Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ይድረስ ለሪፖርተርየከተማው ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተቀጣሪ ሠራተኞችንም ያስብ!

የከተማው ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተቀጣሪ ሠራተኞችንም ያስብ!

ቀን:

ሐሳቡን ያገኘነው ከትግራይ ኦንላይን ድረ ገጽ ላይ ከወጣ አንድ ጽሑፍ ያገኘነው የእንግሊዝኛ መልዕክት እንዲህ ይላል፡ “Mekle City Administration should think twice before pulling the plug on struggling businesses”፡፡

ይህ አባባል አዲስ መኪና በብድር ካልገዛችሁ በቀር ላገለገለ መኪና የታክሲ ፈቃድ አልሰጥም እያለ ለሚገኘው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የሚስማማ ይመስለናል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ለከተማዋ ይህ ነው የሚባልና ፋይዳ ያለው ፖሊሲ መከተል የተሳነው መሥሪያ ቤቱ፣ ይህን አሠራር በጉልበት በመጫን ኑሯችንን ለማሻሻል በምንፍጨረጨር ሰዎች ጫንቃ ላይ ጭኖብናል፡፡ ያለችንን ጥሪት በፈለግነው መንገድ እንዳትጠቀምባት አግዶናል፡፡

ሲሻው ሚኒባሶችን አጥፍቼ በትልልቅ አውቶቡሶች እተካቸዋለሁ ይላል፡፡ ሲያሰኘው ደግሞ ብስክሌቶችን አሠማራለሁ ይላል፡፡ እንዲህ በሚዋልለው አሠራሩ ዳፋ የትራንስርት ችግሩ ግን በየጊዜው አየተባባሰ ይገኛል፡፡

- Advertisement -

ታክሲዎች ከሴቼንቶ ወደ ላዳ የተቀየሩት እኮ በመንግሥት ጣልቃ ገብነት አይደለም፡፡ ውይይቶች ወደ ሚኒባስ የተለወጡትም እንዲሁ በመንግሥት ጣልቃ ገብነት አልነበረም፡፡ ሚኒባሶችን በአሁኑ ጊዜ ወደ ዶልፊን መከኖች የመቀየሩ አዝማሚያ ጊዜው የፈጠረው ሒደት ነው፡፡ ላዳዎችንም ወደ ዲኤክስና ወደሌላ የመኪና ዓይነቶች የመለወጥ አዝማሚያና ተፈጥሯዊ ሒደት በትራንስፖርት ባለሥልጣን ጣልቃ ገብነት ተጨናግፎ ይገኛል፡፡

ስለዚህ ቢሮው በማን አለብኝነት ብንለው ይሻላል፣ በአንድ ጀምበር ያለመውን  በተገቢው መንገድ ሳያስብበት ተግባራዊ እንደያደርገው፣ መብታችንን የማይጋፋ ውሳኔም እንዲያሳልፍ መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንፈልጋለን፡፡ ድግሪ ይዘን ሥራ ስላጣን በሹፍርና ሙያ የተሠማራን ሰዎች እንዳለን፣ እየሠራንም የምንማር እንዳለን የትራንስፖርት ባለሥልጣኑ ቢገነዘብልን ጥሩ ይመስለናል፡፡ እኛም ጥቅሱን በጥቅስ “the Addis Ababa City Administration should think twice before pulling the plug on struggling businesses”በማለት የከተማው አስተዳደር ጉዳያችንን እንዲገነዘበው እንጠይቃለን፡፡

(ተቀጣሪ የታክሲ ሾፌሮች፤ ከአዲስ አበባ)

***

የሕወሓት ሹም ሽር ‹‹ከባልሽ ባሌ ይበልጣል›› ነገር

በተለያዩ ጊዜያት የፌዴራሉ መንግሥትና የክልል ባለሥልጣናት የኃላፊነት ቦታዎችን ሲቀያየሩ ማየት በመንግሥት አስተዳደራዊ አወቃቀር ውስጥ የተለመደ ሆኗል፡፡

የክልል መንግሥታት ኃላፊዎችን ወደ ፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ማዛወር (ዲሞሽንም ይባል ፕሮሞሽን)፣ ሚኒስትሮችን ድንገት አንስቶም ወደ ክልል መውሰድ ምን ዓይነት ውሳኔ እንደሆነ የሕግ ተቀባይነት ይኖረው እንደሆነ ሳስብ ግራ ይገባኛል፡፡ ምንም እንኳ የፌዴራሉንም ሆነ የክልል መንግሥታትን የአመራር ቦታ የያዙት የኢሕአዴግ ሰዎች ብቻ በመሆናቸው እንዳሻቸው በየቦታው ቢቀያየሩም፣ ሿሚውም ሻሪውም የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚዎች ናቸው እንባላለን፡፡

 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕግ አግባብና በፓርላማ አስጸድቀው የሾሟቸውን ሚኒስትሮች የክልል መንግሥታት ጉባዔ ባደረጉና አዳዲስ ግለሰቦችን መቀያየር ባስፈልጋቸው ቁጥር፤ ጨርሶ ሰው የጠፋ፣ የታጣ ይመስል በድንገት ከሚኒስትር ቦታቸው ላይ አንስተው የፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ የሚያደርጉበት መብትና ሥልጣናቸው እስከ ምን ድረስ ይሆን? እላለሁ፡፡

