Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትተስፈንጣሪው ሸረሪት

ተስፈንጣሪው ሸረሪት

ቀን:

ተስፈንጣሪው ሸረሪት (ጃምፒንግ ስፓይደር) የሚዘለውን ርቀት በትክክል ለማስላት የሚያስችል ለየት ያለ እይታ አለው። ሸረሪቱ ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው? ይላል ጄደብሊው ዶት ኦርግ በድረ ገጹ፡፡

ተስፈንጣሪው ሸረሪት ዘሎ የሚያርፍበት ነገር ምን ያህል እንደሚርቅ ለመለካት ሁለቱ ዋነኛ ዓይኖቹ ያላቸውን ልዩ ችሎታ ይጠቀማል፤ የእነዚህ ዓይኖች ሬቲና ንብርብር ሆኖ የተሠራ ነው። ንብርብር ከሆኑት ክፍሎች አንደኛው አረንጓዴ ቀለምን ጥርት አድርጎ የሚቀበል ሲሆን ሌላኛው ክፍል ደግሞ ብዥ አድርጎ ይቀበላል። ምስሉ በጣም ብዥ ያለ መሆኑ ሸረሪቱ የሚያየው ነገር በጣም ቅርብ መሆኑን ለማወቅ ያስችለዋል። ይህ ደግሞ የሚዘልበትን ርቀት በትክክል ለማስላትና የሚያድነውን ነገር ለመያዝ ያስችለዋል።

ተመራማሪዎች ይህ ሸረሪት የሚጠቀምበትን ዘዴ በመቅዳት የአንድን ነገር ርቀት በትክክል መለካት የሚችሉ ባለ ሦስት ጎንዮሽ (3-D) ካሜራዎችን አልፎ ተርፎም ሮቦቶችን ለመሥራት አስበዋል። ሳይንስናው የተባለው በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የዜና አውታር እንደገለጸው ከሆነ “ግማሽ ሴንቲ ሜትር ርዝመትና ከዝንብ አንጎል ያነሰ አንጎል ያላቸው እንስሳት፣ ውስብስብ የሆኑ የእይታ መረጃዎችን ተቀብለው በዚያ መሠረት እርምጃ መውሰድ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ” ለማሳየት የተስፈንጣሪው ሸረሪት እይታ “ግሩም ምሳሌ” ነው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...