Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሰው በመግደልና ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ጌጣጌጦች በመዝረፍ የተጠረጠሩ ተከሰሱ

ሰው በመግደልና ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ጌጣጌጦች በመዝረፍ የተጠረጠሩ ተከሰሱ

ቀን:

መርካቶ አመዴ ገበያ ተብሎ በሚጠራው የገበያ ሥፍራ የወርቅና የብር ጌጣጌጦች መሥሪያና መሸጫ ሱቅ ውስጥ፣ አንድ ሰው በመግደል 10.4 ሚሊዮን ብር ዘርፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች ወደ ሱቁ በመግባት የፖሊስ መታወቂያ አሳይተው፣ በሱቁ ውስጥ ያገኙትን ወንድወሰን ገብረ ሚካኤል የተባለ ግለሰብ አንቀውና አፍነው በመግደል 465,000 ብር ጥሬ ገንዘብና ግምታቸው ከአሥር ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የብርና ወርቅ ጌጣጌጦች ዘርፈው መሰወራቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡

ተከሳሾቹ ጋሻው አጥናፉ፣ ማስተዋል እርቅይሁን፣ ዮሐንስ ታዬ፣ ደግሰው አንዱዓለም፣ ወ/ሮ ዘውድነሽ በቀለና አዳነ ዓለሙ የሚባሉ መሆናቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡

ሟች ወንድወሰንን አንቀውና አፍነው መሬት ላይ ከጣሉት በኋላ እጅና እግሩን በገመድ በማሰር የካዝና ቁልፍ ከኪሱ በመውሰድ የወንጀል ድርጊቱን መፈጸማቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል፡፡ ሟች ሕይወቱ ያለፈው በአፍንጫውና በአንገቱ ላይ በደረሰበት አፈና ምክንያት የአየር እጥረት ገጥሞት መሆኑንም አክሏል፡፡

ተከሳሾቹ ገንዘቡንና ጌጣጌጦቹን ዘርፈው ከተሰወሩ በኋላ ቤት፣ ሽጉጥና ተሽከርካሪዎች መግዛታቸውን፣ የወርቅና የብር ጌጣጌጦችን ለተለያዩ የወርቅና የብር መሸጫ ሱቆች መሸጣቸውን፣ በየግላቸው በተለያዩ ንግድ ባንኮች የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ማስቀመጣቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

ተከሳሾቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀ) እና 671(2) እና አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29(1) እና (2ሀ) ሥር የተደነገገውን ተላልፈው ወንጀሉን ፈጽመዋል ብሎ ዓቃቤ ሕግ ክሱን አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ አራተኛ፣ አምስተኛና ስድስተኛ ተከሳሾች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለታኅሳስ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ በመስጠት እስከዚያው በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ አዟል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...