ከሰሞኑ  እንደ ማራቶን ከረዘመው የሕወሓት የስብሰባ ጉዞ በኋላ፣ ሊቀመንበሩን ጨምሮ አዳዲስ የፓርቲውን ሥራ አስፈጻሚዎች እንደሾመ ተከታትለናል፡፡ ከተሿሚዎቹ ውስጥ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፌዴራል መንግሥት የሾሟቸው ሚኒስትሮች ይገኙባቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል  ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ አስመላሽ ገብረ ሥላሴ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በእርግጥ ሕወሓት እነዚህን ሰዎች ከፌዴራል የሥራ ኃላፊነታቸው አንስቶ ወደ ክልል ሲወስዳቸው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚን ይሁንታና ፈቃድ አግኝቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእነሱ ቦታ ሌሎች ሰዎችን ለፌዴራሉ መንግሥት ሊሾሙ ነው? ወይስ የፓርቲና የመንግሥት ሥራ በመደበላለቁ ተሿሚዎቹ አንድ ቀን መቐለ አንድ ቀን አዲስ አበባ እየተመላለሱ ሊሠሩ ነው? አልገባኝም፡፡ የሚያስረዳኝ እሻለሁ፡፡ በአጠቃላይ ኢሕአዴግ እንደ ገዢ ፓርቲነቱ የፌደራልና የክልል መንግሥታት የሥልጣን መዋቅሮችን የመዘርጋትና የመመደብ ኃላፊነት ቢኖርበትም፣ በየጊዜው የሥራ አመራር ለውጥ ወይም ሹም ሽር ሊደረግ ይችላል፡፡ ነገር ግን ባለሥልጣናትን ወደዚያ ወደዚህ ከማድረግ፣ ተተኪዎችን ማብቃት አይጠቅምም ትላላችሁ? ወይስ ዛሬም የፓርቲም ሆነ የመንግሥትን ኃላፊነት የሚረከቡ ወጣቶች ሕወሓት ኢሕአዴግ አላፈራም? ለነገሩ ይኼ ችግር በሕወሓት ወይም በብአዴን አለያም በኦሕዴድ ብቻ ሳይሆን፣ በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ውስጥ የሚስተዋል ነው፡፡

 ልዩነታቸው ግን ኢሕአዴግ ከኢትዮጵያን ከዳር እስከዳር እያስተዳደረ የሚገኝ፣ ተቃዋሚዎች ደግሞ የተጎሳቆለ ጽሕፈት ቤት፣ ገንዘብ አልባ ከመሆናቸው በተጨማሪ አገር በማስተደደር ኃላፊነት ላይ የሌሉበት መሆናቸው ላይ ነው፡፡ በመሆኑም የፓርቲዎች ሹምሽር ጉዳይ ቢታሰብበት እላለሁ፡፡ በደፈናው ‹‹ከባልሽ ባሌ ይበልጣል፤›› ማለትስ ይቻላልን? ነባር አመራሮችን ብቻ ወዲያ ወዲህ ከማድረግ ይልቅ ለወጣቶችና ለአዳዲስ ግለሰቦች እምነትና ኃላፊነት ለምን አይሰጥም? የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዴሞክራሲና የቴክኖሎጂ ግስጋሴ እንዲህ ያለውን አካሄድስ ይፈቅዳል? አገራዊ ፋይዳና አንድምታው አይታይም ወይ?

(ተክልዬ ጀማነህ፣ ከአዲስ አበባ)

***

ተጨማሪ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች የሥራ ግብር ይቀነስላቸው

2008 ዓ.ም. ከክረምቱ ወራት ጀምሮ መንግሥት የገቢ ግብር አዋጁን ለማሻሻል ሽር ጉድ ሲል የነበረው የሠራተኞችና የሕዝቡን የግብር ቅሬታ ለመፍታት ነበር፡፡ ከ2006 .ም. በፊት መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለጠየቀው ማብራርያ በጊዜው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ካይደኪ ገዘኸኝ በፃፉት ደብዳቤ (በቁጥር 3.0/487 27/07/2006)  የተብራራውን የገቢ ግብር አዋጅ መንግሥት ካሻሻለው በኋላ እንደገና በጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም.  በጻፉት  ደብዳቤ ወይም ስርኩላር ይኼንን ማብራርያ ማጠፋቸው ይህች አገር የምታወጣቸው ሕጎቿ እየተጣረሱሠራተኛውን ክፍል እያወዛገቡ የሚገኙ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡

            በሚገባ መታተርና በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ መሥራት መቻልን ቅጣት የሚያስከትል አስመስለውት ይገኛል፡፡ ተቀጣሪ በየሄደበት እንዲከፍል የሚገደድበት የ35 በመቶ (ምንም እንኳ ከታች ወደ ላይ እንደ ደመወዙ መጠን እየጨመረ የሚሔድም ቢሆን) የሥራ ግብር  ምናለ ቢቀር? ተጨማሪ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ተጨማሪ ሥራ ለሠሩበት ይክፈሉ ከተባለም ወደ ሁለት በመቶ ዝቅ ቢደረግ ምናለበት? ወለድ አምስት በመቶ፣ የትርፍ ድርሻ ወይም ዲቪደንድ አሥር በመቶ ቢደረግ ምን ይከፋል?

            2008  ዓ.ም. የገቢ ግብር አዋጅ ሲሻሻል ጥያቄው ቀርቦላቸው ለተጨማሪ ሥራ የሚከፈለው ግብር ሁለት በመቶ እንደሚሆን በወቅቱ የነበሩት ኃላፊ መልስ ሲሰጥበት እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ሠራተኞች ሁለት በመቶ ብቻ ነው ታክስ የሚከፍሉት በማለት ማብራርያ ሲሰጥ ልክ ዛሬ እንደተባለ ነው የማስታውሰው፡፡ ይኼ የብዙዎች ጥያቄ እንደሆነ በማሰብ ይኼንን ደብዳቤ የላክሁት ሕዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ነው፡፡

(ተክላይ ገብረማርያም፣ መቐለ)

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...