፡፡

  • (ካሕሣይ ገብረእግዚአብሔር)

 

*****

በል ንፈስ በል ንፈስ አንተ ሞገደኛ የክረምት ወጨፎ

በል ንፈስ፤ በል ንፈስ፤ አንተ ሞገደኛ፤ የክረምት ወጨፎ

ምንም እንኳን ባትሆን የዚያን ያህል ክፉ

ምስጋና እንደካደ እንደሰው ልጅ ጥፉ፡

እስተዚህም ባይሆን የጥርስህ ስለቱ፤

ሆኖም ብትሰወር ምንም በትታይ፤

ስትንፋስህ ጭምር ባልጎ የለም ወይ፡፡

ሆያ ሆዬ በሉ! ሆያ ሆዬ በሉ!

ለዛፍ ለቅጠሉ፣

የሸፍጥ ከሆነ አብዛኛው ሽርክና፤

አብዛኛው ፍቅርም ተራ ድንቁርና፤

ለዛፍ ለቅጠሉ፤ ሆያ ሆዬ በሏ!

የዚች ዓለም ኑሮ፤ አቤት መጣፈጧ፤

ከዊሊያም ሼክስፒር/ ስድ ትርጉም በዳዊት ዘኪሮስ

 

 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች