Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኦሕዴድ ከአምስት ሺሕ በላይ በሚሆኑ መካከለኛ አመራሮች ላይ ሹም ሽር ለማድረግ ግምገማ...

ኦሕዴድ ከአምስት ሺሕ በላይ በሚሆኑ መካከለኛ አመራሮች ላይ ሹም ሽር ለማድረግ ግምገማ ተቀመጠ

ቀን:

በከፍተኛ አመራር ደረጃ መሠረታዊ ሹም ሽር ያካሄደው የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ከአምስት ሺሕ በላይ በሚሆኑ መካከለኛ አመራሮች ላይም ለውጥ ለማድረግ ግምገማ ጀመረ፡፡

ኦሕዴድ በጅማ፣ በነቀምት፣ በአዳማ፣ በሐረርና በሻሸመኔ ከተሞች ከጥቅምት 25 ቀን እስከ ኅዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚቆይ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮና የካቢኔ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እየተካሄደ ባለው ‹‹ጥልቅ ተሃድሶ›› ሂስና ግለሂስ ተካሂዶ ጠንካራና ደካማ አመራሮች ይለያሉ፡፡

‹‹ችግር ያለባቸው አመራሮች ተጠያቂ የሚደረጉበት አሠራር ይሆናል፤›› ሲሉ አቶ ፍቃዱ ሪፖርተር ገለጸዋል፡፡

ከ5,000 በላይ የሚሆኑ የኦሕዴድ አመራሮች ወደ ግምገማ የገቡት፣ በማዕከል ደረጃ የሚገኘው የኦሕዴድ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ አካሂዶ መሠረታዊ የአመራር ለውጥ ካካሄደ በኋላ ነው፡፡

አቶ ፍቃዱ እንደገለጹት፣ ከመካከለኛ አመራሩ በኋላ ዝቅተኛ አመራሩም በቀጣይ ወደ ተሃድሶ ይገባል፡፡ ኦሕዴድ ቀደም ብሎ ባካሄደው የከፍተኛ አመራሮች ግምገማ የፓርቲው ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ ሙክታር ከድር፣ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩትን ወ/ሮ አስቴር ማሞ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ካቢኔም እንዲሁ ለውጥ ተደርጎ አቶ ለማ መገርሳ የክልሉ ፕሬዚዳንት፣ አቶ እሸቱ ደሴ ደግሞ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ አድርጎ ከመምረጡ በተጨማሪ፣ በርካታ የካቢኔ አባላትን በመሻር ለውጥ ተደርጓል፡፡

ኦሕዴድ በማዕከልና በካቢኔ ያደረገውን ለውጥ በመካከለኛ አመራሮች ደረጃ ለመድገም ነው ተሃድሶ የገባው ተብሏል፡፡

አቶ ፍቃዱ እንዳሉት፣ በኦሮሚያ ክልል የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ መስመርን ማጥራት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ሒደት ሥልጣንን ለግል ጥቅም ማዋል በክልሉ እየተንሰራፋ በመምጣቱ ይኼንን ዝንባሌ ማስቀረት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

‹‹ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ የመንግሥትን ሥልጣን ለሕዝብ ጥቅም ማዋል ያስፈልጋል፤›› ሲሉ አቶ ፍቃዱ የተሃድሶውን ዓላማ ገልጸዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት አንድ ዓመት ባስቆጠረው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ የበርካታዎች ሕይወት ከማለፉ በተጨማሪ በርካታ ንብረቶች ወድመዋል፡፡

በተቃውሞዎቹ ምክንያት የኦሮሚያ ክልል በዋናነት ጥያቄዎቹ የተነሱበት እንደመሆኑ፣ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ኦሕዴድ ከሌሎች የግንባሩ ፓርቲዎች ቅድሚያ ወስዶ ለውጦች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...