Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ካቢኔ ሊያዋቅር መሆኑ ተሰማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ካቢኔ ሊያዋቅር መሆኑ ተሰማ

ቀን:

  በአገር አቀፍ ደረጃ እየተነሱ ያሉ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የፌዴራል መንግሥት አዲስ ካቢኔ በመመሥረቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚሁ ቅርፅ የራሱን አዲስ ካቢኔ በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ማድረግ ሊጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በከተማው ካቢኔ ለውጥ ለማድረግ ዝግጅቱ በቅርቡ ይጀመራል፡፡

መረጃዎች እንደጠቆሙት ከካቢኔ ለውጥ በተጨማሪ የፌዴራል መንግሥቱን ቅርፅ ይዘው ተዋቅረው የነበሩት የመሬት ልማትና ማኔጀመንት ክላስተር፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር፣ የመልካም አስተዳደርና የሲቪል ሰርቪስ ክላስተሮች ይፈርሳሉ፡፡

- Advertisement -

በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ2005 ዓ.ም. ሥልጣን ከተረከበ ወዲህ፣ እየተባባሰ የመጣውን የነዋሪዎች ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ ዕርምጃዎች ቢወስድም የነዋሪዎች ጥያቄ ግን ተባብሶ ከመቀጠል ያገደው ነገር የለም፡፡

አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ጥያቄ ለመፍታት ከወሰዳቸው ዕርምጃዎች መካከል በ2005 ዓ.ም በጀት ዓመት በመጨረሻዎቹ ሦስት ወራት፣ የፈጣን ምላሽ አምጭ አሠራር ተግባራዊ አድርጎ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማስተካከል በኅዳር 2006 ዓ.ም የሠራዊት ግንባታ ዕቅድ አውጥቶ ነበር፡፡

በ2008 ዓ.ም. ደግሞ በምክትል ከንቲባውና በሁለት ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሚመሩ ክላስተሮች ተግባራዊ ከማድረጉም በተጨማሪ፣ የከተማውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አቋቁሞ በማስጠናት ላይ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤቱ እየተካሄደ የሚገኘው መጠነ ሰፊ የመዋቅር ጥናት በግንቦት 2008 ዓ.ም. ተጠናቆ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በ2009 ዓ.ም. ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ነበር፡፡ ጥናቱ እስካሁን ባለመጠናቀቁ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡

ነገር ግን በአጠቃላይ የተወሰዱት ዕርምጃዎች መጠነኛና የአንድ ሰሞን ለውጥ ከማምጣት የዘለለ አስተዋጽኦ እንዳላበረከቱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ባለጉዳዮችን ማመላለስ፣ ፋይል መደበቅ፣ ውሳኔዎች ማጓተት፣ በምልጃና በሙስና አገልግሎት መስጠት፣ ለአቤቱታ ምላሽ አለመስጠት፣ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ ሲንከባለሉ ለመጡ ሰነድ አልባ ይዞታዎች ምላሽ አለመስጠት፣ ለልማት ተነሽዎች በቂ ቤትና ምትክ ቦታ አለማዘጋጀት፣ የካሳ ክፍያ አነስተኛ መሆን፣ የሊዝ መሬት አሰጣጥ ሕግና ደንብ ያልተከተለ መሆን ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...